የሐ​ዋ​ር​ያት ሥራ 7:57-60

የሐ​ዋ​ር​ያት ሥራ 7:57-60 አማ2000

እነ​ር​ሱም በታ​ላቅ ቃል ጮኹ፤ ጆሮ​አ​ቸ​ው​ንም ደፈኑ፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ተነ​ሥ​ተው ከበ​ቡት። ከከ​ተ​ማም ወደ ውጭ ጐት​ተው አው​ጥ​ተው ወገ​ሩት፤ የሚ​ወ​ግ​ሩት ሰዎ​ችም ልብ​ሳ​ቸ​ውን ሳውል በሚ​ባል ጐል​ማሳ እግር አጠ​ገብ አስ​ቀ​መጡ። እስ​ጢ​ፋ​ኖ​ስም፥ “ጌታዬ ኢየ​ሱስ ሆይ፥ ነፍ​ሴን ተቀ​በል” እያለ ሲጸ​ልይ ይወ​ግ​ሩት ነበር። በጕ​ል​በ​ቱም ተን​በ​ር​ክኮ፥ “አቤቱ፥ ይህን ኀጢ​አት አት​ቍ​ጠ​ር​ባ​ቸው” ብሎ በታ​ላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህ​ንም ብሎ ሞተ፤ ሳው​ልም በእ​ስ​ጢ​ፋ​ኖስ ሞት ተባ​ባሪ ነበር።