የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘዳ​ግም 28:6-13

ኦሪት ዘዳ​ግም 28:6-13 አማ2000

አን​ተም በመ​ግ​ባ​ትህ ቡሩክ ትሆ​ና​ለህ፥ በመ​ው​ጣ​ት​ህም ቡሩክ ትሆ​ና​ለህ። “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ግ​ርህ በታች ይወ​ድቁ ዘንድ የሚ​ቃ​ወ​ሙ​ህን ጠላ​ቶ​ች​ህን በእ​ጅህ ይጥ​ላ​ቸ​ዋል፤ በአ​ንድ መን​ገድ ይመ​ጡ​ብ​ሃል፤ በሰ​ባ​ትም መን​ገድ ከፊ​ትህ ይሸ​ሻሉ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በረ​ከ​ቱን በአ​ንተ ላይ፥ በጎ​ተ​ራህ፥ በእ​ህ​ል​ህም ሥራ ሁሉ እን​ዲ​ወ​ርድ ይል​ካል፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሚ​ሰ​ጥ​ህም ምድር ይባ​ር​ክ​ሃል። የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ብት​ሰማ፥ በመ​ን​ገ​ዱም ብት​ሄድ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ባ​ቶ​ችህ እንደ ማለ ለእ​ርሱ የተ​ቀ​ደሰ ሕዝብ አድ​ርጎ ያቆ​ም​ሃል። የም​ድር አሕ​ዛ​ብም ሁሉ የአ​ም​ላ​ክህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም በአ​ንተ ላይ እንደ ተጠራ አይ​ተው ይፈ​ሩ​ሃል። አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እር​ስ​ዋን ይሰ​ጥህ ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ችህ በማ​ለ​ላ​ቸው በም​ድ​ርህ ላይ፥ በሆ​ድህ ፍሬ፥ በእ​ር​ሻ​ህም ፍሬ፥ ከብ​ቶ​ች​ህን በማ​ብ​ዛት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ​ነ​ቱን ያበ​ዛ​ል​ሃል። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለም​ድ​ርህ በወ​ራቱ ዝና​ብን ይሰጥ ዘንድ፥ የእ​ጅ​ህ​ንም ሥራ ሁሉ ይባ​ርክ ዘንድ መል​ካ​ሙን መዝ​ገብ ሰማ​ዩን ይከ​ፍ​ት​ል​ሃል፤ ለብዙ አሕ​ዛ​ብም ታበ​ድ​ራ​ለህ፥ አንተ ግን ከማ​ንም አት​በ​ደ​ርም፤ ብዙ አሕ​ዛ​ብን ትገ​ዛ​ለህ፥ አን​ተን ግን እነ​ርሱ አይ​ገ​ዙ​ህም። ዛሬም ያዘ​ዝ​ሁ​ህን የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ሰም​ተህ ብት​ጠ​ብ​ቃት፥ ብታ​ደ​ር​ጋ​ትም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራስ ያደ​ር​ግ​ሃል እንጂ ጅራት አያ​ደ​ር​ግ​ህም፤ ሁል​ጊ​ዜም በላይ እንጂ በታች አት​ሆ​ንም።