ኤፍሬም እንደ ተናገረ በእስራኤል ሥርዐቱን ወሰደ፤ ለበዓልም አደረገው፤ ሞተም። ዳግመኛም በደሉ፤ ጠራቢ በሚሠራው አምሳል ከወርቃቸውና ከብራቸው ጣዖትን ሠሩ፤ እንዲህም አሉ “ሰውን ሠዉ፤ ላሙ ግን አልቋል።” ስለዚህም እንደ ማለዳ ደመና፥ በጥዋት እንደሚያልፍ ጠል፥ በዐውሎ ነፋስም ከዐውድማ እንደሚበተን እብቅ፥ ከምድጃም እንደሚወጣ ጢስ ይሆናሉ። ሰማይን ያጸናሁ፥ ምድርንም የፈጠርሁ፥ እጆችም የሰማይ ሠራዊትን ያቆሙ አምላክህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ። እንዳትከተላቸውም እነርሱን አላሳየሁህም። ከግብፅ ምድርም ያወጣሁህ እኔ ነኝ። ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ አትወቅ፤ ከእኔ በቀር የሚያድንህ የለምና። በምድረ በዳና በዞርህበት ምድር ሁሉ ጠበቅሁህ። ከተሰማራችሁ በኋላ ጠገባችሁ፤ በጠገባችሁም ጊዜ ልባችሁ ታበየ፤ ስለዚህም ረሳችሁኝ።
ትንቢተ ሆሴዕ 13 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ትንቢተ ሆሴዕ 13:1-6
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች