የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ኤፌ​ሶን ሰዎች 2:1-7

ወደ ኤፌ​ሶን ሰዎች 2:1-7 አማ2000

እና​ን​ተም በኀ​ጢ​አ​ታ​ችሁ ምው​ታን ሆና​ችሁ ነበር። ይኸ​ውም ቀድሞ በዚህ ዓለም ሥር​ዐት፥ አሁን በከ​ሓ​ድ​ያን ልጆች የሚ​በ​ረ​ታ​ታ​ባ​ቸ​ውና፥ በነ​ፋስ አም​ሳል የሚ​ገ​ዛ​ቸው አለቃ እንደ ነበ​ረው ፈቃድ ጸን​ታ​ችሁ የነ​በ​ራ​ች​ሁ​በት ነው። እኛ ሁላ​ችን ቀድሞ እንደ ሥጋ​ችን ምኞት ኖርን፤ የሥ​ጋ​ች​ን​ንም ፈቃ​ድና ያሰ​ብ​ነ​ውን አደ​ረ​ግን፤ እንደ ሌሎች ኃጥ​አ​ንም ሁሉ የጥ​ፋት ልጆች ሆንን። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን በም​ሕ​ረቱ ባለ​ጸ​ግ​ነ​ትና በወ​ደ​ደን በፍ​ቅሩ ብዛት፥ በኃ​ጢ​አ​ታ​ችን የሞ​ትን ሳለን በክ​ር​ስ​ቶስ ሕይ​ወ​ትን ሰጠን፤ በጸ​ጋ​ውም ዳንን። በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም አስ​ነ​ሥቶ በሰ​ማ​ያት ከእ​ርሱ ጋር አኖ​ረን። በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ይቅር ስላ​ለን የጸ​ጋ​ውን ባለ​ጠ​ግ​ነት ብዛት በሚ​መ​ጣው ዓለም ይገ​ልጥ ዘንድ፥