ያዕቆብም በግብፅ የሚሸመት እህል እንዳለ ሰማ፤ ልጆቹንም፥ “ለምን ትተክዛላችሁ?” አላቸው። እንዲህም አለ፥ “እነሆ፥ እህል በግብፅ እንዳለ ሰምቼአለሁ፤ ወደዚያ ውረዱ፤ እንድንድንና በራብ እንዳንሞትም ከዚያ ሸምቱልን።” የዮሴፍም ዐሥሩ ወንድሞቹ እህልን ከግብፅ ይሸምቱ ዘንድ ወረዱ፤ የዮሴፍን ወንድም ብንያምን ግን ያዕቆብ ከወንድሞቹ ጋር አልሰደደውም፥ “ምናልባት ክፉ እንዳያገኘው” ብሎአልና። የእስራኤልም ልጆች ለእህል ሸመታ ከመጡት ጋር ገቡ፤ በከነዓን ሀገር ራብ ነበርና። ዮሴፍም በግብፅ ምድር ላይ ገዥ ነበረ፤ እርሱም ለምድር ሕዝብ ሁሉ እህል ይሸጥ ነበር፤ የዮሴፍም ወንድሞች በመጡ ጊዜ በምድር ላይ በግንባራቸው ሰገዱለት። ዮሴፍም ወንድሞቹን በአያቸው ጊዜ ዐወቃቸው፤ እንደማያውቃቸውም ሆነ፤ ክፉ ቃልንም ተናገራቸው፥ “እናንተ ከወዴት መጣችሁ?” አላቸው። እነርሱም፥ “ከከነዓን ምድር እህል ልንሸምት የመጣን ነን” አሉት። ዮሴፍም ወንድሞቹን ዐወቃቸው፤ እነርሱ ግን አላወቁትም፤ ዮሴፍም አይቶት የነበረውን ሕልም ዐሰበ። እንዲህም አላቸው፥ “እናንተ ሰላዮች ናችሁ ፤ የሀገሩን ሁኔታ ልታዩ መጥታችኋል።” እነርሱም አሉት፥ “ጌታ ሆይ፥ አይደለም፤ ባሪያዎችህስ ስንዴ ሊገዙ መጥተዋል፤ እኛ ሁላችን የአንድ ሰው ልጆች ነን፤ እኛ የሰላም ሰዎች ነን፤ ባሪያዎችህስ ሰላዮች አይደሉም።” እርሱም አላቸው፥ “አይደለም፤ ነገር ግን እናንተ ሰላዮች ናችሁ፤ የሀገሩንም ሁኔታ ልታዩ መጥታችኋል።” እነርሱም አሉ፥ “ባሪያዎችህ በከነዓን ምድር የምንኖር ዐሥራ ሁለት ወንድማማቾች ነን፤ ታናሹም እነሆ ዛሬ ከአባታችን ጋር ነው፤ ሌላውም ሞቶአል።” ዮሴፍም አላቸው፥ “እናንተ ሰላዮች ናችሁ ብዬ የተናገርሁአችሁም ይህ ነው፤ በዚህ ትታወቃላችሁ፤ ታናሽ ወንድማችሁን ከአላመጣችሁ በቀር ‘የፈርዖንን ሕይወት!’ ከዚህ አትወጡም። ወንድማችሁን ያመጣ ዘንድ ከእናንተ አንዱን ላኩ፤ እናንተ ግን እውነትን የምትናገሩ ከሆነ ወይም ከአልሆነ ነገራችሁ እስኪታወቅ ድረስ ከዚህ ተቀመጡ፤ ይህ ከአልሆነ ‘የፈርዖንን ሕይወት!’ ሰላዮች ናችሁ።” ሦስት ቀን ያህልም በግዞት ቤት ጨመራቸው። በሦስተኛው ቀን ዮሴፍ እንዲህ አላቸው፥ “ትድኑ ዘንድ ይህን አድርጉ፤ እኔ እግዚአብሔርን እፈራለሁና። እናንተ ሰላማውያን ከሆናችሁ ከእናንተ አንዱ ወንድማችሁ በግዞት ቤት ይታሰር፤ እናንተ ግን ሂዱ፤ የሸመታችሁትን እህልም ውሰዱ፤ ታናሹንም ወንድማችሁን ወደ እኔ አምጡ፤ ነገራችሁ የታመነ ይሆናልና፤ ይህ ከአልሆነ ግን ትሞታላችሁ።” እንዲህም አደረጉ።
ኦሪት ዘፍጥረት 42 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኦሪት ዘፍጥረት 42:1-20
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos