የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 56

56
አሕ​ዛብ ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝብ እን​ደ​ሚ​ሆኑ
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ማዳኔ ሊመጣ ምሕ​ረ​ቴም ሊገ​ለጥ ቀር​ቦ​አ​ልና ፍር​ድን ጠብቁ፤ ጽድ​ቅ​ንም አድ​ርጉ። 2ይህን የሚ​ያ​ደ​ርግ በእ​ር​ሱም ጸንቶ የሚ​ኖር፥ ሰን​በ​ታ​ት​ንም የሚ​ጠ​ብ​ቅና የማ​ያ​ረ​ክስ፥ እጁ​ንም ክፋት ከማ​ድ​ረግ የሚ​ጠ​ብቅ ሰው ብፁዕ ነው።” 3ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የተ​ጠጋ መጻ​ተኛ፥ “በእ​ው​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሕ​ዝቡ ይለ​የ​ኛል” አይ​በል፤ ጃን​ደ​ረ​ባም፥ “እነሆ፥ እኔ እንደ ደረቀ ዛፍ ነኝ” አይ​በል። 4እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለጃ​ን​ደ​ረ​ቦች እን​ዲህ ይላል፥ “ሰን​በ​ቴን ቢጠ​ብቁ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ኝ​ንም ነገር ቢመ​ርጡ፥ በቃል ኪዳ​ኔም ጸን​ተው ቢኖሩ፥ 5በቤ​ቴና በቅ​ጥሬ ውስጥ ከወ​ን​ዶ​ችና ከሴ​ቶች ልጆች ይልቅ የሚ​በ​ልጥ ስም የሚ​ያ​ስ​ጠራ ቦታን እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የማ​ይ​ጠፋ የዘ​ለ​ዓ​ለም ስም​ንም እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።” 6ከሌ​ላም ሕዝብ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​መ​ለ​ሱ​ትን ለእ​ር​ሱም ባሪ​ያ​ዎች የሆ​ኑ​ትን፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስም የወ​ደ​ዱ​ትን፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ባሪ​ያ​ዎቹ የሆ​ኑ​ትን፥ “ሰን​በ​ታ​ቴን የሚ​ጠ​ብ​ቁ​ት​ንና የማ​ያ​ረ​ክ​ሱ​ትን፥ በቃል ኪዳ​ኔም ጸን​ተው የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሁሉ፥ 7ወደ ተቀ​ደሰ ተራ​ራዬ አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በጸ​ሎ​ቴም ቤት ደስ አሰ​ኛ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ቤቴ ለአ​ሕ​ዛብ ሁሉ የሚ​ሆን የጸ​ሎት ቤት ይባ​ላ​ልና፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውና ቍር​ባ​ና​ቸ​ውም በመ​ሠ​ዊ​ያዬ ላይ የተ​መ​ረጠ ይሆ​ናል። 8ከእ​ስ​ራ​ኤል የተ​በ​ተ​ኑ​ትን የሚ​ሰ​በ​ስብ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ ወደ ተሰ​በ​ሰ​ቡት ሌሎ​ችን እሰ​በ​ስ​ብ​ለ​ታ​ለሁ” ይላል።
9እና​ንተ የም​ድረ በዳ አራ​ዊት ሁሉ ኑ፤ እና​ንተ የዱር አራ​ዊት ሁሉ ብሉ። 10ሁሉም ዕው​ራን እንደ ሆኑ ኑና እዩ፤ ሁሉ ያለ ዕው​ቀት ናቸው፤ ሁሉም ዲዳ የሆኑ ውሾች ናቸው፤ ይጮ​ኹም ዘንድ አይ​ች​ሉም፤ በመ​ኝ​ታ​ቸ​ውም ሕል​ምን ያል​ማሉ፤ ማን​ቀ​ላ​ፋ​ት​ንም ይወ​ድ​ዳሉ። 11ሁሉም ከቶ የማ​ይ​ጠ​ግቡ የረ​ከሱ ውሾች ናቸው፤ እነ​ር​ሱም ያስ​ተ​ውሉ ዘንድ የማ​ይ​ችሉ ክፉ​ዎች ናቸው፤ ሁሉም እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው እንደ ፈቃ​ዳ​ቸው መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን ተከ​ት​ለ​ዋል። 12ኑ፤ የወ​ይን ጠጅ እን​ው​ሰድ፤ በሚ​ያ​ሰ​ክ​ርም መጠጥ እን​ርካ፤ ዛሬም እንደ ሆነ እን​ዲሁ ነገ ይሆ​ናል፤ ከዛ​ሬም ይልቅ እጅግ ይበ​ል​ጣል ይላሉ።#ምዕ. 56 ቍ. 12 በዕብ. ብቻ ነው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ