ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 9:1-11

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 9:1-11 አማ2000

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኖኅ​ንና ልጆ​ቹን ባረ​ካ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ብዙ፤ ተባዙ፤ ምድ​ር​ንም ሙሉ​አት፤ ግዙ​አ​ትም። አስ​ፈ​ሪ​ነ​ታ​ች​ሁና አስ​ደ​ን​ጋ​ጭ​ነ​ታ​ችሁ በም​ድር አራ​ዊት፥ በሰ​ማይ ወፎች፥ በም​ድር ላይ በሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሱ​ትም፥ በባ​ሕር ዓሦ​ችም ሁሉ ላይ ይሁን፤ እነ​ር​ሱ​ንም በእ​ጃ​ችሁ ሰጠ​ኋ​ችሁ። ሕይ​ወት ያለው ተን​ቀ​ሳ​ቃሽ ሁሉ መብል ይሁ​ና​ችሁ፤ ሁሉ​ንም እንደ ለመ​ለመ ቡቃያ ሰጠ​ኋ​ችሁ። ነገር ግን ደመ ነፍስ ያለ​በ​ትን ሥጋ አት​ብሉ፤ ነፍ​ሳ​ችሁ ያለ​ች​በ​ትን ደማ​ች​ሁን ከአ​ራ​ዊት ሁሉ እጅ እሻ​ዋ​ለሁ፤ ከሰ​ውም እጅ፥ ከሰው ወን​ድም እጅ፥ የሰ​ውን ነፍስ እሻ​ለሁ። የሰ​ውን ደም የሚ​ያ​ፈ​ስስ ሁሉ ስለ​ዚያ ደም ፈንታ ደሙ ይፈ​ስ​ሳል፤ ሰውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መልክ ፈጥ​ሬ​ዋ​ለ​ሁና። እና​ን​ተም ብዙ፤ ተባዙ፤ ምድ​ር​ንም ሙሉ​አት፤ ግዙ​አ​ትም።” እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለኖኅ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ለል​ጆቹ እን​ዲህ ብሎ ተና​ገረ፦ “እኔም እነሆ፥ ቃል ኪዳ​ኔን ከእ​ና​ንተ ጋር፥ ከእ​ና​ን​ተም በኋላ ከዘ​ራ​ችሁ ጋር አጸ​ና​ለሁ፤ ከእ​ና​ንተ ጋር ላሉ​ትም፥ ሕያው ነፍስ ላላ​ቸው ሁሉ፥ ከእ​ና​ንተ ጋር ከመ​ር​ከብ ለወ​ጡት ለወ​ፎች፥ ለእ​ን​ስ​ሳ​ትም፥ ለም​ድር አራ​ዊ​ትም ሁሉ፥ ለማ​ን​ኛ​ውም ለም​ድር አራ​ዊት ሁሉ ይሆ​ናል። ቃል ኪዳ​ኔ​ንም ከእ​ና​ንተ ጋር አጸ​ና​ለሁ፤ ሥጋ ያለ​ውም ሁሉ ዳግ​መኛ በጥ​ፋት ውኃ አይ​ጠ​ፋም፤ ምድ​ር​ንም ለማ​ጥ​ፋት ዳግ​መኛ የጥ​ፋት ውኃ አይ​ሆ​ንም።”

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}