ኦሪት ዘዳ​ግም 19:10-12

ኦሪት ዘዳ​ግም 19:10-12 አማ2000

አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትወ​ር​ሳት ዘንድ በሚ​ሰ​ጥህ ምድር ውስጥ ንጹሕ ደም እን​ዳ​ይ​ፈ​ስስ፥ በው​ስ​ጥ​ህም የደም ወን​ጀ​ለኛ እን​ዳ​ይ​ኖር። “ሰው ግን ባል​ን​ጀ​ራ​ውን ቢጠላ፥ ቢሸ​ም​ቅ​በ​ትም፥ በእ​ር​ሱም ላይ ቢነሣ፥ ቢገ​ድ​ለ​ውም፥ ከእ​ነ​ዚህ ከተ​ሞች በአ​ን​ዲቱ ቢማ​ጠን፥ የከ​ተ​ማው ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ይል​ካሉ፤ ከዚ​ያም ይይ​ዙ​ታል። በባ​ለ​ደ​ሙም እጅ አሳ​ል​ፈው ይሰ​ጡ​ታል፤ ይሞ​ታ​ልም።