እናንተ የተጠመቃችሁበትንና ብዙ መከራ የታገሣችሁበትን የቀደመውን ዘመን አስቡ፤ እናንተ ተሰድባችሁ ነበር፤ መከራም አጽንተውባችሁ ነበር፤ ተዘባብተውባችሁም ነበር፤ በዚህም መንገድ እንዲህ ከሆኑት ጋር ተባብራችሁ ነበር። በእስራቴም ጊዜ ከእኔ ጋር በመከራ ተባብራችኋል፤ የገንዘባችሁንም መዘረፍ በደስታ ተቀብላችኋል፤ በሰማያት ለዘለዓለም የሚኖር ከዚህ የሚበልጥና የተሻለ ገንዘብ እንዳላችሁ ታውቃላችሁና። ትልቁን ዋጋችሁን የምታገኙባትን መታመናችሁን አትጣሉ። ነገር ግን የእግዚአብሔርን ፈቃድ አድርጋችሁ የተሰጣችሁን ተስፋ ታገኙ ዘንድ መታገሥ ያስፈልጋችኋል። “ገና ጥቂት ቀን አለና፤ የሚመጣውም ፈጥኖ ይደርሳል፥ አይዘገይምም። ጻድቅ በእምነት ይድናል፤ ወደኋላ ቢመለስ ግን ልቡናዬ በእርሱ ደስ አይላትም።” እኛ ግን ነፍሳቸውን ሊያድኑ ከሚያምኑት ነን እንጂ ወደ ጥፋት ከሚያፈገፍጉት አይደለንም።
ወደ ዕብራውያን 10 ያንብቡ
ያዳምጡ ወደ ዕብራውያን 10
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ወደ ዕብራውያን 10:32-39
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos