ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 30:18-21

ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 30:18-21 አማ2000

አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈራጅ ነውና ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይራ​ራ​ላ​ችሁ ዘንድ ይታ​ገ​ሣል፤ ይም​ራ​ች​ሁም ዘንድ ከፍ ከፍ ይላል፤ እር​ሱን በመ​ተ​ማ​መን የሚ​ጠ​ባ​በቁ ሁሉ ብፁ​ዓን ናቸው። ቅዱስ ሕዝብ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ውስጥ በጽ​ዮን ይኖ​ራል፤ ልቅ​ሶን አል​ቅሺ፤ ይቅር በለ​ኝም በዪ፤ ልቅ​ሶ​ሽን ባየ ጊዜ ይቅር ይል​ሻል፤ ሰም​ቶ​ሻ​ልና። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የጭ​ን​ቀ​ትን እን​ጀ​ራና የመ​ከ​ራን ውኃ ይሰ​ጥ​ሃል። የሚ​ያ​ሳ​ስ​ቱ​ህም እን​ግ​ዲህ ወደ አንተ አይ​ቀ​ር​ቡም፤ ዐይ​ኖ​ችህ ግን የሚ​ያ​ሳ​ስ​ቱ​ህን ያያሉ፤ ወደ ቀኝም ቢሆን ወደ ግራም ቢሆን በኋ​ላህ በዚህ መን​ገድ እን​ሂድ የሚ​ሉና የሚ​ሳ​ሳቱ ሰዎ​ችን ድምፅ ጆሮ​ዎ​ችህ ይሰ​ማሉ።