የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 19

19
የሰ​ዶም ኀጢ​አት
1ሁለ​ቱም መላ​እ​ክት በመሸ ጊዜ ወደ ሰዶም ደረሱ፤ ሎጥም በሰ​ዶም ከተማ በር ተቀ​ምጦ ነበር። ሎጥም ባያ​ቸው ጊዜ ሊቀ​በ​ላ​ቸው ተነሣ፤ ፊቱ​ንም ወደ ምድር ደፍቶ ሰገ​ደ​ላ​ቸው፤ 2አላ​ቸ​ውም፥ “ጌቶች ሆይ፥ ወደ ባሪ​ያ​ችሁ ቤት ገብ​ታ​ችሁ እደሩ፤ እግ​ራ​ች​ሁ​ንም ታጠቡ፤ ነገም ማል​ዳ​ችሁ መን​ገ​ዳ​ች​ሁን ትሄ​ዳ​ላ​ችሁ።” እነ​ር​ሱም፥ “በአ​ደ​ባ​ባዩ እና​ድ​ራ​ለን እንጂ፥ አይ​ሆ​ንም” አሉት። 3እር​ሱም ግድ አላ​ቸው፤ ወደ እር​ሱም አቀኑ፤ ወደ ቤቱም ገቡ፤ ቂጣ​ንም አስ​ጋ​ገ​ረ​ላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም በሉ። 4ገና ሳይ​ተ​ኙም የዚ​ያች ከተማ ሰዎች፥ ታና​ሹም፥ ታላ​ቁም ቤቱን በአ​ን​ድ​ነት ከበ​ቡት። 5ሎጥ​ንም ጠር​ተው እን​ዲህ አሉት፥ “በሌ​ሊት ወደ አንተ የገ​ቡት ሰዎች ወዴት ናቸው? እና​ው​ቃ​ቸው ዘንድ ወደ እኛ አው​ጣ​ቸው።” 6ሎጥም ወደ እነ​ርሱ ወደ ደጅ ፊት ለፊት ወጣ፤ መዝ​ጊ​ያ​ው​ንም በስ​ተ​ኋ​ላው ዘጋው፤ 7እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ ለእ​ና​ንተ አግ​ባ​ባ​ችሁ አይ​ደ​ለም፤ በእ​ነ​ዚህ ላይ ክፉ አታ​ድ​ርጉ፤ 8እነሆ፥ ወን​ድን ያላ​ወቁ ሁለት ሴቶች ልጆች አሉኝ፤ እነ​ር​ሱን ላው​ጣ​ላ​ችሁ፤ እንደ ወደ​ዳ​ች​ሁም አድ​ር​ጉ​አ​ቸው፤ በእ​ነ​ዚህ ሰዎች ብቻ ምንም በደል አታ​ድ​ርጉ፤ እነ​ርሱ በቤቴ ጥላ ሥር ገብ​ተ​ዋ​ልና።” 9እነ​ር​ሱም፥ “ወዲያ ሂድ፤ ከእኛ ጋር ልት​ኖር መጣህ እንጂ ልት​ገ​ዛን አይ​ደ​ለም፤ አሁ​ንም ከእ​ነ​ርሱ ይልቅ አን​ተን እና​ሠ​ቃ​ይ​ሃ​ለን” አሉት። 10እጅ​ግም ተጋ​ፉት፤ የደ​ጁ​ንም መዝ​ጊያ ለመ​ስ​በር ቀረቡ። እነ​ዚ​ያም ሰዎች እጃ​ቸ​ውን ዘር​ግ​ተው ሎጥን ወደ እነ​ርሱ ዘንድ ወደ ቤት ስበው አገ​ቡት፤ መዝ​ጊ​ያ​ው​ንም ዘጉት። 11በቤቱ ደጃፍ የነ​በ​ሩ​ት​ንም ሰዎች ከታ​ና​ሻ​ቸው ጀምሮ እስክ ታላ​ቃ​ቸው ድረስ ዐይ​ና​ቸ​ውን አሳ​ወ​ሩ​አ​ቸው፤ ደጃ​ፉ​ንም ሲፈ​ልጉ ደከሙ፤ አጡ​ትም።#“አጡ​ትም” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. እና በዕብ. የለም።
ሎጥ ሰዶ​ምን ትቶ እንደ ወጣ
12እነ​ዚ​ያም መላ​እ​ክት#በግ​እዙ “እነ​ዚያ መላ​እ​ክት” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊቃ. እና በዕብ. “ሁለቱ ሰዎች” ይላል። ሎጥን አሉት፥ “ከዚህ ሌላ ማን አለህ? አማ​ችም ቢሆን፥ ወንድ ልጅም ቢሆን፥ ሴት ልጅም ብት​ሆን፥ በዚህ ከተማ የም​ታ​ው​ቀው ወዳጅ ቢኖ​ርህ ያለ​ህን ሁሉ ከዚህ ስፍራ አስ​ወ​ጣ​ቸው፤ 13እኛ ይህ​ችን ስፍራ እና​ጠ​ፋ​ታ​ለ​ንና፥ ጩኸ​ታ​ቸው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ትልቅ ሆኖ​አ​ልና፤ እና​ጠ​ፋ​ትም ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልኮ​ናል።” 14ሎጥም ወጣ፤ ልጆ​ቹን ለሚ​ያ​ገ​ቡት ለአ​ማ​ቾ​ቹም አላ​ቸው፥ “ተነሡ፤ ከዚች ስፍራ ውጡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህ​ችን ከተማ ያጠ​ፋ​ታ​ልና።” ለአ​ማ​ቾቹ ግን የሚ​ያ​ፌ​ዝ​ባ​ቸው መሰ​ላ​ቸው። 15ጎህም በቀ​ደደ ጊዜ መላ​እ​ክት ሎጥን፥ “ተነሣ፤ ሚስ​ት​ህ​ንና ከዚህ ያሉ​ትን ሁለ​ቱን ሴቶች ልጆ​ች​ህን ውሰድ፤ አን​ተም በከ​ተ​ማ​ዪቱ ሰዎች ኀጢ​አት እን​ዳ​ት​ጠፋ” እያሉ ያስ​ቸ​ኩ​ሉት ነበር። 16እር​ሱም በዘ​ገየ ጊዜ እነ​ዚያ መላ​እ​ክት የእ​ር​ሱን እጅ፥ የሚ​ስ​ቱ​ንም እጅ፥ የሁ​ለ​ቱን ሴቶች ልጆ​ቹ​ንም እጅ ይዘው አወ​ጡ​አ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራር​ቶ​ላ​ቸ​ዋ​ልና። 17ወደ ሜዳም በወጡ ጊዜ እን​ዲህ አሉት፥ “ራስ​ህን አድን፤ ወደ ኋላም አት​መ​ል​ከት፤ አን​ተ​ንም መከራ እን​ዳ​ታ​ገ​ኝህ በዚች ሀገር በዳ​ር​ቻ​ዋና በተ​ራ​ራዋ አት​ቁም።”#በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. “በተ​ራ​ራው ራስ​ህን አድን” ይላል። 18ሎጥም አላ​ቸው፥ “ጌቶች ሆይ፥ በጀ በሉኝ፤ 19እነሆ፥ ባሪ​ያህ በፊ​ትህ ምሕ​ረ​ትን አግ​ኝቼ እን​ደ​ሆነ፥ ሰው​ነ​ቴ​ንም ታድ​ናት ዘንድ፥ ቸር​ነ​ት​ህን አብ​ዝ​ተ​ህ​ልኝ እንደ ሆነ፥ መከራ አግ​ኝ​ቶኝ እን​ዳ​ል​ጠፋ ወደ ተራራ ሸሽቼ ራሴን ማዳን አል​ች​ልም። 20እነሆ፥ ይህች ከተማ ወደ እር​ስዋ ሸሽቶ ለማ​ም​ለጥ ቅርብ ናት፤ እር​ስ​ዋም ትንሽ ናት፤ ነፍ​ሴን ለማ​ዳን ወደ እር​ስዋ ሸሽቼ ራሴን ላድን፤ ሰው​ነ​ቴም ከዳ​ነች ትንሽ አይ​ደ​ለ​ችም፤”#ዕብ. “እር​ስዋ ትንሽ ከተማ አይ​ደ​ለ​ች​ምን?” ይላል። 21እር​ሱም አለው፥ “ስለ እር​ስዋ የነ​ገ​ር​ኸ​ኝን ያችን ከተማ እን​ዳ​ላ​ጠ​ፋት እነሆ፥ እን​ዳ​ል​ኸው ልመ​ና​ህን ተቀ​ብ​ዬ​ሃ​ለሁ፤ 22እን​ግ​ዲህ ፍጠ​ንና በዚያ ራስ​ህን አድን፤ ወደ​ዚያ እስ​ክ​ት​ደ​ርስ ድረስ ምንም አደ​ርግ ዘንድ አል​ች​ል​ምና።” ስለ​ዚ​ህም የዚ​ያች ከተማ ስም ሴጎር ተባለ።
የሰ​ዶ​ምና የገ​ሞራ መጥ​ፋት
23ፀሐይ በም​ድር ላይ ወጣች፤ ሎጥም ወደ ሴጎር ገባ። 24እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሰ​ዶ​ምና በገ​ሞራ ላይ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ከሰ​ማይ እሳ​ትና ዲን አዘ​ነበ፤ 25እነ​ዚ​ያ​ንም ከተ​ሞች፥ በዙ​ሪ​ያ​ቸው ያለ​ው​ንም ሁሉ፥ በከ​ተ​ሞ​ችም የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሁሉ፥ የም​ድ​ሩ​ንም ቡቃያ ሁሉ ገለ​በጠ። 26የሎ​ጥም ሚስት ወደ ኋላዋ ተመ​ለ​ከ​ተች፤ የጨው ሐው​ል​ትም ሆነች። 27አብ​ር​ሃ​ምም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቆሞ ወደ ነበ​ረ​በት ስፍራ ለመ​ሄድ ማልዶ ተነሣ፤ 28ወደ ሰዶ​ምና ገሞራ፥ ወደ አው​ራ​ጃ​ዎ​ች​ዋም ሁሉ ተመ​ለ​ከተ፤ እነ​ሆም፥ ነበ​ል​ባል ከም​ድር እንደ ምድጃ ጢስ ሲወጣ አየ።
29እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እነ​ዚ​ያን ከተ​ሞ​ችና ሎጥ የሚ​ኖ​ር​ባ​ቸ​ውን አው​ራ​ጃ​ዎ​ች​ዋን ሁሉ ባጠፋ ጊዜ አብ​ር​ሃ​ምን ዐሰ​በው፤ ሎጥ​ንም ከጥ​ፋት መካ​ከል አወ​ጣው።
የሞ​አ​ባ​ው​ያ​ንና የአ​ሞ​ና​ው​ያን መወ​ለድ
30ሎጥም ከሴ​ጎር ወጣ፤ ከሁ​ለ​ቱም ሴቶች ልጆቹ ጋር በተ​ራራ ተቀ​መጠ፤ በሴ​ጎር መቀ​መ​ጥን ፈር​ቶ​አ​ልና እር​ሱና ሁለቱ ሴቶች ልጆቹ በዋሻ ተቀ​መጡ። 31ታላ​ቂ​ቱም ታና​ሺ​ቱን አለ​ቻት፥ “አባ​ታ​ችን ሽማ​ግሌ ነው፤ በም​ድ​ርም ሁሉ እን​ዳ​ለው ልማድ ሊገ​ና​ኘን የሚ​ችል ሰው በም​ድር ላይ የለም። 32ነዪ፥ አባ​ታ​ች​ንን ወይን እና​ጠ​ጣ​ውና ከእ​ርሱ ጋር እን​ተኛ፤ ከአ​ባ​ታ​ች​ንም ዘር እና​ስ​ቀር።” 33በዚ​ያ​ችም ሌሊት አባ​ታ​ቸ​ውን ወይን አጠ​ጡት፤ ታላ​ቂ​ቱም ገባች፤ በዚ​ያ​ችም ሌሊት ከአ​ባቷ ጋር ተኛች፤ እር​ሱም ስት​ተ​ኛም፥ ስት​ነ​ሣም አላ​ወ​ቀም። 34በነ​ጋ​ውም ታላ​ቂቱ ታና​ሺ​ቱን አለ​ቻት፥ “እነሆ፥ ትና​ንት ከአ​ባቴ ጋር ተኛሁ፤ ዛሬ ሌሊት ደግሞ ወይን እና​ጠ​ጣው፤ አን​ቺም ግቢና ከእ​ርሱ ጋር ተኚ፤ ከአ​ባ​ታ​ች​ንም ዘር እና​ስ​ቀር።” 35አባ​ታ​ቸ​ው​ንም በዚ​ያች ሌሊት ደግሞ ወይን አጠ​ጡት፤ ታና​ሺ​ቱም ገብታ ከአ​ባቷ ጋር ተኛች፤ እር​ሱም ስት​ተ​ኛም ስት​ነ​ሣም አላ​ወ​ቀም። 36የሎ​ጥም ሁለቱ ሴቶች ልጆች ከአ​ባ​ታ​ቸው ፀነሱ። 37ታላ​ቂ​ቱም ወንድ ልጅ ወለ​ደች፤ ስሙ​ንም ሞዓብ ብላ ጠራ​ችው፤ ይህም ከአ​ባቴ የወ​ለ​ድ​ሁት ማለት ነው። እር​ሱም እስከ ዛሬ የሞ​ዓ​ባ​ው​ያን አባት ነው። 38ታና​ሺ​ቱም ደግሞ ወንድ ልጅ ወለ​ደች፤ ስሙ​ንም የወ​ገኔ ልጅ ስትል አሞን#ግሪክ ሰባ. ሊ. “አማን” ይላል። ብላ ጠራ​ችው፤ እር​ሱም እስከ ዛሬ የአ​ሞ​ና​ው​ያን አባት ነው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ