የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 45:4-9

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 45:4-9 አማ2000

ዮሴ​ፍም ወን​ድ​ሞ​ቹን፥ “ወደ እኔ ቅረቡ” አላ​ቸው። ወደ እር​ሱም ቀረቡ። እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ወደ ግብፅ የሸ​ጣ​ች​ሁኝ እኔ ወን​ድ​ማ​ችሁ ዮሴፍ ነኝ። አሁ​ንም ወደ​ዚህ ስለ​ሸ​ጣ​ች​ሁኝ አት​ፍሩ፤ አት​ቈ​ር​ቈ​ሩም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሕ​ይ​ወት ከእ​ና​ንተ በፊት ልኮ​ኛ​ልና። እነሆ፥ ይህ ሁለቱ ዓመት በም​ድር ላይ ራብ የሆ​ነ​በት ነውና፤ የማ​ይ​ታ​ረ​ስ​በ​ትና የማ​ይ​ታ​ጨ​ድ​በት አም​ስት ዓመት ገና አለ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በም​ድር ላይ እን​ድ​ት​ድ​ኑና እን​ድ​ት​ተ​ርፉ እመ​ግ​ባ​ችሁ ዘንድ ከእ​ና​ንተ በፊት ላከኝ። አሁ​ንም እና​ንተ ወደ​ዚህ የላ​ካ​ች​ሁኝ አይ​ደ​ላ​ች​ሁም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላከኝ እንጂ፤ ለፈ​ር​ዖ​ንም እንደ አባት አደ​ረ​ገኝ፤ በቤ​ቱም ሁሉ ላይ ጌታ፥ በግ​ብፅ ምድ​ርም ሁሉ ላይ አለቃ አደ​ረ​ገኝ። አሁ​ንም ፈጥ​ና​ችሁ ወደ አባቴ ሂዱ፤ እን​ዲ​ህም በሉት፦ ልጅህ ዮሴፍ የሚ​ለው ነገር ይህ ነው፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በግ​ብፅ ምድር ሁሉ ላይ ጌታ አደ​ረ​ገኝ፤ ወደ እኔ ና፤ በዚ​ያም አት​ዘ​ግይ፤

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}