የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ኤፌ​ሶን ሰዎች 2:11-16

ወደ ኤፌ​ሶን ሰዎች 2:11-16 አማ2000

እና​ንተ አሕ​ዛብ አስቡ፤ ቀድሞ በሥጋ ሥር​ዐት ነበ​ራ​ችሁ፤ ያል​ተ​ገ​ዘ​ሩም ይሉ​አ​ችሁ ነበር፤ እን​ዲህ የሚ​ሉ​አ​ች​ሁም የተ​ገ​ዘሩ ሰዎች ናቸው፤ ግዝ​ረት ግን በሥጋ ላይ የሚ​ደ​ረግ የሰው እጅ ሥራ ነው። ያን​ጊዜ ክር​ስ​ቶ​ስን አታ​ው​ቁ​ትም ነበር፤ ከእ​ስ​ራ​ኤል ሕግ የተ​ለ​ያ​ችሁ ነበ​ራ​ችሁ፤ ከተ​ስ​ፋው ሥር​ዐ​ትም እን​ግ​ዶች ነበ​ራ​ችሁ፤ ተስ​ፋም አል​ነ​በ​ራ​ች​ሁም፤ በዚ​ህም ዓለም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አታ​ው​ቁ​ትም ነበር። አሁን ግን ቀድሞ ርቃ​ችሁ የነ​በ​ራ​ችሁ እና​ንተ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ሆና​ችሁ በክ​ር​ስ​ቶስ ደም ቀረ​ባ​ችሁ። ሁለ​ቱን አንድ ያደ​ረገ ሰላ​ማ​ችን እርሱ ነውና፥ በሥ​ጋ​ውም በመ​ካ​ከል የነ​በ​ረ​ውን የጥል ግድ​ግዳ አፍ​ርሶ ጥልን ሻረ። ሁለ​ቱ​ንም አድሶ አንድ ያደ​ር​ጋ​ቸው ዘንድ በሥ​ር​ዐቱ የት​እ​ዛ​ዝን ሕግ አጠፋ፤ ዕር​ቅ​ንም አደ​ረገ። በመ​ስ​ቀ​ሉም በአ​ንድ ሥጋው ሁለ​ቱን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቀ​ረ​ባ​ቸው፤ በእ​ር​ሱም ጥልን አጠፋ።

Free Reading Plans and Devotionals related to ወደ ኤፌ​ሶን ሰዎች 2:11-16