የሐ​ዋ​ር​ያት ሥራ 7:9-16

የሐ​ዋ​ር​ያት ሥራ 7:9-16 አማ2000

“የቀ​ደሙ አባ​ቶ​ችም በዮ​ሴፍ ላይ ቀን​ተው ወደ ግብፅ ሀገር ሸጡት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ከእ​ርሱ ጋር ነበረ። ከመ​ከ​ራ​ውም ሁሉ አዳ​ነው፤ በግ​ብፅ ንጉሥ በፈ​ር​ዖን ፊትም ሞገ​ስ​ንና ጥበ​ብን ሰጠው፤ በግ​ብ​ፅና በቤቱ ሁሉ ላይ ቢት​ወ​ደድ አድ​ርጎ ሾመው። በግ​ብ​ፅና በከ​ነ​ዓን ሀገር ሁሉ ረኃ​ብና ታላቅ ጭንቅ መጣ፤ አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም የሚ​በ​ሉት አጡ። ያዕ​ቆ​ብም በግ​ብፅ ሀገር እህል እን​ዳለ ሰማ፤ አባ​ቶ​ቻ​ች​ን​ንም አስ​ቀ​ድሞ ላካ​ቸው። ወደ ግብ​ፅም እንደ ገና በተ​መ​ለሱ ጊዜ ወን​ድ​ሞቹ ዮሴ​ፍን ዐወ​ቁት፤ ፈር​ዖ​ንም የዮ​ሴ​ፍን ዘመ​ዶች ዐወ​ቃ​ቸው። ዮሴ​ፍም አባ​ቱን ያዕ​ቆ​ብ​ንና ዘመ​ዶ​ቹን ሁሉ እን​ዲ​ጠ​ሩ​አ​ቸው ላከ፤ ቍጥ​ራ​ቸ​ውም ሰባ አም​ስት ነፍስ ነበር። “ያዕ​ቆ​ብም ወደ ግብፅ ወረደ፥ እር​ሱም አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም ሞቱ። ወደ ሴኬ​ምም አፍ​ል​ሰው አብ​ር​ሃም ከሴ​ኬም አባት ከኤ​ሞር ልጆች በገ​ን​ዘቡ በገ​ዛው መቃ​ብር ቀበ​ሩ​ዋ​ቸው።