ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 50:17-20

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 50:17-20 አማ2000

‘ዮሴ​ፍን እን​ዲህ በሉት፦ እባ​ክህ የወ​ን​ድ​ሞ​ች​ህን በደል ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ይቅር በል፤ እነ​ርሱ በአ​ንተ ክፉ አድ​ር​ገ​ው​ብ​ሃ​ልና፤’ አሁ​ንም እባ​ክህ የአ​ባ​ትህ አም​ላክ ባሪ​ያ​ዎች የበ​ደ​ሉ​ህን ይቅር በል።” ዮሴ​ፍም ይህን ሲሉት አለ​ቀሰ። ወን​ድ​ሞቹ ደግሞ መጡ፤ “እነሆ፥ እኛ ለአ​ንተ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ነን” አሉት። ዮሴ​ፍም አላ​ቸው፥ “አት​ፍሩ፤ ይህ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ሆኖ​አ​ልና። እና​ንተ በእኔ ላይ ክፉ መከ​ራ​ችሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ዛሬ እንደ ሆነው ብዙ ሕዝብ እን​ዲ​መ​ገብ ለማ​ድ​ረግ ለእኔ መል​ካም መከረ።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}