ፈርዖንም ዮሴፍን አለው፥ “እግዚአብሔር ይህን ሁሉ ገልጦልሃልና ከአንተ ይልቅ ብልህና ዐዋቂ ሰው የለም። አንተ በቤቴ ላይ ተሾም፤ ሕዝቤም ሁሉ ለቃልህ ይታዘዝ፤ እኔም ከዙፋኔ በቀር ከአንተ የምበልጥበት የለም።” ፈርዖንም ዮሴፍን፥ “በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ሾምሁህ” አለው። ፈርዖን ቀለበቱን ከእጁ አወለቀ፤ በዮሴፍም እጅ አደረገው፤ የነጭ ሐር ልብስንም አለበሰው፤ በአንገቱም የወርቅ ዝርግፍን አደረገለት፤ የእርሱም በምትሆን በሁለተኛይቱ ሰረገላ አስቀመጠው፤ ስገዱ እያለም በፊት በፊቱ አዋጅ ነጋሪ እንዲሄድ አደረገ፤ በግብፅ ምድር ሁሉ ላይም ሾመው። ፈርዖንም ዮሴፍን አለው፥ “እኔ ራሴ ፈርዖን ነኝ፤ በግብፅ ሀገር ሁሉ ያለ አንተ ማንም እጁን አያንሣ።”
ኦሪት ዘፍጥረት 41 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኦሪት ዘፍጥረት 41:39-44
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos