የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 29

29
ያዕ​ቆብ ወደ ላባ ቤት መድ​ረሱ
1ያዕ​ቆ​ብም በማ​ለዳ ተነ​ሥቶ የያ​ዕ​ቆ​ብና የዔ​ሳው እናት የር​ብቃ ወን​ድም የሶ​ርያ ሰው የባ​ቱ​ኤል ልጅ ወደ​ሚ​ሆን ወደ ላባ ሄደ። 2በተ​መ​ለ​ከ​ተም ጊዜ በሜ​ዳው እነሆ ጕድ​ጓ​ድን አየ፤ በዚ​ያም ሦስት የበ​ጎች መን​ጎች በላዩ ተመ​ስ​ገው ነበር፤ ከዚ​ያች ጕድ​ጓድ በጎ​ቹን ያጠጡ ነበ​ርና፤ በጕ​ድ​ጓ​ድ​ዋም አፍ ታላቅ ድን​ጋይ ነበ​ረች። 3መን​ጎ​ችም ሁሉ ከዚያ በተ​ሰ​በ​ሰቡ ጊዜ እረ​ኞች ድን​ጋ​ይ​ዋን ከጕ​ድ​ጓዱ አፍ ገለል አድ​ር​ገው በጎ​ቹን ያጠጡ ነበር፤ ድን​ጋ​ይ​ዋ​ንም ወደ ስፍ​ራው መል​ሰው በጕ​ድ​ጓዱ አፍ እን​ደ​ገና ይገ​ጥ​ሙት ነበር። 4ያዕ​ቆ​ብም፥ “ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ እና​ንት ከወ​ዴት ናችሁ?” አላ​ቸው። 5እነ​ር​ሱም፥ “እኛ ከካ​ራን ነን” አሉት። “የና​ኮ​ርን ልጅ ላባን ታው​ቁ​ታ​ላ​ች​ሁን?” አላ​ቸው። እነ​ር​ሱም፥ “እና​ው​ቀ​ዋ​ለን” አሉት። 6“እርሱ ደኅና ነውን?” አላ​ቸው። እነ​ር​ሱም፥ “አዎ ደኅና ነው፤ አሁ​ንም ልጁ ራሔል የአ​ባ​ቷን በጎች ይዛ ትመ​ጣ​ለች” አሉት። 7እር​ሱም፥ “ቀኑ ገና ቀትር ነው፥ ከብ​ቶቹ የሚ​ሰ​በ​ሰ​ቡ​በት ሰዓ​ቱም ገና አል​ደ​ረ​ሰም፤ አሁ​ንም በጎ​ቹን አጠ​ጡና ሄዳ​ችሁ አሰ​ማ​ሩ​አ​ቸው” አላ​ቸው። 8እነ​ር​ሱም አሉ፥ “እረ​ኞች ሁሉ ካል​ተ​ሰ​በ​ሰ​ቡና ድን​ጋ​ዪ​ቱን ከጕ​ድ​ጓዱ አፍ ካላ​ነ​ሡ​አት በቀር አን​ች​ልም፤ ከዚ​ያም በኋላ በጎ​ቹን እና​ጠ​ጣ​ለን።” 9እር​ሱም ገና ከእ​ነ​ርሱ ጋር ሲነ​ጋ​ገር እነሆ፥ የላባ ልጅ ራሔል የአ​ባ​ት​ዋን በጎች ይዛ ደረ​ሰች፤ እር​ስዋ የአ​ባ​ቷን በጎች ትጠ​ብቅ ነበ​ርና። 10ያዕ​ቆ​ብም የእ​ና​ቱን ወን​ድም የላ​ባን ልጅ ራሔ​ል​ንና የአ​ጎ​ቱን የላ​ባን በጎች በአየ ጊዜ ቀረበ፤ ከጕ​ድ​ጓ​ዱም አፍ ድን​ጋ​ዩን አነሣ፤ የአ​ጎ​ቱን የላ​ባን በጎ​ችም አጠጣ። 11ያዕ​ቆ​ብም ራሔ​ልን ሳማት፤ ቃሉ​ንም ከፍ አድ​ርጎ አለ​ቀሰ። 12ያዕ​ቆ​ብም የአ​ባቷ ዘመ​ድና የር​ብቃ ልጅ መሆ​ኑን ለራ​ሔል አስ​ታ​ወ​ቃት፤ እር​ስ​ዋም ሮጣ ሄዳ ለአ​ባቷ ይህን ነገር ነገ​ረ​ችው።
13ላባም የእ​ኅ​ቱን የር​ብ​ቃን ልጅ የያ​ዕ​ቆ​ብን ስም#ዕብ. “ዜና” ይላል። በሰማ ጊዜ ሊቀ​በ​ለው ሮጠ፥ አቅ​ፎም ሳመው፥ ወደ ቤቱም አገ​ባው። ነገ​ሩ​ንም ሁሉ ለላባ ነገ​ረው። 14ላባም ያዕ​ቆ​ብን፥ “በእ​ው​ነት አንተ አጥ​ንቴ ሥጋ​ዬም ነህ፤ ከእኔ ጋር ተቀ​መጥ” አለው። አንድ ወር የሚ​ያ​ህ​ልም ከእ​ርሱ ጋር ተቀ​መጠ።
ያዕ​ቆብ ስለ ራሔ​ልና ልያ ላባን ማገ​ል​ገሉ
15ላባም ያዕ​ቆ​ብን፥ “ወን​ድሜ ስለ​ሆ​ንህ በከ​ንቱ አታ​ገ​ለ​ግ​ለ​ኝም ደመ​ወ​ዝህ ምን​ድን ነው? ንገ​ረኝ” አለው 16ለላ​ባም ሁለት ሴቶች ልጆች ነበ​ሩት፤ የታ​ላ​ቂቱ ስም ልያ የታ​ና​ሺ​ቱም ስም ራሔል ነበረ። 17ልያም ዓይነ ልም ነበ​ረች፤ ራሔል ግን መልከ መል​ካም ነበ​ረች፥ ፊቷም ውብ ነበረ። 18ያዕ​ቆ​ብም ራሔ​ልን ወደ​ዳት፤ ያዕ​ቆ​ብም ላባን እን​ዲህ አለው፥ “ስለ ታና​ሺቱ ልጅህ ስለ ራሔል ሰባት ዓመት እገ​ዛ​ል​ሃ​ለሁ። ሚስት ትሆ​ነኝ ዘንድ እር​ስ​ዋን ስጠኝ”#“ሚስት ትሆ​ነኝ ዘንድ እር​ስ​ዋን ስጠኝ” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. እና በዕብ. የለም። አለው። 19ላባም፥ “ለሌላ ሰው ከም​ሰ​ጣት ይልቅ ለማ​ው​ቅህ ለዘ​መዴ ለአ​ንተ ብሰ​ጣት ይሻ​ላል፤ ከእኔ ጋር ተቀ​መጥ” አለው። 20ያዕ​ቆ​ብም ስለ ራሔል ሰባት ዓመት ተገዛ፤ እር​ስ​ዋ​ንም ይወ​ድ​ዳት ስለ​ነ​በረ በእ​ርሱ ዘንድ ጥቂት ቀን ሆነ​ለት።
21ያዕ​ቆ​ብም ላባን፥ “እን​ግ​ዲህ ወደ እር​ስዋ እገባ ዘንድ ሚስ​ቴን ስጠኝ፥ ቀኔ ተፈ​ጽ​ሞ​አ​ልና አለው።” 22ላባም የዚ​ያን ስፍራ ሰዎች ሁሉ ሰበ​ሰበ፥ ሰር​ግም አደ​ረገ። 23በመ​ሸም ጊዜ ልጁን ልያን ወስዶ ወደ ያዕ​ቆብ አስ​ገ​ባት፤ ያዕ​ቆ​ብም ወደ እር​ስዋ ገባ። 24ላባም ለልጁ ልያ አገ​ል​ጋ​ዪ​ቱን ዘለ​ፋን አገ​ል​ጋይ ትሆ​ናት ዘንድ ሰጣት። 25በነ​ጋም ጊዜ እነሆ ልያ ነበ​ረች፤ ያዕ​ቆ​ብም ላባን፥ “ምነው እን​ደ​ዚህ አደ​ረ​ግ​ህ​ብኝ? ያገ​ለ​ገ​ል​ሁህ ስለ ራሔል አል​ነ​በ​ረ​ምን? ለምን አታ​ለ​ል​ኸኝ?” አለው። 26ላባም እን​ዲህ አለ፥ “በሀ​ገ​ራ​ችን ታላ​ቂቱ ሳለች፥ ታና​ሺ​ቱን እን​ሰጥ ዘንድ ወግ አይ​ደ​ለም፤ 27ለዚ​ችም ሰባት ዓመት ፈጽም፤ ሌላ ሰባት ዓመት ደግሞ እኔን ስለ​ም​ታ​ገ​ለ​ግ​ለኝ አገ​ል​ግ​ሎት እር​ስ​ዋን ደግሞ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።” 28ያዕ​ቆ​ብም እን​ዲህ አደ​ረገ፤ ለዚ​ችም ሰባት ዓመት ፈጸመ፤ ልጁን ራሔ​ል​ንም ለእ​ርሱ ሚስት ትሆ​ነው ዘንድ ሰጠው። 29ላባም ለልጁ ለራ​ሔል አገ​ል​ጋ​ዪ​ቱን ባላን አገ​ል​ጋይ ትሆ​ናት ዘንድ ሰጣት። 30ያዕ​ቆ​ብም ወደ ራሔል ደግሞ ገባ። ራሔ​ል​ንም ከልያ ይልቅ ወደ​ዳት፤ ሌላ ሰባት ዓመ​ትም ተገ​ዛ​ለት።
ለያ​ዕ​ቆብ የተ​ወ​ለዱ ልጆች
31እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ልያ የተ​ጠ​ላች መሆ​ን​ዋን በአየ ጊዜ ማኅ​ፀ​ን​ዋን ከፈ​ተ​ላት፤ ራሔል ግን መካን ነበ​ረች። 32ልያም ፀነ​ሰች፤ ወንድ ልጅ​ንም ወለ​ደች፥ ስሙ​ንም ሮቤል ብላ ጠራ​ችው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መዋ​ረ​ዴን አይ​ቶ​አ​ልና፥ እን​ግ​ዲ​ህስ ወዲህ ባሌ ይወ​ድ​ደ​ኛል” ስትል። 33ልያም ዳግ​መኛ ፀነ​ሰች፤ ሁለ​ተኛ ወንድ ልጅ​ንም ለያ​ዕ​ቆብ ወለ​ደ​ች​ለት፤ “እኔ እንደ ተጠ​ላሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ሰማ ይህን ጨመ​ረ​ልኝ” አለች፤ ስሙ​ንም ስም​ዖን ብላ ጠራ​ችው ። 34ደግ​ሞም ፀነ​ሰች፤ ወንድ ልጅ​ንም ወለ​ደች፤ “ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲ​ህስ ባሌ ወደ እኔ ይጠ​ጋል፤ ሦስት ወን​ዶች ልጆ​ችን ወል​ጄ​ለ​ታ​ለ​ሁና” አለች፤ ስለ​ዚ​ህም ስሙን ሌዊ ብላ ጠራ​ችው። 35ደግ​ሞም ፀነ​ሰች፤ ወንድ ልጅ​ንም ወለ​ደች፤ በዚ​ህም ጊዜ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ግ​ና​ለሁ” አለች፤ ስለ​ዚ​ህም ስሙን ይሁዳ ብላ ጠራ​ችው። መው​ለ​ድ​ንም አቆ​መች።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ