መጽ​ሐፈ ዕዝራ 1

1
አይ​ሁድ ወደ ሀገ​ራ​ቸው እን​ዲ​መ​ለሱ ቂሮስ እንደ ፈቀ​ደ​ላ​ቸው
1በኤ​ር​ም​ያስ አፍ የተ​ና​ገ​ረው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ከተ​ፈ​ጸመ በኋላ በፋ​ርስ ንጉሥ በቂ​ሮስ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ዓመት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የፋ​ር​ስን ንጉሥ የቂ​ሮ​ስን መን​ፈስ አስ​ነሣ፤ እር​ሱም በመ​ን​ግ​ሥቱ ሁሉ አዋጅ አስ​ነ​ገረ፤ ደግ​ሞም በጽ​ሕ​ፈት እን​ዲህ አለ፦ 2“የፋ​ርስ ንጉሥ ቂሮስ እን​ዲህ ይላል፦ የሰ​ማይ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ድ​ርን መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ ሰጥ​ቶ​ኛል፤ በይ​ሁ​ዳም ባለ​ችው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቤትን እሠ​ራ​ለት ዘንድ እን​ዳ​ስብ አደ​ረ​ገኝ፤ 3ከሕ​ዝቡ ሁሉ በእ​ና​ንተ ዘንድ ማንም ቢሆን አም​ላኩ ከእ​ርሱ ጋር ይሁን፤ እር​ሱም በይ​ሁዳ ወዳ​ለ​ችው ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ይውጣ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ለሚ​ኖ​ረው አም​ላክ፥ ለእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤትን ይሥራ፤ 4በስ​ደት በሚ​ኖ​ር​ባ​ቸው ከተ​ሞች ሁሉ ለቀ​ረው ሰው ሁሉ የሀ​ገሩ ሰዎች በብ​ርና በወ​ርቅ፥ በዕ​ቃም፥ በእ​ን​ስ​ሳም ይር​ዱት፤ ይህም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላለው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በፈ​ቃ​ዳ​ቸው ከሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት ሌላ ይሁን።”
5የይ​ሁ​ዳና የብ​ን​ያም የአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆ​ችም፥ ካህ​ና​ቱም፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑም፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያለ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ለመ​ሥ​ራት ይወጡ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈ​ሳ​ቸ​ውን ያነ​ሣ​ሣው ሁሉ ተነሡ። 6በዙ​ሪ​ያ​ቸ​ውም ያሉ ሁሉ በፈ​ቃ​ዳ​ቸው ካቀ​ረ​ቡት ሁሉ ሌላ በብር ዕቃና በወ​ርቅ፥ በገ​ን​ዘ​ቦ​ችና በእ​ን​ስ​ሶች፥ በሌ​ላም ስጦታ ይረ​ዷ​ቸው ነበር። 7ንጉሡ ቂሮ​ስም ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወስዶ በአ​ም​ላኩ#ዕብ. “በአ​ማ​ል​ክቱ” ይላል። ቤት ያኖ​ራ​ቸ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤተ መቅ​ደስ ዕቃ​ዎች አወጣ። 8የፋ​ርስ ንጉሥ ቂሮ​ስም የመ​ዝ​ገብ ሐላፊ በነ​በ​ረው በሚ​ት​ሪ​ዳጡ እጅ አወ​ጣ​ቸው፤ ለይ​ሁ​ዳም መስ​ፍን ለሲ​ሳ​ብ​ሳር ቈጠ​ራ​ቸው። 9ቍጥ​ራ​ቸ​ውም ይህ ነው፤ ሠላሳ የወ​ርቅ ሳሕ​ኖች፥ አንድ ሺህም የብር ሳሕ​ኖች፥ ሃያ ዘጠ​ኝም ቢላ​ዋ​ዎች፥ ሠላሳ የወ​ርቅ ዳካ​ዎች፥ 10አራት መቶ ዐሥ​ርም ሌላ ዓይ​ነት የብር ዳካ​ዎች፥ አንድ ሺህም ሌላ ዕቃ ነበረ። 11የወ​ር​ቁና የብሩ ዕቃ​ዎች ሁሉ አም​ስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ፤ እነ​ዚ​ህ​ንም ሁሉ ሲሳ​ብ​ሳር ከባ​ቢ​ሎን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ከተ​መ​ለሱ ምር​ኮ​ኞች ጋር ወሰደ።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ