ኢያሱም ሙሴ እንደ አለው አደረገ፤ ወጥቶም ከዐማሌቅ ጋር ተዋጋ፤ ሙሴና አሮን፥ ሖርም ወደ ኮረብታው ራስ ወጡ። እንዲህም ሆነ፤ ሙሴ እጁን በአነሣ ጊዜ እስራኤል ድል ያደርግ ነበር ፤ እጁንም በአወረደ ጊዜ ዐማሌቅ ድል ያደርግ ነበር። የሙሴ እጆች ግን ከብደው ነበር፤ ድንጋይም ወሰዱ፤ በበታቹም አኖሩ፤ እርሱም ተቀመጠበት፤ አሮንና ሖርም አንዱ በዚህ አንዱ በዚያ ሆነው እጆቹን ይደግፉ ነበር፤ ፀሐይም እስክትገባ ድረስ እጆቹ ተዘርግተው ነበር። ኢያሱም ዐማሌቅንና ሕዝቡን በሰይፍ ስለት አሸነፈ። እግዚአብሔርም ሙሴን፥ “የዐማሌቅን ዝክር ከሰማይ በታች ጨርሼ እደመስሳለሁና ይህን ለመታሰቢያ በመጽሐፍ ጻፈው፤ በኢያሱም ጆሮ ተናገር” አለው።
ኦሪት ዘፀአት 17 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኦሪት ዘፀአት 17:10-14
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች