የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፀ​አት 3:3-11

ኦሪት ዘፀ​አት 3:3-11 አማ2000

ሙሴም፥ “ልሂ​ድና ቍጥ​ቋ​ጦው ስለ​ምን አል​ተ​ቃ​ጠ​ለም? ይህን ታላቅ ራእይ ልይ” አለ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ ይመ​ለ​ከት ዘንድ እንደ መጣ በአየ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከቍ​ጥ​ቋ​ጦው ውስጥ እር​ሱን ጠርቶ፥ “ሙሴ! ሙሴ!” አለው እር​ሱም፥ “ይህ ምን​ድን ነው?” አለ። “ወደ​ዚህ አት​ቅ​ረብ፤ አንተ የቆ​ም​ህ​ባት ስፍራ የተ​ቀ​ደ​ሰች መሬት ናትና፥ ጫማ​ህን ከእ​ግ​ርህ አውጣ” አለው። ደግ​ሞም፥ “እኔ የአ​ባ​ቶ​ችህ አም​ላክ፥ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ፥ የይ​ስ​ሐ​ቅም አም​ላክ፥ የያ​ዕ​ቆ​ብም አም​ላክ ነኝ” አለው። ሙሴም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያይ ዘንድ ፈር​ቶ​አ​ልና ፊቱን መለሰ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “በግ​ብፅ ያለ​ውን የሕ​ዝ​ቤን መከራ በእ​ው​ነት አየሁ፦ ከአ​ሠ​ሪ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም የተ​ነሣ ጩኸ​ታ​ቸ​ውን ሰማሁ፤ ሥቃ​ያ​ቸ​ው​ንም ዐው​ቄ​አ​ለሁ፤ ከግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንም እጅ አድ​ና​ቸው ዘንድ፥ ከዚ​ያ​ችም ሀገር ወተ​ትና ማር ወደ​ም​ታ​ፈ​ስ​ሰው ሀገር፥ ወደ ሰፊ​ዪ​ቱና ወደ መል​ካ​ሚቱ ሀገር፥ ወደ ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ኬጤ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ኤዌ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም ስፍራ አወ​ጣ​ቸው ዘንድ ወረ​ድሁ። አሁ​ንም እነሆ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ጩኸት ወደ እኔ ደረሰ፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ባ​ቸ​ውን ግፍ ደግሞ አየሁ። አሁ​ንም ና፤ ወደ ግብፅ ንጉሥ ወደ ፈር​ዖን እል​ክ​ሃ​ለሁ። ሕዝ​ቤን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከግ​ብፅ ምድር ታወ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ።” ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን፥ “ወደ ግብፅ ንጉሥ ወደ ፈር​ዖን እሄድ ዘንድ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ከግ​ብፅ ምድር አወጣ ዘንድ እኔ ማን ነኝ?” አለው።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}