የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 37:26-36

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 37:26-36 አማ2000

ይሁ​ዳም ወን​ድ​ሞ​ቹን እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ወን​ድ​ማ​ች​ንን ገድ​ለን ደሙን ብን​ሸ​ሽግ ጥቅ​ማ​ችን ምን​ድን ነው? ኑ፥ ለእ​ነ​ዚህ ይስ​ማ​ኤ​ላ​ው​ያን እን​ሽ​ጠው፤ እጃ​ች​ንን ግን በእ​ርሱ ላይ አን​ጣል፤ ወን​ድ​ማ​ችን ሥጋ​ችን ነውና።” ወን​ድ​ሞ​ቹም የነ​ገ​ራ​ቸ​ውን ሰሙት። እነ​ዚያ ይስ​ማ​ኤ​ላ​ው​ያን ነጋ​ዴ​ዎ​ችም ሲያ​ልፉ ወን​ድ​ሞቹ ዮሴ​ፍን ከጕ​ድ​ጓድ ጐት​ተው አወ​ጡት፤ ለይ​ስ​ማ​ኤ​ላ​ው​ያ​ንም ዮሴ​ፍን በሃያ ብር ሸጡት፤ እነ​ር​ሱም ዮሴ​ፍን ወደ ግብፅ ወሰ​ዱት። ሮቤ​ልም ወደ ጕድ​ጓዱ ተመ​ለሰ፤ እነ​ሆም፥ ዮሴ​ፍን ከጕ​ድ​ጓድ በአ​ጣው ጊዜ ልብ​ሱን ቀደደ። ሮቤ​ልም ወደ ወን​ድ​ሞቹ ተመ​ልሶ፥ “ብላ​ቴ​ናው በጕ​ድ​ጓድ የለም፤ እን​ግ​ዲህ እኔ ወዴት እሄ​ዳ​ለሁ?” አለ። የዮ​ሴ​ፍ​ንም ቀሚስ ወሰዱ፤ የፍ​የ​ልም ጠቦት አር​ደው ቀሚ​ሱን በደም ነከ​ሩት። ብዙ ኅብር ያለ​በ​ትን ቀሚ​ሱ​ንም ላኩ፤ ወደ አባ​ታ​ቸ​ውም አገ​ቡት፤ እን​ዲ​ህም አሉት፥ “ይህን ልብስ አገ​ኘን፤ ይህ የል​ጅህ ልብስ እንደ ሆነ ወይም እን​ዳ​ል​ሆነ እስኪ እየው?” እር​ሱም ዐውቆ፥ “የልጄ ቀሚስ ነው፤ ክፉ አውሬ በል​ቶ​ታል፤ ዮሴ​ፍን ቦጫ​ጭ​ቆ​ታል” አለ። ያዕ​ቆ​ብም ልብ​ሱን ቀደደ፤ በወ​ገ​ቡም ማቅ ታጥቆ ለልጁ ብዙ ቀን አለ​ቀሰ። ወን​ዶች ልጆ​ቹና ሴቶች ልጆቹ ሁሉ ተሰ​ብ​ስ​በው መጡ። ኀዘ​ኑ​ንም ያስ​ተ​ዉት ዘንድ አባ​ታ​ቸ​ውን ማለ​ዱት። ኀዘ​ኑ​ንም መተ​ውን እንቢ አለ፥ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ወደ ልጄ ወደ መቃ​ብር እያ​ዘ​ንሁ እወ​ር​ዳ​ለሁ።” አባ​ቱም ስለ እርሱ አለ​ቀሰ። እነ​ዚያ ይስ​ማ​ኤ​ላ​ው​ያን ሰዎች ግን ዮሴ​ፍን በግ​ብፅ ለፈ​ር​ዖን ጃን​ደ​ረባ ለዘ​በ​ኞቹ አለቃ ለጲ​ጥ​ፋራ ሸጡት።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}