የሙሴም አማት አለው፥ “አንተ የምታደርገው ይህ ነገር ትክክል አይደለም። አንተ፥ ከአንተም ጋር ያለው ሕዝብ ትደክማላችሁ፤ ይህ ነገር ይከብድብሃል፤ አንተ ብቻህን ልታደርገው አትችልም። አሁንም እመክርሃለሁና ስማኝ፤ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋር ይሆናል፤ አንተ በእግዚአብሔር ፊት ለሕዝቡ ሁን፤ ነገራቸውንም ወደ እግዚአብሔር አድርስ፤ የእግዚአብሔርንም ሥርዐቱንና ሕጉን መስክርላቸው፤ የሚሄዱበትንም መንገድ፥ የሚያደርጉትንም ሥራ ሁሉ አሳያቸው። አንተም ከሕዝቡ ሁሉ ኀያላን ሰዎችን፥ እግዚአብሔርን የሚፈሩትን እውነተኞች ሰዎችን፥ ትዕቢትንም የሚጠሉ ሰዎችን ፈልግ። ከእነርሱም የሺህ አለቆችን፥ የመቶ አለቆችን፥ የአምሳ አለቆችን፥ የዐሥርም አለቆችን ሹምላቸው። በሕዝቡ ላይ ሁል ጊዜ ይፍረዱ፤ የከበዳቸውን ነገር ወደ አንተ ያምጡት፤ ቀላሉን ነገር ሁሉ እነርሱ ይፍረዱ፤ ያቃልሉልሃል፤ ይረዱሃልም። ይህንም ቃሌን ብታደርግ፥ እግዚአብሔር ያበረታሃል፤ መፍረድም ትችላለህ፤ ሕዝቡም ሁሉ በሰላም ወደ ስፍራው ይመለሳል።” ሙሴም የአማቱን ቃል ሰማ፤ እንደ አለውም አደረገ። ሙሴም ከእስራኤል ሁሉ ችሎታ ያላቸውን ሰዎች መረጠ፤ በሕዝቡም ላይ የሺህ አለቆች፥ የመቶ አለቆች፥ የአምሳም አለቆች፥ የዐሥርም አለቆች አድርጎ ሾማቸው።
ኦሪት ዘፀአት 18 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኦሪት ዘፀአት 18:17-25
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos