የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ አሞጽ 7

7
ራእይ ስለ አን​በጣ
1ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ አሳ​የኝ፤ እነ​ሆም ከም​ሥ​ራቅ አን​በጣ ይመ​ጣል፤ አን​ዱም ኵብ​ኵባ ንጉሡ ጎግ ነበረ።#ዕብ. “የኋ​ለ​ኛው ሣር በሚ​በ​ቅ​ል​በት መጀ​መ​ሪያ ላይ አን​በ​ጣን ፈጠረ ፤ እነ​ሆም ከን​ጉሡ አጨዳ በኋላ የበ​ቀለ የገቦ ነበረ” ይላል። 2የም​ድ​ሩ​ንም ሣር በልቶ ይጨ​ር​ሳል፤ እኔም፥ “ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ! ይቅር እን​ድ​ትል እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ፤ ያዕ​ቆ​ብን ማን ያነ​ሣ​ዋል? ጥቂት ነውና” አልሁ። 3እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ​ዚህ ነገር ራራ፤ “ይህ አይ​ሆ​ንም፤” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።
ራእይ ስለ እሳት
4ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አሳ​የኝ፤ እነ​ሆም ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለመ​ፍ​ረድ በቃሉ እሳ​ትን ጠራ፤ እር​ስ​ዋም ታላ​ቁን ቀላ​ይና ምድ​ርን በላች። 5እኔም፥ “ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ! እን​ድ​ት​ተው እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ፤ ያዕ​ቆ​ብን ማን ያነ​ሣ​ዋል? ጥቂት ነውና” አልሁ። 6እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ​ዚህ ነገር ራራ፤ “ይህ ደግሞ አይ​ሆ​ንም፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።
ነቢዩ ስለ ቱንቢ ያየው ራእይ
7ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ አሳ​የኝ፤ እነ​ሆም አንድ ሰው#ዕብ. “ጌታ ቱንቢ ይዞ ...” ይላል። በቱ​ንቢ በተ​ሠራ ቅጥር ላይ ቆሞ ነበር፤ በእ​ጁም ቱንቢ ነበር። 8እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “አሞጽ ሆይ! የም​ታ​የው ምን​ድን ነው?” አለኝ። እኔም፥ “ቱንቢ ነው” አልሁ። ጌታም፥ “እነሆ! በሕ​ዝቤ በእ​ስ​ራ​ኤል መካ​ከል ቱንቢ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ ደግሞ ይቅር አል​ላ​ቸ​ውም። 9መሳ​ቂያ የሆኑ የኮ​ረ​ብ​ታው መስ​ገ​ጃ​ዎች ይፈ​ር​ሳሉ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም መቅ​ደ​ሶች ባድማ ይሆ​ናሉ፤ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓ​ምም ቤት ላይ በሰ​ይፍ እነ​ሣ​ለሁ” አለ።
አሞ​ጽና አሜ​ስ​ያስ
10የቤ​ቴ​ልም ካህን አሜ​ስ​ያስ ወደ እስ​ራ​ኤል ንጉሥ ወደ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ልኮ፥ “አሞጽ በእ​ስ​ራ​ኤል ቤት መካ​ከል ዐም​ፆ​ብ​ሃል፤ ምድ​ሪ​ቱም ቃሉን ሁሉ ልት​ሸ​ከም አት​ች​ልም” አለ። 11አሞጽ፥ “ኢዮ​ር​ብ​ዓም በሰ​ይፍ ይሞ​ታል፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ከሀ​ገሩ ተማ​ርኮ ይሄ​ዳል” ብሎ​አ​ልና። 12አሜ​ስ​ያ​ስም አሞ​ጽን፥ “ባለ ራእዩ ሆይ! ሂድ፤ ወደ ይሁዳ ምድር ሽሽ፤ በዚ​ያም ተቀ​መጥ፥#ዕብ. “እን​ጀ​ራን ብላ” ይላል። በዚ​ያም ትን​ቢ​ትን ተና​ገር፤ 13ነገር ግን ቤቴል የን​ጉሥ መቅ​ደ​ስና የመ​ን​ግ​ሥት ቤት ናትና ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ በዚህ ደግሞ ትን​ቢት አት​ና​ገር” አለው።
14አሞ​ጽም መልሶ አሜ​ስ​ያ​ስን አለው፥ “እኔ ላም ጠባ​ቂና በለስ ለቃሚ ነኝ እንጂ ነቢይ ወይም የነ​ቢይ ልጅ አይ​ደ​ለ​ሁም፤ 15እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጎ​ቹን ከመ​ከ​ተል ወሰ​ደኝ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ ሂድ፥ ለሕ​ዝቤ ለእ​ስ​ራ​ኤል ትን​ቢት ተና​ገር አለኝ። 16አሁ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስማ፤ አንተ፦ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ትን​ቢት አት​ና​ገር፥ የያ​ዕ​ቆ​ብ​ንም ቤት አት​ዘ​ብ​ዝ​ባ​ቸው ብለ​ሃል። 17ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ሚስ​ትህ በከ​ተ​ማ​ይቱ ውስጥ አመ​ን​ዝራ ትሆ​ና​ለች፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ች​ህም በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃሉ፤ ምድ​ር​ህም በገ​መድ ትከ​ፈ​ላ​ለች፤ አን​ተም በረ​ከ​ሰች ምድር ትሞ​ታ​ለህ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ከም​ድሩ ተማ​ርኮ ይሄ​ዳል።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ