የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ሕዝ​ቅ​ኤል 36:13-38

ትን​ቢተ ሕዝ​ቅ​ኤል 36:13-38 አማ2000

ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነ​ርሱ፦ ሰው በላ​ተኛ ነሽ፤ በሕ​ዝ​ብ​ሽም መካ​ከል ልጆ​ች​ሽን አጥ​ፍ​ተ​ሻል ብለ​ዋ​ች​ኋ​ልና፤ ስለ​ዚህ ዳግ​መኛ ሰው በላ​ተኛ አት​ሆ​ኝም፤ ዳግ​መ​ኛም ሕዝ​ብ​ሽን ልጅ አልባ አታ​ደ​ር​ጊም፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። ዳግ​መ​ኛም የአ​ሕ​ዛ​ብን ስድብ አላ​ሰ​ማ​ብ​ሽም፤ ዳግ​መ​ኛም የአ​ሕ​ዛ​ብን ውር​ደት አት​ሸ​ከ​ሚም፤ ዳግ​መ​ኛም ሕዝ​ብ​ሽን አታ​ሰ​ና​ክ​ዪም፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።” የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት በም​ድ​ራ​ቸው በተ​ቀ​መጡ ጊዜ በመ​ን​ገ​ዳ​ቸ​ውና በጣ​ዖ​ታ​ቸው አረ​ከ​ሱ​አት፤ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውም በፊቴ እንደ አደፍ ርኵ​ሰት ነበረ። በም​ድር ላይ ስለ አፈ​ሰ​ሱት ደም፥ በጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ስለ አረ​ከ​ሱ​አት መዓ​ቴን አፈ​ሰ​ስ​ሁ​ባ​ቸው፤ ወደ አሕ​ዛ​ብም በተ​ን​ኋ​ቸው፤ ወደ ሀገ​ሮ​ችም ዘራ​ኋ​ቸው፤ እንደ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውና እንደ በደ​ላ​ቸ​ውም መጠን ፈረ​ድ​ሁ​ባ​ቸው። ወደ ገቡ​ባ​ቸ​ውም ወደ አሕ​ዛብ በመጡ ጊዜ፥ ሰዎች እነ​ር​ሱን፦ ከም​ድ​ራ​ቸው የወጡ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝብ እነ​ዚህ ናቸው ሲሉ​አ​ቸው ቅዱስ ስሜን አረ​ከሱ። እኔ ግን የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት በመ​ጡ​ባ​ቸው በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ስለ አረ​ከ​ሱት ስለ ቅዱስ ስሜ ስል ራራ​ሁ​ላ​ቸው። “ስለ​ዚህ ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት እን​ዲህ በላ​ቸው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! በገ​ባ​ች​ሁ​ባ​ቸው በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ስላ​ረ​ከ​ሳ​ች​ሁት ስለ ቅዱስ ስሜ ነው እንጂ ስለ እና​ንተ የም​ሠራ አይ​ደ​ለ​ሁም። በአ​ሕ​ዛ​ብም ዘንድ የረ​ከ​ሰ​ውን፥ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ያረ​ከ​ሳ​ች​ሁ​ትን ገናና ስሜን እቀ​ድ​ሰ​ዋ​ለሁ፤ በዐ​ይ​ና​ቸ​ውም ዘንድ በተ​ቀ​ደ​ስ​ሁ​ባ​ችሁ ጊዜ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ አሕ​ዛብ ያው​ቃሉ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። ከአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል አወ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከየ​ሀ​ገ​ሩም ሁሉ እሰ​በ​ስ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ ወደ ገዛ ምድ​ራ​ች​ሁም እመ​ል​ሳ​ች​ኋ​ለሁ። ጥሩ ውኃ​ንም እረ​ጭ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም ከር​ኵ​ሰ​ታ​ችሁ ሁሉ ትነ​ጻ​ላ​ችሁ፤ ከጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ሁሉ አነ​ጻ​ች​ኋ​ለሁ። አዲስ ልብ​ንም እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ አዲስ መን​ፈ​ስ​ንም በው​ስ​ጣ​ችሁ አኖ​ራ​ለሁ፤ የድ​ን​ጋ​ዩ​ንም ልብ ከሥ​ጋ​ችሁ አወ​ጣ​ለሁ፤ የሥ​ጋ​ንም ልብ እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ። መን​ፈ​ሴ​ንም በው​ስ​ጣ​ችሁ አኖ​ራ​ለሁ፤ በት​እ​ዛ​ዜም እን​ድ​ት​ሄዱ አደ​ር​ጋ​ች​ኋ​ለሁ፤ ፍር​ዴ​ንም ትጠ​ብ​ቃ​ላ​ችሁ ታደ​ር​ጉ​ት​ማ​ላ​ችሁ። ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም በሰ​ጠ​ኋት ምድር ትኖ​ራ​ላ​ችሁ፤ ሕዝ​ብም ትሆ​ኑ​ኛ​ላ​ችሁ፤ እኔም አም​ላክ እሆ​ና​ች​ኋ​ለሁ። ከር​ኵ​ሰ​ታ​ች​ሁም ሁሉ አድ​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ እህ​ል​ንም እጠ​ራ​ዋ​ለሁ፤ አበ​ዛ​ው​ማ​ለሁ፤ ራብ​ንም አላ​መ​ጣ​ባ​ች​ሁም። ደግ​ሞም የራ​ብን ስድብ ከአ​ሕ​ዛብ ዘንድ እን​ዳ​ት​ሸ​ከሙ የዛ​ፍን ፍሬና የእ​ር​ሻ​ውን መከር አበ​ዛ​ለሁ። ክፉ​ውን መን​ገ​ዳ​ች​ሁ​ንና መል​ካም ያይ​ደ​ለ​ውን ሥራ​ች​ሁ​ንም ታስ​ባ​ላ​ችሁ፤ ስለ በደ​ላ​ች​ሁና ስለ ርኵ​ሰ​ታ​ች​ሁም ራሳ​ች​ሁን ትጸ​የ​ፋ​ላ​ችሁ። ይህን የሠ​ራሁ ስለ እና​ንተ እን​ዳ​ይ​ደለ በእ​ና​ንተ ዘንድ የታ​ወቀ ይሁን፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! ስለ መን​ገ​ዳ​ችሁ እፈ​ሩና ተዋ​ረዱ። “ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ከኀ​ጢ​አ​ታ​ችሁ ሁሉ በአ​ነ​ጻ​ኋ​ችሁ ጊዜ በከ​ተ​ሞች ሰዎ​ችን አኖ​ራ​ለሁ፤ ባድ​ማ​ዎ​ቹም ስፍ​ራ​ዎች ይሠ​ራሉ። ባድማ የነ​በ​ረች፥ በመ​ን​ገ​ደ​ኛም ሁሉ ዐይን ዘንድ ባድማ የነ​በ​ረች ምድር ትታ​ረ​ሳ​ለች። ሰዎ​ችም ባድማ የነ​በ​ረች ይህች ምድር እንደ ዔድን ገነት ሆና​ለች፤ የፈ​ረ​ሱት፥ ባድማ የሆ​ኑት፥ የጠ​ፉ​ትም ከተ​ሞች ተመ​ሽ​ገ​ዋል፤ ሰውም የሚ​ኖ​ር​ባ​ቸው ሆነ​ዋል ይላሉ። በዙ​ሪ​ያ​ች​ሁም የቀ​ሩት አሕ​ዛብ፥ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የፈ​ረ​ሱ​ትን ስፍ​ራ​ዎች እንደ ሠራሁ፥ ውድማ የሆ​ነ​ው​ንም እንደ ተከ​ልሁ ያው​ቃሉ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፥ እኔም አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ። “ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ስለ​ዚህ ደግሞ አደ​ር​ግ​ላ​ቸው ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ይሹ​ኛል፤ ሰው​ንም እንደ መንጋ አበ​ዛ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ። እንደ ተቀ​ደሱ በጎች፥ በበ​ዓ​ላ​ቶ​ችዋ ቀን እን​ደ​ሚ​ሆኑ እንደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በጎች እን​ዲሁ የፈ​ረ​ሱት ከተ​ሞች በሰ​ዎች መንጋ ይሞ​ላሉ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።”