የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፀ​አት 37

37
የቃል ኪዳኑ ታቦት አሠ​ራር
(ዘፀ. 25፥10-22)
1ባስ​ል​ኤ​ልም ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት ታቦ​ትን ሠራ፤ ርዝ​መቷ ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወር​ድዋ አንድ ክንድ ተኩል፥ ቁመ​ቷም አንድ ክንድ ተኩል ነበረ። 2በው​ስ​ጥ​ዋም፥ በው​ጭ​ዋም በጥሩ ወርቅ ለበ​ጣት፤ በዙ​ሪ​ያ​ዋም የወ​ርቅ አክ​ሊል አደ​ረ​ገ​ላት። 3አራት የወ​ርቅ ቀለ​በ​ቶ​ችም አደ​ረ​ገ​ላት፤ እነ​ር​ሱ​ንም በአ​ራቱ እግ​ሮ​ችዋ ላይ አኖረ። በአ​ንድ ወገን ሁለት ቀለ​በ​ቶች፥ በሌ​ላ​ውም ወገን ሁለት ቀለ​በ​ቶች ሆኑ። 4መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ች​ዋ​ንም ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት ሠራ፤ በወ​ር​ቅም ለበ​ጣ​ቸው። 5ታቦ​ቷ​ንም ለመ​ሸ​ከም በታ​ቦቷ አጠ​ገብ ባሉት አራት ቀለ​በ​ቶች መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ች​ዋን አገባ። 6ከጥሩ ወር​ቅም ርዝ​መቱ ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወር​ዱም አንድ ክንድ ተኩል የሆነ የስ​ር​የት መክ​ደኛ ሠራ​ላት። 7ሁለት ኪሩ​ቤ​ል​ንም ከተ​ቀ​ጠ​ቀጠ ወርቅ ሠራ፤ በስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ውም ላይ በሁ​ለት ወገን አደ​ረ​ጋ​ቸው። 8ከስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ውም ጋር አን​ዱን ኪሩብ በአ​ንድ ወገን፥ ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም ኪሩብ በሌላ ወገን በዚ​ህና በዚያ ሁለ​ቱን ኪሩ​ቤል ከስ​ር​የት መክ​ደ​ኛው በላይ ሠራ፤ 9ኪሩ​ቤ​ልም ክን​ፎ​ቻ​ቸ​ውን ወደ ላይ የዘ​ረጉ ሆኑ፥ የስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ው​ንም በክ​ን​ፎ​ቻ​ቸው ሸፈኑ፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ተያዩ፤ የኪ​ሩ​ቤ​ልም ፊቶ​ቻ​ቸው ወደ መክ​ደ​ኛው ተመ​ለ​ከቱ።
የኅ​ብ​ስተ ገጹ ገበታ አሠ​ራር
(ዘፀ. 25፥23-30)
10ርዝ​መቱ ሁለት ክንድ፥ ወር​ዱም አንድ ክንድ፥ ቁመ​ቱም አንድ ክንድ ተኩል የሆ​ነ​ውን ገበታ ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት ሠራ። 11በጥ​ሩም ወርቅ ለበ​ጠው፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም የወ​ርቅ አክ​ሊል አደ​ረ​ገ​ለት። 12በዙ​ሪ​ያ​ውም አንድ ጋት የሚ​ያ​ህል ክፈፍ አደ​ረ​ገ​ለት፤ የወ​ር​ቅም አክ​ሊል በክ​ፈፉ ዙሪያ አደ​ረ​ገ​ለት። 13አራ​ትም የወ​ርቅ ቀለ​በ​ቶች አደ​ረ​ገ​ለት፤ ቀለ​በ​ቶ​ቹ​ንም አራቱ እግ​ሮቹ ባሉ​በት በአ​ራቱ ማዕ​ዘ​ኖች አደ​ረገ። 14ገበ​ታ​ው​ንም ለመ​ሸ​ከም መሎ​ጊ​ያ​ዎቹ እን​ዲ​ሰ​ኩ​ባ​ቸው ቀለ​በ​ቶች በክ​ፈፉ አቅ​ራ​ቢያ ነበሩ። 15ገበ​ታ​ው​ንም ይሸ​ከ​ሙ​ባ​ቸው ዘንድ መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹን ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት ሠርቶ በወ​ርቅ ለበ​ጣ​ቸው። 16ለማ​ፍ​ሰ​ሻም ይሆኑ ዘንድ በገ​በ​ታው ላይ የሚ​ኖ​ሩ​ትን ዕቃ​ዎች፥ ወጭ​ቶ​ቹ​ንና ጭል​ፋ​ዎ​ቹን፥ ጽዋ​ዎ​ቹ​ንም፥ መቅ​ጃ​ዎ​ቹ​ንም ከጥሩ ወርቅ አደ​ረ​ጋ​ቸው።
የመ​ቅ​ረዙ አሠ​ራር
(ዘፀ. 25፥31-40)
17መቅ​ረ​ዝ​ዋ​ንም ከጥሩ ወርቅ አደ​ረገ፤ መቅ​ረ​ዝ​ዋ​ንም ከእ​ግ​ር​ዋና ከአ​ገ​ዳዋ ጋር በተ​ቀ​ረጸ ሥራ አደ​ረገ፤ ጽዋ​ዎ​ች​ዋን፥ ጕብ​ጕ​ቦ​ች​ዋን፥ አበ​ቦ​ች​ዋን ከዚ​ያው በአ​ን​ድ​ነት አደ​ረገ። 18በስ​ተ​ጎ​ንዋ ስድ​ስት ቅር​ን​ጫ​ፎች ወጡ​ላት፤ ሦስቱ የመ​ቅ​ረ​ዝዋ ቅር​ን​ጫ​ፎች በአ​ንድ ወገን፥ ሦስ​ቱም የመ​ቅ​ረ​ዝዋ ቅር​ን​ጫ​ፎች በሁ​ለ​ተ​ኛው ወገን ወጡ። 19በአ​ን​ደ​ኛው ቅር​ን​ጫፍ ጕብ​ጕ​ቡ​ንና አበ​ባ​ውን፥ ሦስ​ትም የለ​ውዝ አበባ የሚ​መ​ስ​ሉ​ትን ጽዋ​ዎች፥ በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ቅር​ን​ጫፍ ጕብ​ጕ​ቡ​ንና አበ​ባ​ውን፥ ሦስ​ትም የለ​ውዝ አበባ የሚ​መ​ስ​ሉ​ትን ጽዋ​ዎች፥ እን​ዲ​ሁም ከመ​ቅ​ረ​ዝዋ ለወጡ ለስ​ድ​ስቱ ቅር​ን​ጫ​ፎች አደ​ረገ። 20በመ​ቅ​ረ​ዝ​ዋም ጕብ​ጕ​ቦ​ች​ዋ​ንና አበ​ቦ​ች​ዋን፥ አራ​ትም የለ​ውዝ አበባ የሚ​መ​ስ​ሉ​ትን ጽዋ​ዎች አደ​ረገ። 21ከመ​ቅ​ረ​ዝዋ ለወጡ ለስ​ድ​ስት ቅር​ን​ጫ​ፎች ከሁ​ለት ቅር​ን​ጫ​ፎች በታች አንድ ሆኖ የተ​ሠራ አንድ ጕብ​ጕብ፥ ከሁ​ለ​ትም ቅር​ን​ጫ​ፎች በታች አንድ ሆኖ የተ​ሠራ አንድ ጕብ​ጕብ፥ ደግሞ ከሁ​ለት ቅር​ን​ጫ​ፎች በታች አንድ ሆኖ የተ​ሠራ አንድ ጕብ​ጕብ ነበረ። 22ጕብ​ጕ​ቦ​ች​ዋና ቅር​ን​ጫ​ፎ​ችዋ ከእ​ርሱ ጋር አንድ ነበሩ፤ ሁሉም አንድ ሆኖ ከተ​ቀ​ረጸ ከጥሩ ወርቅ ተሠ​ርቶ ነበር። 23ሰባ​ቱ​ንም መብ​ራ​ቶ​ች​ዋን መኰ​ስ​ተ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋ​ንም፥ የኵ​ስ​ታሪ ማድ​ረ​ጊ​ያ​ዎ​ች​ዋ​ንም ከጥሩ ወርቅ ሠራ። 24መቅ​ረ​ዙ​ንም፥ ዕቃ​ው​ንም ሁሉ ከአ​ንድ መክ​ሊት ጥሩ ወርቅ አደ​ረገ።
የዕ​ጣን መሠ​ዊ​ያው አሠ​ራር
(ዘፀ. 30፥1-5)
25የዕ​ጣን መሠ​ዊ​ያ​ንም ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት ሠራ፤ ርዝ​መቱ አንድ ክንድ፥ ስፋቱ አንድ ክንድ፤ አራት ማዕ​ዘን ነበር፤ ከፍ​ታ​ውም ሁለት ክንድ ነበር፤ ቀን​ዶ​ቹም ከእ​ርሱ ጋር በአ​ን​ድ​ነት የተ​ሠሩ ነበሩ። 26ላይ​ኛ​ው​ንና የግ​ድ​ግ​ዳ​ው​ንም ዙሪያ፥ ቀን​ዶ​ቹ​ንም በጥሩ ወርቅ ለበ​ጠው፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም የወ​ርቅ ክፈፍ አደ​ረ​ገ​በት። 27ከክ​ፈ​ፉም በታች ሁለት የወ​ርቅ ቀለ​በ​ቶች አደ​ረ​ገ​በት፤ በዚ​ህና በዚያ በሁ​ለ​ቱም ጎን አደ​ረ​ጋ​ቸው፤ ለመ​ሸ​ከ​ምም የመ​ሎ​ጊ​ያ​ዎች መግ​ቢያ ነበሩ። 28መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት አደ​ረገ፤ በወ​ር​ቅም ለበ​ጣ​ቸው። 29የተ​ቀ​ደ​ሰ​ው​ንም የቅ​ብ​ዐ​ቱን ዘይት፥ ጥሩ​ው​ንም የጣ​ፋጭ ሽቱ ዕጣን በቀ​ማሚ ብል​ሃት እንደ ተሠራ አደ​ረገ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ