መጽ​ሐፈ መክ​ብብ 9:7-9

መጽ​ሐፈ መክ​ብብ 9:7-9 አማ2000

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራ​ህን ተቀ​ብ​ሎ​ታ​ልና፦ ና እን​ጀ​ራ​ህን በደ​ስታ ብላ፥ በበጎ ልቡ​ናም የወ​ይን ጠጅ​ህን ጠጣ። ሁል​ጊዜ ልብ​ስህ ነጭ ይሁን፤ ቅባ​ትም ከራ​ስህ ላይ አይ​ታጣ። በሕ​ይ​ወ​ትህ፥ አን​ተም ከፀ​ሓይ በታች በም​ት​ደ​ክ​ም​በት ድካም ይህ ዕድል ፈን​ታህ ነውና ከንቱ በሆነ በሕ​ይ​ወ​ትህ ዘመን ሁሉ፥ ከፀ​ሓይ በታች በሰ​ጠህ፥ በከ​ንቱ ዘመ​ንህ ሁሉ፥ ከም​ት​ወ​ድ​ዳት ሚስ​ትህ ጋር ደስ ይበ​ልህ።