ወደ ቈላ​ስ​ይስ ሰዎች 2:1-19

ወደ ቈላ​ስ​ይስ ሰዎች 2:1-19 አማ2000

ስለ እና​ንተ እና በሎ​ዶ​ቅያ ስላሉ፥ ፊቴ​ንም በሥጋ ስላ​ላ​ዩት ምእ​መ​ናን ሁሉ ምን ያህል እን​ደ​ም​ጋ​ደል ልታ​ውቁ እወ​ዳ​ለሁ። ይኸ​ውም ልቡ​ና​ቸው ደስ ይለው ዘንድ፥ ትም​ህ​ር​ታ​ቸ​ውም በማ​ወቅ፥ በፍ​ቅ​ርና ፍጹ​ም​ነት ባለው ባለ​ጸ​ግ​ነት፥ በጥ​በ​ብና በሃ​ይ​ማ​ኖት፥ ስለ ክር​ስ​ቶ​ስም የሆ​ነ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምክር በማ​ወቅ ይጸና ዘንድ ነው። የተ​ሰ​ወረ የጥ​በ​ብና የም​ክር መዝ​ገብ ሁሉ በእ​ርሱ ዘንድ አለ። ይህ​ንም የም​ላ​ችሁ በሚ​ያ​ባ​ብል ነገር የሚ​ያ​ስ​ታ​ችሁ እን​ዳ​ይ​ኖር ነው። እኔ በሥጋ ከእ​ና​ንተ ዘንድ ባል​ኖ​ርም እን​ኳን፥ በመ​ን​ፈስ ከእ​ና​ንተ ጋር ነኝ፤ እነሆ ጠባ​ያ​ች​ሁ​ንና ሥር​ዐ​ታ​ች​ሁን፥ በክ​ር​ስ​ቶ​ስም ያለ የእ​ም​ነ​ታ​ች​ሁን ጽናት ስለ አየሁ ደስ ይለ​ኛል። እን​ግ​ዲህ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን እንደ ተቀ​በ​ላ​ች​ሁት፥ በእ​ርሱ ተመ​ላ​ለሱ። በእ​ርሱ ተመ​ሥ​ር​ታ​ችሁ ታነጹ፤ በም​ስ​ጋ​ናው ትበዙ ዘንድ፥ በተ​ማ​ራ​ች​ሁት ሃይ​ማ​ኖት ጽኑ። ለዚህ ዓለም ስሕ​ተት፥ በክ​ር​ስ​ቶስ ሕግ ያይ​ደለ፥ በሰው ሠራሽ ሥር​ዐት ለከ​ንቱ የሚ​ያ​ታ​ልሉ ሰዎች በነ​ገር ማራ​ቀቅ እን​ዳ​ያ​ታ​ል​ሉ​አ​ችሁ፥ ተጠ​ን​ቀቁ። በእ​ርሱ ፍጹም መለ​ኮቱ በሥጋ ተገ​ልጦ ይኖ​ራ​ልና። እና​ን​ተም በእ​ርሱ ፍጹ​ማን ሁኑ፤ እርሱ ለአ​ለ​ቅ​ነት ሁሉና ለሥ​ል​ጣን ሁሉ ራስ ነውና። የኀ​ጢ​አ​ትን ሰው​ነት ሸለ​ፈት በመ​ግ​ፈፍ በክ​ር​ስ​ቶስ መገ​ረዝ በሰው እጅ የአ​ል​ተ​ደ​ረገ መገ​ረ​ዝን በእ​ርሱ ሆና​ችሁ ተገ​ረ​ዛ​ችሁ። በጥ​ም​ቀ​ትም ከእ​ርሱ ጋር ተቀ​ብ​ራ​ች​ኋል፤ በእ​ር​ስ​ዋም ከሙ​ታን ለይቶ ባስ​ነ​ሣው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ረዳ​ት​ነ​ትና በሃ​ይ​ማ​ኖት ከእ​ርሱ ጋር ተነ​ሥ​ታ​ች​ኋል። እና​ን​ተም በኀ​ጢ​አ​ታ​ች​ሁና ሥጋ​ች​ሁን ባለ​መ​ገ​ረዝ ሙታን ነበ​ራ​ች​ሁና፥ ከእ​ርሱ ጋር ሕያ​ዋን አደ​ረ​ጋ​ችሁ፤ ኀጢ​አ​ታ​ች​ሁ​ንም ሁሉ ይቅር አላ​ችሁ። ከባ​ላ​ጋ​ራ​ችን የተ​ነሣ በት​እ​ዛዝ የተ​ጻ​ፈ​ውን የዕ​ዳ​ች​ንን ደብ​ዳቤ ደመ​ሰ​ሰ​ልን፤ ከመ​ካ​ከ​ላ​ች​ንም አራ​ቀው፤ በመ​ስ​ቀ​ሉም ቸነ​ከ​ረው። አለ​ቆ​ች​ንና ገዢ​ዎ​ችን በመ​ግ​ፈፉ በግ​ልጥ አሳ​ያ​ቸው፤ ራቁ​ቱን በመ​ሆ​ኑም አሳ​ፈ​ራ​ቸው። እን​ግ​ዲህ በመ​ብ​ልም ቢሆን፥ በመ​ጠ​ጥም ቢሆን፥ በልዩ ልዩ በዓ​ላ​ትም ቢሆን፥ በመ​ባ​ቻም ቢሆን፥ በሰ​ን​በ​ትም ቢሆን የሚ​ነ​ቅ​ፋ​ችሁ እን​ዳ​ይ​ኖር ተጠ​ን​ቀቁ። ይህ ሁሉ ይመጣ ዘንድ ላለው ጥላ ነውና። አካሉ ግን የክ​ር​ስ​ቶስ ነው። በመ​ታ​ለ​ልና ራስን ዝቅ በማ​ድ​ረግ ለመ​ላ​እ​ክት አም​ልኮ ትታ​ዘዙ ዘንድ ወድዶ፥ በአ​ላ​የ​ውም በከ​ንቱ የሥ​ጋው ምክር እየ​ተ​መካ የሚ​ያ​ሰ​ን​ፋ​ችሁ አይ​ኑር። ሥጋ ሁሉ ጸንቶ በሚ​ኖ​ር​በት፥ በሥ​ርና በጅ​ማ​ትም በሚ​ስ​ማ​ማ​በት፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሚ​ያ​ድ​ግ​በ​ትና በሚ​ጸ​ና​በት፥ በሚ​ሞ​ላ​በ​ትም በራስ አይ​ጸ​ናም።