የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፀ​አት 6:2-13

ኦሪት ዘፀ​አት 6:2-13 አማ2000

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን ተና​ገ​ረው አለ​ውም፥ “እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ። ለአ​ብ​ር​ሃ​ምም፥ ለይ​ስ​ሐ​ቅም፥ ለያ​ዕ​ቆ​ብም ሁሉን እን​ደ​ሚ​ችል አም​ላክ ተገ​ለ​ጥሁ፤ ነገር ግን ስሜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​ታ​ወ​ቀ​ላ​ቸ​ውም ነበር። የነ​በ​ሩ​ባ​ት​ንም የከ​ነ​ዓ​ንን ምድር እሰ​ጣ​ቸው ዘንድ ከእ​ነ​ርሱ ጋር ቃል ኪዳ​ኔን አቆ​ምሁ። ደግሞ እኔ ግብ​ፃ​ው​ያን የገ​ዙ​አ​ቸ​ውን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ልቅሶ ሰማሁ፤ ቃል ኪዳ​ኔ​ንም አሰ​ብሁ።” ስለ​ዚ​ህም ፈጥ​ነህ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ በላ​ቸው፥ “እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ ከግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንም ተገ​ዥ​ነት አወ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከባ​ር​ነ​ታ​ቸ​ውም አድ​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ በተ​ዘ​ረጋ ክንድ፤ በታ​ላቅ ፍር​ድም እታ​ደ​ጋ​ች​ኋ​ለሁ፤ ለእ​ኔም ሕዝብ እን​ድ​ት​ሆኑ እቀ​በ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ አም​ላ​ክም እሆ​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔም ከግ​ብ​ፃ​ው​ያን ባር​ነት ያወ​ጣ​ኋ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ። ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐቅ፥ ለያ​ዕ​ቆ​ብም እሰ​ጣት ዘንድ እጄን ወደ ዘረ​ጋ​ሁ​ባት ምድር አገ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ እር​ስ​ዋ​ንም ርስት አድ​ርጌ እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ።” ሙሴም ይህን ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ተና​ገረ፤ እነ​ርሱ ግን ከሰ​ው​ነ​ታ​ቸው መጨ​ነቅ፥ ከሥ​ራ​ቸ​ውም ክብ​ደት የተ​ነሣ ቃሉን አል​ሰ​ሙ​ትም። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦ “ግባ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከሀ​ገሩ ይለ​ቅቅ ዘንድ ለግ​ብፅ ንጉሥ ለፈ​ር​ዖን ንገ​ረው።” ሙሴም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት፥ “እነሆ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አል​ሰ​ሙ​ኝም፤ እን​ዴ​ትስ ፈር​ዖን ይሰ​ማ​ኛል? እኔም አን​ደ​በተ ርቱዕ አይ​ደ​ለ​ሁም” ብሎ ተና​ገረ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን ተና​ገ​ራ​ቸው፤ የግ​ብፅ ንጉሥ ፈር​ዖ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከግ​ብፅ እን​ዲ​ያ​ወ​ጣ​ቸው ይነ​ግ​ሩት ዘንድ አዘ​ዛ​ቸው።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}