ኦሪት ዘፀ​አት 17:9-13

ኦሪት ዘፀ​አት 17:9-13 አማ2000

ሙሴም ኢያ​ሱን፥ “ጐል​ማ​ሶ​ችን ለአ​ንተ ምረጥ፤ ሲነ​ጋም ወጥ​ተህ ከዐ​ማ​ሌቅ ጋር ተዋጋ፤ እኔም በተ​ራ​ራው ራስ ላይ እቆ​ማ​ለሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በትር በእጄ ናት” አለው። ኢያ​ሱም ሙሴ እንደ አለው አደ​ረገ፤ ወጥ​ቶም ከዐ​ማ​ሌቅ ጋር ተዋጋ፤ ሙሴና አሮን፥ ሖርም ወደ ኮረ​ብ​ታው ራስ ወጡ። እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ሙሴ እጁን በአ​ነሣ ጊዜ እስ​ራ​ኤል ድል ያደ​ርግ ነበር ፤ እጁ​ንም በአ​ወ​ረደ ጊዜ ዐማ​ሌቅ ድል ያደ​ርግ ነበር። የሙሴ እጆች ግን ከብ​ደው ነበር፤ ድን​ጋ​ይም ወሰዱ፤ በበ​ታ​ቹም አኖሩ፤ እር​ሱም ተቀ​መ​ጠ​በት፤ አሮ​ንና ሖርም አንዱ በዚህ አንዱ በዚያ ሆነው እጆ​ቹን ይደ​ግፉ ነበር፤ ፀሐ​ይም እስ​ክ​ት​ገባ ድረስ እጆቹ ተዘ​ር​ግ​ተው ነበር። ኢያ​ሱም ዐማ​ሌ​ቅ​ንና ሕዝ​ቡን በሰ​ይፍ ስለት አሸ​ነፈ።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}