የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 41:14-25

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 41:14-25 አማ2000

ፈር​ዖ​ንም ልኮ ዮሴ​ፍን አስ​ጠ​ራው፤ ከግ​ዞት ቤትም አወ​ጡት፤ ራሱ​ንም ላጩት፤ ልብ​ሱ​ንም ለወጡ፤ ወደ ፈር​ዖ​ንም ገባ። ፈር​ዖ​ንም ዮሴ​ፍን አለው፥ “ሕል​ምን አየሁ፤ የሚ​ተ​ረ​ጕ​ም​ል​ኝም አጣሁ፤ ሕል​ምን እንደ ሰማህ፥ እንደ ተረ​ጐ​ም​ህም ስለ አንተ ሰማሁ።” ዮሴ​ፍም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከገ​ለ​ጸ​ለት ሰው በቀር መተ​ር​ጐም የሚ​ችል የለም” ብሎ ለፈ​ር​ዖን መለ​ሰ​ለት። ፈር​ዖ​ንም ለዮ​ሴፍ እን​ዲህ አለው፥ “እነሆ፥ በሕ​ልሜ በወ​ንዝ ዳር ቆሜ ነበር፤ እነ​ሆም፥ ሥጋ​ቸው የወ​ፈረ፥ መል​ካ​ቸ​ውም ያማረ ሰባት ላሞች ወጡ፤ በወ​ንዙ ዳር በመ​ስ​ኩም ይሰ​ማሩ ነበር፤ ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ እነሆ፥ የደ​ከሙ፥ መል​ካ​ቸ​ውም እጅግ የከፋ፥ ሥጋ​ቸ​ውም የከሳ ሌሎች ሰባት ላሞች ከወ​ንዙ ወጡ፤ በግ​ብ​ፅም ምድር ሁሉ እንደ እነ​ርሱ መልከ ክፉ ከቶ አላ​የ​ሁም፤ እነ​ዚያ የከ​ሱ​ትና መልከ ክፉ​ዎቹ ላሞች እነ​ዚ​ያን የመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ዎ​ቹን ያማ​ሩና የወ​ፈሩ ሰባት ላሞች ዋጡ​አ​ቸው፤ በሆ​ዳ​ቸ​ውም ተዋጡ፤ በሆ​ዳ​ቸ​ውም ውስጥ የገባ እን​ደ​ሌለ ሆኑ፤ መል​ካ​ቸ​ውም በመ​ጀ​መ​ሪያ እንደ ነበ​ረው የከፋ ነበረ፤ ነቃ​ሁም። ዳግ​መ​ኛም ተኛሁ፤ በሕ​ል​ሜም እነሆ፥ የጐ​መ​ሩና መል​ካም የሆኑ ሰባት እሸ​ቶች ከአ​ንድ አገዳ ሲወጡ አየሁ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ እነሆ የሰ​ለ​ቱና በነ​ፋስ የተ​መቱ ሌሎች ሰባት እሸ​ቶች ወጡ፤ እነ​ዚያ የሰ​ለ​ቱ​ትና በነ​ፋስ የተ​መ​ቱት እሸ​ቶች እነ​ዚ​ያን ያማ​ሩ​ት​ንና የጐ​መ​ሩ​ትን ሰባ​ቱን እሸ​ቶች ዋጡ​አ​ቸው። ለሕ​ልም ተር​ጓ​ሚ​ዎ​ችም ሕል​ሜን ነገ​ርሁ፤ የተ​ረ​ጐ​መ​ል​ኝም የለም።” ዮሴ​ፍም ፈር​ዖ​ንን አለው፥ “የፈ​ር​ዖን ሕልሙ አንድ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊያ​ደ​ር​ገው ያለ​ውን ለፈ​ር​ዖን አሳ​ይ​ቶ​ታል።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}