የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘዳ​ግም 2

2
እስ​ራ​ኤል በበ​ረሃ የዞ​ሩ​ባ​ቸው ዓመ​ታት
1“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዳ​ለኝ ተመ​ል​ሰን በኤ​ር​ትራ ባሕር መን​ገድ ወደ ምድረ በዳ ሄድን፤ የሴ​ይ​ር​ንም ተራራ ብዙ ቀን ዞርን። 2እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረኝ፦ 3‘ይህን ተራራ መዞር ይበ​ቃ​ች​ኋል፤ ተመ​ል​ሳ​ችሁ ወደ መስዕ ሂዱ።’ 4ሕዝ​ቡ​ንም እን​ዲህ ብለህ እዘ​ዛ​ቸው፦ በሴ​ይር ላይ በተ​ቀ​መ​ጡት በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ በዔ​ሳው ልጆች ሀገር ታል​ፋ​ላ​ችሁ፤ እነ​ርሱ ይፈ​ሩ​አ​ች​ኋል፤ እን​ግ​ዲህ እጅግ ተጠ​ን​ቀቁ። 5የሴ​ይ​ርን ተራራ ለዔ​ሳው ልጆች ርስት አድ​ርጌ ስለ ሰጠሁ እኔ ከም​ድ​ራ​ቸው የጫማ መር​ገጫ ታህል እን​ኳን አል​ሰ​ጣ​ች​ሁ​ምና አት​ጣ​ሉ​አ​ቸው። 6ከእ​ነ​ርሱ በገ​ን​ዘብ ምግብ ገዝ​ታ​ችሁ ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ ውኃም ደግሞ በገ​ን​ዘብ በመ​ለ​ኪያ ገዝ​ታ​ችሁ ትጠ​ጣ​ላ​ችሁ። 7አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ጅ​ህን ሥራ ሁሉ ባር​ኮ​ል​ሃ​ልና፤ ይህን ታላ​ቅና የሚ​ያ​ስ​ፈራ ምድረ በዳ እን​ዴት እንደ ዞር​ኸው ዕወቅ፤#ዕብ. “በዚህ በታ​ላቅ ምድረ በዳ መሄ​ድ​ህን ዐው​ቆ​አል” ይላል። በዚህ አርባ ዓመት ውስጥ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነበረ፤ ከተ​ና​ገ​ር​ኸው ሁሉ አን​ዳ​ችም አላ​ሳ​ጣ​ህም። 8በሴ​ይ​ርም ከተ​ቀ​መ​ጡት ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ከዔ​ሳው ልጆች በዓ​ረባ መን​ገድ ከኤ​ሎ​ንና#ዕብ. “ከኤ​ላ​ትና” ይላል። ከጋ​ስ​ዮን-ጋብር አለ​ፍን። ተመ​ል​ሰ​ንም በሞ​ዓብ ምድረ በዳ መን​ገድ አለ​ፍን።
9“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፦ እኔ አሮ​ኤ​ርን#ዕብ. “ዔርን” ይላል። ለሎጥ ልጆች ርስት አድ​ርጌ ስለ ሰጠሁ ከም​ድሩ ርስት አል​ሰ​ጣ​ች​ሁ​ምና ሞዓ​ባ​ው​ያ​ንን አት​ጣላ፤ በሰ​ል​ፍም አት​ው​ጋ​ቸው። 10እንደ ዔና​ቃ​ው​ያን ታላ​ቅና ብዙ ሕዝብ ኀያ​ላ​ንም የሆኑ ኦሚ​ና​ው​ያን አስ​ቀ​ድሞ በዚያ ይቀ​መጡ ነበር። 11እነ​ር​ሱም ደግሞ እንደ ዔና​ቃ​ው​ያን ራፋ​ይም ተብ​ለው ይታ​ወቁ ነበር፤ ሞዓ​ባ​ው​ያን ግን “ኦሚን” ብለው ይጠ​ሩ​አ​ቸው ነበር። 12ሖራ​ው​ያ​ንም ደግሞ አስ​ቀ​ድሞ በሴ​ይር ላይ ተቀ​ም​ጠው ነበር፤ የዔ​ሳው ልጆች ግን መቱ​አ​ቸው፤ ከፊ​ታ​ቸ​ውም አጠ​ፉ​አ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሰ​ጠው በር​ስቱ ምድር እስ​ራ​ኤል እን​ዳ​ደ​ረገ፥ በስ​ፍ​ራ​ቸው ተቀ​መጡ። 13አሁ​ንም ‘ተነ​ሡና ተጓዙ፤ የዛ​ሬ​ድ​ንም ፈፋ ተሻ​ገሩ፤’ የዛ​ሬ​ድ​ንም ፈፋ ተሻ​ገ​ርን። 14የዛ​ሬ​ድ​ንም ፈፋ እስከ ተሻ​ገ​ር​ን​በት ድረስ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ማለ​ባ​ቸው ተዋ​ጊ​ዎች የሆኑ የዚ​ያች ትው​ልድ ሰዎች ከሰ​ፈሩ መካ​ከል እስከ ጠፉ ድረስ፥ ከቃ​ዴስ በርኔ የተ​ጓ​ዝ​ን​በት ዘመን ሠላሳ ስም​ንት ዓመት ሆነ። 15ከሰ​ፈ​ርም መካ​ከል ተለ​ይ​ተው እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በላ​ያ​ቸው ነበረ።
16“እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ተዋ​ጊ​ዎቹ ከጠፉ፥ ከሕ​ዝ​ቡም መካ​ከል ከሞቱ በኋላ፥ 17እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረኝ፦ 18‘አንተ ዛሬ የሞ​ዓ​ብን ዳርቻ አሮ​ኤ​ርን ታል​ፋ​ለህ፤ 19ለሎ​ጥም ልጆች ርስት አድ​ርጌ ስለ ሰጠሁ ከአ​ሞን ልጆች ምድር ርስት አል​ሰ​ጥ​ህ​ምና በአ​ሞን ልጆች አቅ​ራ​ቢያ ስት​ደ​ርስ አት​ጣ​ላ​ቸው፤ አት​ው​ጋ​ቸ​ውም።’ 20ያም ደግሞ የራ​ፋ​ይም ምድር ተብሎ ተቈ​ጠረ፤ ራፋ​ይ​ምም አስ​ቀ​ድሞ በዚያ ተቀ​ም​ጠው ነበረ፤ አሞ​ና​ው​ያን ግን “ዘም​ዞ​ማ​ው​ያን” ብለው ይጠ​ሩ​አ​ቸ​ዋል። 21እነ​ር​ሱም እንደ ዔና​ቃ​ው​ያን ታላ​ቅና ብዙ፥ ጽኑ​ዓ​ንም ሕዝብ ነበሩ፤#ዕብ. “እንደ ዔና​ቅም ልጆች ቁመ​ታ​ቸው የረ​ዘመ ነበሩ” ይላል። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከፊ​ታ​ቸው አጠ​ፋ​ቸው፤ እነ​ር​ሱ​ንም አሳ​ድ​ደው በስ​ፍ​ራ​ቸው ተቀ​መጡ። 22ሖራ​ው​ያ​ንን ከፊ​ታ​ቸው አጥ​ፍቶ በሴ​ይር ለተ​ቀ​መ​ጡት ለዔ​ሳው ልጆች እን​ዳ​ደ​ረገ#ዕብ. “እን​ዲሁ ለእ​ነ​ርሱ አደ​ረገ እነ​ር​ሱ​ንም አሳ​ድ​ደው ...” ይላል። እነ​ርሱ ወረ​ሱ​አ​ቸው፤ በእ​ነ​ር​ሱም ፋንታ#ዕብ. “በስ​ፍ​ራ​ቸው” ይላል። እስከ ዛሬ ድረስ ተቀ​መጡ። 23እስከ ጋዛም ድረስ በአ​ሴ​ሮት ተቀ​ም​ጠው የነ​በ​ሩ​ትን ኤዋ​ው​ያ​ን​ንና ከቀ​ጰ​ዶ​ቅያ የወጡ ቀጰ​ዶ​ቃ​ው​ያ​ንን#ዕብ. “ከከ​ፍ​ቶር የወጡ ከፍ​ቶ​ራ​ው​ያን” ይላል። አጠ​ፉ​አ​ቸው፤ በእ​ነ​ር​ሱም ፋንታ ተቀ​መጡ። 24ደግ​ሞም አለ፦ ተነ​ሥ​ታ​ችሁ ሂዱ፤ የአ​ር​ኖ​ን​ንም ሸለቆ ተሻ​ገሩ፤ እነሆ፥ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ዊ​ውን የሐ​ሴ​ቦ​ንን ንጉሥ ሴዎ​ንን፥ ምድ​ሩ​ንም በእ​ጅህ አሳ​ልፌ ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ፤ እር​ስ​ዋን ግዛት፤ ውረ​ሳት፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ተዋጋ። 25ከሰ​ማይ በታች ባሉ አሕ​ዛብ ሁሉ ላይ ማስ​ደ​ን​ገ​ጥ​ህ​ንና ማስ​ፈ​ራ​ት​ህን እሰ​ድድ ዘንድ ዛሬ እጀ​ም​ራ​ለሁ፤ ስም​ህን በሰሙ ጊዜ በፊ​ትህ ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣሉ፤ ድን​ጋ​ጤም ይይ​ዛ​ቸ​ዋል።
እስ​ራ​ኤል ንጉሥ ሴዎ​ንን ድል እንደ አደ​ረጉ (ዘኍ​. 21፥ 21-30)
26“ከቄ​ድ​ሞ​ትም ምድረ በዳ የሰ​ላ​ምን ቃል ይነ​ግ​ሩት ዘንድ ወደ ሐሴ​ቦን ንጉሥ ወደ ሴዎን እን​ዲህ ብዬ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላክሁ፦ 27‘በሀ​ገ​ርህ ላይ ልለፍ፤ በአ​ውራ ጎዳና እሄ​ዳ​ለሁ፤ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አል​ተ​ላ​ለ​ፍም። 28የም​በ​ላ​ውን ምግብ በገ​ን​ዘብ ሽጥ​ልኝ፤ የም​ጠ​ጣ​ው​ንም ውኃ በገ​ን​ዘብ ስጠኝ፤ በእ​ግሬ ብቻ ልለፍ፤ 29በሴ​ይር የተ​ቀ​መጡ የዔ​ሳው ልጆች፥ በአ​ሮ​ዔ​ርም የተ​ቀ​መጡ ሞዓ​ባ​ው​ያን እን​ዳ​ደ​ረ​ጉ​ልኝ፥ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ​ሚ​ሰ​ጠን ምድር ዮር​ዳ​ኖ​ስን እስ​ክ​ሻ​ገር ድረስ በእ​ግሬ ልለፍ። 30የሐ​ሴ​ቦን ንጉሥ ሴዎን ግን ያሳ​ል​ፈን ዘንድ አል​ፈ​ቀ​ደም፤ እንደ ዛሬው ሁሉ በእ​ጅህ አሳ​ልፎ ይሰ​ጠው ዘንድ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈ​ሱን አደ​ን​ድ​ኖ​ታ​ልና፥ ልቡ​ንም አጽ​ን​ቶ​ታ​ልና። 31እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ ‘የሐ​ሴ​ቦ​ንን ንጉሥ አሞ​ራ​ዊ​ውን ሴዎ​ን​ንና ምድ​ሩን በፊ​ትህ በእ​ጅህ አሳ​ልፌ መስ​ጠት እነሆ፥ ጀመ​ርሁ፤ ምድ​ሩን ትገዛ ዘንድ መው​ረስ ጀምር’ አለኝ። 32ሴዎ​ንም ሕዝ​ቡም ሁሉ ሊዋ​ጉን ወደ ኢያሳ ወጡ። 33አም​ላ​ካ​ች​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እር​ሱን አሳ​ልፎ በእ​ጃ​ችን ሰጠን፤ እር​ሱ​ንም፥ ልጆ​ቹ​ንም፥ ሕዝ​ቡ​ንም ሁሉ መታን። 34በዚ​ያን ጊዜም ከተ​ሞ​ቹን ሁሉ ወሰ​ድን፤ ከተ​ማ​ው​ንም#ዕብ. “የተ​ቀ​መ​ጡ​ባ​ቸ​ውን ሰዎች” ይላል። ሁሉ፥ ሴቶ​ች​ንም፥ ሕፃ​ኖ​ች​ንም አጠ​ፋን፤ አን​ዳ​ችም የሸሸ በሕ​ይ​ወት አላ​ስ​ቀ​ረ​ንም፥ 35ለእኛ ከማ​ረ​ክ​ና​ቸው ከብ​ቶ​ቻ​ቸ​ውና ከከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው ከወ​ሰ​ድ​ነው ምርኮ በቀር። 36በአ​ር​ኖን ሸለቆ አጠ​ገብ ካለ​ችው ከአ​ሮ​ዔ​ርና በሸ​ለ​ቆ​ውም ውስጥ ካለ​ችው ከተማ ጀም​ረን እስከ ገለ​ዓድ ተራራ ድረስ ማን​ኛ​ዪ​ቱም ከተማ አላ​መ​ለ​ጠ​ች​ንም፤ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሁሉን አሳ​ልፎ በእ​ጃ​ችን ሰጠን። 37ዳሩ ግን አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘን ወደ አሞን ልጆች ምድር፥ በያ​ቦ​ቅም ወንዝ አጠ​ገብ ወደ አለው ስፍራ ሁሉ፥ በተ​ራ​ራ​ማ​ውም ሀገር ወደ አሉ ከተ​ሞች አል​ደ​ረ​ስ​ንም።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ