የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ዕብ​ራ​ው​ያን 7:1-3

ወደ ዕብ​ራ​ው​ያን 7:1-3 አማ2000

የሳ​ሌም ንጉሥ፥ የል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ካህን የሆነ፥ ይህ መልከ ጼዴቅ፥ አብ​ር​ሃም ነገ​ሥ​ታ​ትን ድል ነሥቶ በተ​መ​ለሰ ጊዜ ከእ​ርሱ ጋር ተገ​ና​ኝቶ ባረ​ከው። አብ​ር​ሃ​ምም ከገ​ን​ዘቡ ሁሉ ከዐ​ሥር አንድ ሰጠው፤ መጀ​መ​ሪያ የስሙ ትር​ጓሜ የጽ​ድቅ ንጉሥ ነበር፤ በኋ​ላም የሳ​ሌም ንጉሥ ተባለ፤ የሰ​ላም ንጉሥ ማለት ነው። አባት የለ​ውም፤ እና​ትም የለ​ች​ውም፤ ትው​ል​ዱም አይ​ታ​ወ​ቅም፤ ለዘ​መኑ መጀ​መ​ሪያ፥ ለሕ​ይ​ወ​ቱም መጨ​ረሻ የለ​ውም፤ ክህ​ነቱ የወ​ልደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምሳሌ ሆኖ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ራል።