የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ሕዝ​ቅ​ኤል 2

2
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቅ​ኤ​ልን ለነ​ቢ​ይ​ነት እንደ ጠራው
1እር​ሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! በእ​ግ​ርህ ቁም፤ እኔም እና​ገ​ር​ሃ​ለሁ” አለኝ። 2በተ​ና​ገ​ረ​ኝም ጊዜ መን​ፈስ በእኔ ላይ መጣ፤ አነ​ሣ​ኝም፤ በእ​ግ​ሬም አቆ​መኝ፤ የሚ​ና​ገ​ረ​ኝ​ንም ሰማሁ። 3እር​ሱም እን​ዲህ አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! እኔን ወደ አስ​መ​ረ​ሩኝ ወደ እስ​ራ​ኤል ቤት እል​ክ​ሃ​ለሁ። እነ​ር​ሱና አባ​ቶ​ቻ​ቸው እስከ ዛሬ ድረስ ዐመ​ፁ​ብኝ። 4እነ​ርሱ ፊታ​ቸው የከፋ፥ ልባ​ቸው የደ​ነ​ደነ ልጆች ናቸው። እኔ ወደ እነ​ርሱ እል​ክ​ሃ​ለሁ፤ አን​ተም፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል በላ​ቸው።
5“እነ​ርሱ ዐመ​ፀኛ ቤት ናቸ​ውና ቢሰሙ ወይም ቢፈሩ አንተ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ነቢይ እንደ ሆንህ ያው​ቃሉ። 6አንተ የሰው ልጅ ሆይ! ኩር​ን​ች​ትና እሾህ ከአ​ንተ ጋር ቢኖ​ሩም፥#“እሾ​ህና ኩር​ን​ች​ትም ከአ​ንተ ጋር ቢሆኑ” የሚ​ለው በዕብ. ብቻ። አን​ተም በጊ​ን​ጦች መካ​ከል ብት​ቀ​መጥ፥ አት​ፍ​ራ​ቸው፤ ቃላ​ቸ​ው​ንም አት​ፍራ፤ አንተ ቃላ​ቸ​ውን አት​ፍራ፤ ከፊ​ታ​ቸ​ውም የተ​ነሣ አት​ደ​ን​ግጥ፤ እነ​ርሱ ዐመ​ፀኛ ቤት ናቸ​ውና። 7እነ​ርሱ ዐመ​ፀኛ ቤት ስለ​ሆኑ ቢሰሙ ወይም ቢደ​ነ​ግጡ ቃሌን ትነ​ግ​ራ​ቸ​ዋ​ለህ።
8“አንተ የሰው ልጅ ሆይ! የም​ነ​ግ​ር​ህን ስማ፤ እን​ደ​እ​ዚያ ዐመ​ፀኛ ቤት ዐመ​ፀኛ አት​ሁን፤ አፍ​ህን ክፈት፤ የም​ሰ​ጥ​ህ​ንም ብላ።” 9በአ​የ​ሁም ጊዜ፥ እነሆ እጅ ወደ እኔ ተዘ​ር​ግታ ነበር፤ እነ​ሆም የመ​ጽ​ሐፍ ጥቅ​ልል ነበ​ረ​ባት። 10በፊ​ቴም ዘረ​ጋው፤ በው​ስ​ጥና በው​ጭም ተጽ​ፎ​በት ነበረ፤ ጽሑ​ፉም “ልቅ​ሶና ኀዘን፥ ዋይ​ታም” ይል ነበር።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ