የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፀ​አት 40

40
ድን​ኳኑ ተተ​ክሎ ለአ​ገ​ል​ግ​ሎት መዋሉ
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ሲል ተና​ገ​ረው፦ 2“በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር በፊ​ተ​ኛው ቀን የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ትተ​ክ​ላ​ለህ። 3በእ​ር​ሱም ውስጥ የም​ስ​ክ​ሩን ታቦት ታኖ​ራ​ለህ፤ ታቦ​ቱ​ንም በመ​ጋ​ረጃ ትጋ​ር​ዳ​ለህ። 4ገበ​ታ​ው​ንም ታገ​ባ​ለህ፤ በሥ​ር​ዐ​ቱም ታሰ​ና​ዳ​ዋ​ለህ፤ መቅ​ረ​ዙ​ንም አግ​ብ​ተህ ቀን​ዲ​ሎ​ቹን ትለ​ኵ​ሳ​ለህ። 5የወ​ር​ቁ​ንም ማዕ​ጠ​ንት በም​ስ​ክሩ ታቦት ፊት ታኖ​ራ​ለህ፤ በድ​ን​ኳ​ኑም ደጃፍ ፊት መጋ​ረ​ጃ​ውን ትጋ​ር​ዳ​ለህ። 6ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነ​ው​ንም መሠ​ዊያ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጅ ፊት ታኖ​ረ​ዋ​ለህ። 7የመ​ታ​ጠ​ቢ​ያ​ውን ሰንም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳ​ንና በመ​ሠ​ዊ​ያው መካ​ከል ታኖ​ረ​ዋ​ለህ፤ በው​ስ​ጡም ውኃ ትጨ​ም​ር​በ​ታ​ለህ። 8በዙ​ሪ​ያ​ውም አደ​ባ​ባ​ዩን ትሠ​ራ​ለህ፤ የአ​ደ​ባ​ባ​ዩ​ንም ደጃፍ መጋ​ረጃ ትዘ​ረ​ጋ​ለህ።#ምዕ. 40 ቍ. 7 እና 8 በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። 9የቅ​ብ​ዐ​ቱ​ንም ዘይት ወስ​ደህ ድን​ኳ​ኑን፥ በው​ስ​ጥ​ዋም ያለ​ውን ሁሉ ትቀ​ባ​ለህ፤ እር​ስ​ዋ​ንም ዕቃ​ዋ​ንም ሁሉ ትቀ​ድ​ሳ​ለህ፤ ቅድ​ስ​ትም ትሆ​ና​ለች። 10ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትም የሚ​ሆ​ነ​ውን መሠ​ዊያ፥ ዕቃ​ው​ንም ሁሉ ትቀ​ባ​ዋ​ለህ፤ መሠ​ዊ​ያ​ው​ንም ትቀ​ድ​ሳ​ለህ፤ መሠ​ዊ​ያ​ውም ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ይሆ​ናል። 11የመ​ታ​ጠ​ቢ​ያ​ውን ሰንና መቀ​መ​ጫ​ው​ንም ቀብ​ተህ ትቀ​ድ​ሳ​ለህ። 12አሮ​ን​ንና ልጆ​ቹ​ንም ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ አቅ​ር​በህ በውኃ ታጥ​ባ​ቸ​ዋ​ለህ። 13ለአ​ሮ​ንም የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ልብስ ታለ​ብ​ሰ​ዋ​ለህ፤ ትቀ​ባ​ዋ​ለህ፤ ትቀ​ድ​ሰ​ው​ማ​ለህ፤ ካህ​ንም ይሆ​ነ​ኛል። 14ልጆ​ቹ​ንም ታቀ​ር​ባ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ቀሚ​ሳ​ቸ​ው​ንም ታለ​ብ​ሳ​ቸ​ዋ​ለህ፤ 15አባ​ታ​ቸ​ውን እንደ ቀባህ ትቀ​ባ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ካህ​ና​ትም ይሆ​ኑ​ኛል። ይህም ለልጅ ልጃ​ቸው ለዘ​ለ​ዓ​ለም የክ​ህ​ነት ቅብ​ዐት ይሆ​ን​ላ​ቸ​ዋል።” 16ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ አደ​ረገ፤ እን​ዲ​ሁም አደ​ረገ።
17እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ከግ​ብፅ ምድር ከወጡ በኋላ በሁ​ለ​ተ​ኛው ዓመት በፊ​ተ​ኛው ወር በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ድን​ኳ​ንዋ ተተ​ከ​ለች። 18ሙሴም ድን​ኳ​ን​ዋን ተከለ፤ እግ​ሮ​ች​ዋ​ንም አኖረ፤ ሳን​ቆ​ች​ዋ​ንም አቆመ፤ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋ​ንም አደ​ረ​ገ​ባ​ቸው፤ ምሰ​ሶ​ዎ​ች​ዋ​ንም አቆመ። 19እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው መጋ​ረ​ጃ​ውን በድ​ን​ኳኑ ላይ ዘረ​ጋው፤ የድ​ን​ኳ​ኑ​ንም መደ​ረ​ቢያ በላዩ አደ​ረ​ገ​በት።
20ሙሴም ጽላ​ቱን ወስዶ በታ​ቦቱ ውስጥ አኖ​ረው፤ መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም በታ​ቦቱ ቀለ​በ​ቶች ውስጥ አደ​ረገ፤ የስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ው​ንም በታ​ቦቱ ላይ አኖ​ረው። 21ታቦ​ቷ​ንም ወደ ድን​ኳኑ አገባ፥ የሚ​ሸ​ፍ​ነ​ው​ንም መጋ​ረጃ አድ​ርጎ የም​ስ​ክ​ሩን ታቦት ሸፈነ።
22እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ገበ​ታ​ውን በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ፥ ከመ​ጋ​ረ​ጃው ውጭ በድ​ን​ኳኑ በመ​ስዕ በኩል አኖ​ረው፤ 23ኅብ​ስተ ገጹ​ንም በላዩ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አሰ​ናዳ።
24እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው መቅ​ረ​ዙን በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ፥ በገ​በ​ታ​ውም ፊት ለፊት፥ በድ​ን​ኳኑ በአ​ዜብ በኩል አኖረ፤ 25ቀን​ዲ​ሎ​ቹ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አበራ።
26እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው የወ​ር​ቁን ማዕ​ጠ​ንት በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ በመ​ጋ​ረ​ጃው ፊት አኖረ። 27የአ​ዘ​ጋ​ጀ​ው​ንም ዕጣን ዐጠ​ነ​በት።
28ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ አዘ​ዘው በድ​ን​ኳኑ ደጅ ፊት መጋ​ረ​ጃ​ውን ዘረጋ። 29ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነ​ውን መሠ​ዊ​ያም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጅ አኖረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው በላዩ መሥ​ዋ​ዕ​ቱ​ንና ቍር​ባ​ኑን አቀ​ረበ።
30የመ​ታ​ጠ​ቢ​ያ​ው​ንም ሰን በም​ስ​ክሩ ድን​ኳ​ንና በመ​ሠ​ዊ​ያው መካ​ከል አኖረ፤ ለመ​ታ​ጠ​ቢ​ያም ውኃን ጨመ​ረ​በት። 31በእ​ር​ሱም ሙሴና አሮን፥ ልጆ​ቹም እጆ​ቻ​ቸ​ው​ንና እግ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ታጠቡ፤ 32እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን በገቡ ጊዜ፥ ወደ መሠ​ዊ​ያ​ውም በቀ​ረቡ ጊዜ ይታ​ጠቡ ነበር።#ምዕ. 40 ቍ. 28፥ 30፥ 31 እና 32 በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም።
33በድ​ን​ኳ​ኑና በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ዙሪያ አደ​ባ​ባ​ዩን ሠራ፤ የአ​ደ​ባ​ባ​ዩ​ንም ደጃፍ መጋ​ረጃ ዘረጋ። እን​ዲ​ሁም ሙሴ ሥራ​ውን ፈጸመ።
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር ድን​ኳ​ኑን እንደ ሞላው
(ዘኍ​. 9፥15-23)
34ደመ​ና​ውም የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ከደነ፤ ድን​ኳ​ን​ዋም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ክብር ተሞ​ላች። 35ደመ​ና​ውም በላዩ ስለ​ነ​በር ድን​ኳ​ኑም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ክብር ስለ ተሞላ ሙሴ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ይገባ ዘንድ አል​ቻ​ለም። 36ደመ​ና​ውም ከድ​ን​ኳኑ በተ​ነሣ ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በየ​ነ​ገ​ዳ​ቸው#ዕብ. “መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን” ይላል። ይጓዙ ነበር። 37ደመ​ናው ካል​ተ​ነሣ ግን ደመ​ናው እስ​ከ​ሚ​ነ​ሣ​በት ቀን ድረስ አይ​ጓ​ዙም ነበር። 38ደመና በቀን በድ​ን​ኳኑ ላይ ነበ​ርና፥ እሳ​ቱም በሚ​ጓ​ዙ​በት ሁሉ በሌ​ሊት በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ፊት በእ​ር​ስዋ ላይ ነበ​ርና።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ