የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 16

16
አጋ​ርና ይስ​ማ​ኤል
1የአ​ብ​ራም ሚስት ሦራ ግን ልጅ አል​ወ​ለ​ደ​ች​ለ​ትም ነበር፤ ስምዋ አጋር የተ​ባለ ግብ​ፃ​ዊት አገ​ል​ጋ​ይም ነበ​ረ​ቻት። 2ሦራም አብ​ራ​ምን፥ “እነሆ፥ እን​ዳ​ል​ወ​ልድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘጋኝ፤ ከእ​ር​ስዋ ትወ​ልድ ዘንድ ወደ አገ​ል​ጋዬ ሂድ” አለ​ችው። አብ​ራ​ምም የሚ​ስ​ቱን የሦ​ራን ቃል ሰማ። 3አብ​ራ​ምም በከ​ነ​ዓን ምድር ዐሥር ዓመት ከተ​ቀ​መጠ በኋላ፥ የአ​ብ​ራም ሚስት ሦራ ግብ​ፃ​ዊት አገ​ል​ጋ​ይ​ዋን አጋ​ርን ወስዳ ለአ​ብ​ራም ሚስት ትሆ​ነው ዘንድ ሰጠ​ችው። 4አብ​ራ​ምም ወደ አጋር ገባ፤ ፀነ​ሰ​ችም፤ እንደ ፀነ​ሰ​ችም ባየች ጊዜ እመ​ቤ​ቷን ማክ​በ​ር​ዋን ተወች። 5ሦራም አብ​ራ​ምን፥ “ከአ​ንተ የተ​ነሣ እገ​ፋ​ለሁ፤ እኔ አገ​ል​ጋ​ዬን በብ​ብ​ትህ ሰጠ​ሁህ፤ እንደ ፀነ​ሰ​ችም ባየች ጊዜ እኔን ማክ​በ​ርን ተወች፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል ይፍ​ረድ” አለ​ችው። 6አብ​ራ​ምም ሚስ​ቱን ሦራን፥ “እነሆ፥ አገ​ል​ጋ​ይሽ በእ​ጅሽ ናት፤ እንደ ወደ​ድሽ አድ​ር​ጊ​ባት” አላት። ሦራም አጋ​ርን አሠ​ቃ​የ​ቻት፤ ከእ​ር​ስ​ዋም ኰበ​ለ​ለች።
7የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ክም በውኃ ምንጭ አጠ​ገብ በሱር በረሃ በመ​ን​ገድ አገ​ኛት። 8የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ፥ “የሦራ አገ​ል​ጋይ አጋር ሆይ፥ ከወ​ዴት መጣሽ? ወዴ​ትስ ትሄ​ጂ​ያ​ለሽ?” አላት። እር​ስ​ዋም፥ “እኔ ከእ​መ​ቤቴ ከሦራ ፊት እኰ​በ​ል​ላ​ለሁ” አለች። 9የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ክም፥ “ወደ እመ​ቤ​ትሽ ተመ​ለሺ፤ ከእ​ጅ​ዋም በታች ራስ​ሽን ዝቅ አድ​ርጊ” አላት። 10እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም#ግሪክ ሰባ. ሊ. እና ዕብ. “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ” ይላል። “ከብ​ዛቱ የተ​ነሣ እስ​ከ​ማ​ይ​ቈ​ጠር ድረስ ዘር​ሽን እጅግ አበ​ዛ​ለሁ፥” አላት። 11የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ክም አላት፥ “እነሆ፥ አንቺ ፀን​ሰ​ሻል፤ ወንድ ልጅ​ንም ትወ​ል​ጃ​ለሽ፤ ስሙ​ንም ይስ​ማ​ኤል ብለሽ ትጠ​ሪ​ዋ​ለሽ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥቃ​ይ​ሽን ሰም​ቶ​አ​ልና። 12እር​ሱም የበ​ረሃ ሰው ይሆ​ናል፤#ዕብ. “እርሱ የም​ድረ በዳ አህ​ያን የሚ​መ​ስል ሰው ይሆ​ናል” ይላል። እጁ በሁሉ ላይ ይሆ​ናል፤ የሁ​ሉም እጅ ደግሞ በእ​ርሱ ላይ ይሆ​ናል፤ እር​ሱም በወ​ን​ድ​ሞቹ ሁሉ ፊት ይኖ​ራል።” 13አጋ​ርም ይና​ገ​ራት የነ​በ​ረ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም#ዕብ. “ኤል​ሮኢ ብላ” ይላል። ጠራች፤ “አቤቱ የራ​ራ​ህ​ልኝ አንተ ነህ፤ የተ​ገ​ለ​ጠ​ል​ኝን በፊቴ አይ​ች​ዋ​ለ​ሁና።” 14ስለ​ዚ​ህም የዚ​ያን ጕድ​ጓድ ስም “በፊቴ የተ​ገ​ለ​ጠ​ልኝ የእ​ርሱ ጕድ​ጓድ” ብላ ጠራ​ችው፤ እር​ሱም በቃ​ዴ​ስና በባ​ሬድ መካ​ከል ነው። አጋ​ርም ተመ​ለ​ሰች።#“አጋ​ርም ተመ​ለ​ሰች” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. እና በዕብ. የለም።
15ከዚ​ህም በኋላ አጋር ለአ​ብ​ራም ወንድ ልጅን ወለ​ደ​ች​ለት፤ አብ​ራ​ምም አጋር የወ​ለ​ደ​ች​ለ​ትን የሕ​ፃ​ኑን ስም ይስ​ማ​ኤል ብሎ ጠራው። 16አጋር ይስ​ማ​ኤ​ልን በወ​ለ​ደ​ች​ለት ጊዜ አብ​ራም የሰ​ማ​ንያ አም​ስት#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሰማ​ንያ ስድ​ስት” ይላል። ዓመት ሰው ነበረ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ