የሐ​ዋ​ር​ያት ሥራ 4:31-33

የሐ​ዋ​ር​ያት ሥራ 4:31-33 አማ2000

ሲጸ​ል​ዩም በአ​ን​ድ​ነት ተሰ​ብ​ስ​በው የነ​በ​ሩ​በት ቦታ ተና​ወጠ፤ በሁ​ሉም ላይ መን​ፈስ ቅዱስ መላ​ባ​ቸ​ውና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል በግ​ልጥ አስ​ተ​ማሩ። ያመ​ኑ​ትም ሁሉ አንድ ልብና አን​ዲት ነፍስ ሆነው ይኖሩ ነበር፤ በው​ስ​ጣ​ቸ​ውም የሁሉ ገን​ዘብ በአ​ን​ድ​ነት ነበር እንጂ “ይህ የእኔ ገን​ዘብ ነው” የሚል አል​ነ​በ​ረም። ሐዋ​ር​ያ​ትም የጌ​ታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ትን​ሣኤ በታ​ላቅ ኀይል ይመ​ሰ​ክሩ ነበር፤ በሕ​ዝ​ቡም ዘንድ ታላቅ ጸጋ ነበ​ራ​ቸው።