የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ሆሴዕ 2

2
1ወን​ድ​ማ​ች​ሁን ሕዝቤ፥ እኅ​ታ​ች​ሁ​ንም፦ ሥህ​ልት በሉ​አ​ቸው።
የእ​ስ​ራ​ኤል ሕዝብ እንደ ጎሜር ማመ​ን​ዘ​ራ​ቸው
2እና​ታ​ችሁ ሚስቴ አይ​ደ​ለ​ች​ምና፥ እኔም ባልዋ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምና እና​ታ​ች​ሁን ተዋ​ቀ​ሱ​አት። ዝሙ​ቷን ከፊቷ፥#ግሪክ ሰባ. ሊ. እና አን​ዳ​ንድ ግእዝ “ከፊቴ” ይላል። ምን​ዝ​ር​ና​ዋ​ንም ከጡ​ቶ​ችዋ መካ​ከል አስ​ወ​ግ​ዳ​ለሁ። 3ዕራ​ቁ​ት​ዋ​ንም እን​ድ​ት​ቆም አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ፤ እንደ ሕፃ​ን​ነ​ትዋ ወራት፥ እንደ ተወ​ለ​ደ​ች​ባት እንደ መጀ​መ​ሪ​ያ​ዪ​ቱም ቀን አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ። እንደ ምድረ በዳም አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ፤ ውኃም እን​ደ​ሌ​ላት ምድር አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ፤ በው​ኃም ጥም እገ​ድ​ላ​ታ​ለሁ። 4የዝ​ሙት ልጆች ናቸ​ውና ልጆ​ች​ዋን ይቅር አል​ላ​ቸ​ውም። 5እና​ታ​ቸው አመ​ን​ዝ​ራ​ለ​ችና፤ የወ​ለ​ደ​ቻ​ቸ​ውም፥ “እን​ጀ​ራ​ዬ​ንና ውኃ​ዬን፥ ቀሚ​ሴ​ንና መደ​ረ​ቢ​ያ​ዬን፥ ዘይ​ቴ​ንና የሚ​ገ​ባ​ኝን ሁሉ የሚ​ሰ​ጡኝ ወዳ​ጆ​ችን እከ​ተ​ላ​ቸው ዘንድ እሄ​ዳ​ለሁ” ብላ​ለ​ችና አሳ​ፈ​ረ​ቻ​ቸው። 6ስለ​ዚህ እነሆ ጎዳ​ና​ዋን በእ​ሾህ አጥ​ረ​ዋ​ለሁ፤ መን​ገ​ድ​ዋ​ንም እዘ​ጋ​ዋ​ለሁ፤ ማለ​ፊ​ያም ታጣ​ለች። 7ወዳ​ጆ​ች​ዋ​ንም ትከ​ተ​ላ​ለች፤ ነገር ግን አት​ደ​ር​ስ​ባ​ቸ​ውም፤ ትፈ​ል​ጋ​ቸ​ው​ማ​ለች፤ ነገር ግን አታ​ገ​ኛ​ቸ​ውም፤ እር​ስ​ዋም፥ “ከዛሬ ይልቅ የዚ​ያን ጊዜ ይሻ​ለኝ ነበ​ርና ተመ​ልሼ ወደ ቀደ​መው ባሌ እሄ​ዳ​ለሁ” ትላ​ለች።
8እር​ስ​ዋም እህ​ል​ንና ወይ​ንን ዘይ​ት​ንም የሰ​ጠ​ኋት፥ ብር​ንና ወር​ቅን ያበ​ዛ​ሁ​ላት እኔ እንደ ሆንሁ አላ​ወ​ቀ​ችም። እር​ስዋ ግን ወር​ቁ​ንና ብሩን ለጣ​ዖት አደ​ረ​ገች። 9ስለ​ዚህ እህ​ሌን በጊ​ዜው፥ ወይ​ኔ​ንም በወ​ራቱ እወ​ስ​ዳ​ለሁ፤ ኀፍ​ረ​ቷ​ንም እን​ዳ​ት​ሸ​ፍን ልብ​ሴ​ንና መጎ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ዬን እገ​ፍ​ፋ​ታ​ለሁ። 10አሁ​ንም በወ​ዳ​ጆ​ችዋ ፊት ነው​ር​ዋን እገ​ል​ጣ​ለሁ፤ ከእ​ጄም ማንም አያ​ድ​ና​ትም። 11ደስ​ታ​ዋ​ንም ሁሉ፥ በዓ​ላ​ቶ​ች​ዋ​ንም፥ መባ​ቻ​ዎ​ች​ዋ​ንም፥ ሰን​በ​ቶ​ች​ዋ​ንም፥ ሥር​ዐ​ቶ​ች​ዋ​ንም ሁሉ አስ​ቀ​ራ​ለሁ። 12እር​ስ​ዋም፥ “ወዳ​ጆች የሰ​ጡኝ ዋጋዬ ይህ ነው” ያለ​ች​ውን ሁሉ ወይ​ን​ዋ​ንና በለ​ስ​ዋን አጠ​ፋ​ለሁ፤ ምስ​ክ​ርም ይሆኑ ዘንድ አኖ​ራ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የም​ድረ በዳም አራ​ዊ​ትና የሰ​ማይ ወፎች፥ የም​ድር ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾ​ችም ይበ​ሉ​ታል። 13እኔን ረስታ ወዳ​ጆ​ች​ዋን እየ​ተ​ከ​ተ​ለች፥ በጕ​ት​ቾ​ች​ዋና በጌ​ጥ​ዋም እያ​ጌ​ጠች ለበ​ኣ​ሊም የሠ​ዋ​ች​በ​ትን ወራት እበ​ቀ​ል​ባ​ታ​ለሁ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሕ​ዝቡ ያለው ፍቅር
14ስለ​ዚህ እነሆ አቅ​በ​ዘ​ብ​ዛ​ታ​ለሁ፤ ወደ ምድረ በዳም አመ​ጣ​ታ​ለሁ፤ ለል​ብ​ዋም እና​ገ​ራ​ለሁ።#ግእዝ “ልቧን አዘ​ነ​ጋ​ለሁ” ይላል። 15ከዚ​ያም የተ​ገ​ኘ​ውን ገን​ዘ​ብ​ዋን እሰ​ጣ​ታ​ለሁ፤ ምክ​ር​ዋ​ንም በአ​ኮር ሸለቆ እገ​ል​ጣ​ለሁ፤ እንደ ሕፃ​ን​ነ​ትዋ ወራት፥ ከግ​ብ​ፅም እንደ ወጣ​ች​በት ቀን ትዘ​ም​ራ​ለች።#ግሪክ ሰባ. ሊ. እና ግእዝ “ከግ​ብፅ እንደ ወጣ​ች​በት ቀን ቷረ​ዳ​ለች” ይላል።
16በዚያ ቀን ባሌ ብለሽ ትጠ​ሪ​ኛ​ለሽ እንጂ ዳግ​መኛ በዓ​ሊም ብለሽ አት​ጠ​ሪ​ኝም፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ 17የበ​ዓ​ሊ​ምን ስሞች ከአ​ፍዋ አሰ​ወ​ግ​ዳ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና፥ ስማ​ቸ​ውም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አይ​ታ​ሰ​ብም። 18በዚ​ያም ቀን ከም​ድር አራ​ዊ​ትና ከሰ​ማይ ወፎች፥ ከመ​ሬ​ትም ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾች ጋር ቃል ኪዳን አደ​ር​ግ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ። ቀስ​ት​ንና ሰይ​ፍን፥ ጦር​ንም ከም​ድሩ እሰ​ብ​ራ​ለሁ፤ ተዘ​ል​ለ​ሽም ትቀ​መ​ጫ​ለሽ። 19ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ለእኔ እን​ድ​ት​ሆኚ አጭ​ሻ​ለሁ፤ በጽ​ድ​ቅና በፍ​ርድ በም​ሕ​ረ​ትና በይ​ቅ​ርታ አጭ​ሻ​ለሁ። 20ለእ​ኔም እን​ድ​ት​ሆኚ በመ​ታ​መን አጭ​ሻ​ለሁ፤ አን​ቺም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታው​ቂ​አ​ለሽ።
21በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ይሆ​ናል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ለሰ​ማይ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ሰማ​ይም ለም​ድር ይመ​ል​ሳል፤ 22ምድ​ርም ለእ​ህል፥ ለወ​ይ​ንና ለዘ​ይት ትመ​ል​ሳ​ለች፤ እነ​ር​ሱም ለኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል ይመ​ል​ሳሉ። 23በም​ድ​ርም ላይ ለእኔ እዘ​ራ​ታ​ለሁ፤ ይቅ​ርታ የሌ​ላ​ትን ይቅር እላ​ታ​ለሁ፤#“ይቅ​ርታ የሌ​ላ​ትን ይቅር እላ​ታ​ለሁ” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ያል​ተ​ወ​ደ​ደች የነ​በ​ረ​ች​ውን እወ​ድ​ዳ​ታ​ለሁ፤ ሕዝ​ቤም ያል​ሆ​ነ​ውን፥ “አንተ ሕዝቤ ነህ” እለ​ዋ​ለሁ፤ እር​ሱም፥ “አንተ ጌታ​ዬና አም​ላኬ ነህ” ይለ​ኛል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ