የሐ​ዋ​ር​ያት ሥራ 22:1-16

የሐ​ዋ​ር​ያት ሥራ 22:1-16 አማ2000

“እና​ንተ ወን​ድ​ሞ​ችና አባ​ቶች፥ አሁን በፊ​ታ​ችሁ የም​ና​ገ​ረ​ውን ስሙኝ።” በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ቋንቋ እን​ደ​ሚ​ነ​ግ​ራ​ቸው በሰ​ሙም ጊዜ ጸጥ ብለው አዳ​መ​ጡት። ጳው​ሎ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እኔ አይ​ሁ​ዳዊ ሰው ነኝ፤ የቂ​ል​ቅያ ክፍል በም​ት​ሆን በጠ​ር​ሴስ ከተማ ተወ​ለ​ድሁ፤ በዚ​ችም ከተማ ከገ​ማ​ል​ያል እግር ሥር ሆኜ አደ​ግሁ፤ የአ​ባ​ቶ​ች​ንም ሕግ ተማ​ርሁ፤ እና​ንተ ሁላ​ችሁ ዛሬ እን​ደ​ም​ታ​ደ​ር​ጉ​ትም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀና​ተኛ ነበ​ርሁ። ይህን ትም​ህ​ርት የሚ​ከ​ተሉ ወን​ዶ​ች​ንም ሴቶ​ች​ንም እያ​ሰ​ርሁ ወደ ወህኒ ቤት አሳ​ልፌ በመ​ስ​ጠት እስከ ሞት ድረስ አሳ​ደ​ድ​ኋ​ቸው። እን​ዲ​ቀ​ጡም ከዚያ ያሉ​ትን አስሬ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም አመ​ጣ​ቸው ዘንድ በደ​ማ​ስቆ ወደ አሉ ወን​ድ​ሞች እን​ድ​ሄድ ከእ​ነ​ርሱ ዘንድ የሥ​ል​ጣን ደብ​ዳቤ የተ​ቀ​በ​ል​ኋ​ቸው ሊቀ ካህ​ና​ቱና መም​ህ​ራን ሁሉ ይመ​ሰ​ክ​ራሉ። “ከዚህ በኋላ ወደ ደማ​ስቆ ስሄድ ቀትር በሆነ ጊዜ ወደ ከተ​ማው አቅ​ራ​ቢያ ደርሼ ሳለሁ ድን​ገት ታላቅ መብ​ረቅ ከሰ​ማይ በእኔ ላይ አን​ፀ​ባ​ረቀ። በም​ድር ላይም ወደ​ቅሁ ‘ሳውል ሳውል ለምን ታሳ​ድ​ደ​ኛ​ለህ?’ የሚል ቃል​ንም ሰማሁ። እኔም መልሼ፦ ‘አቤቱ፥ አንተ ማነህ?’ አል​ሁት፤ እር​ሱም፦ ‘አንተ የም​ታ​ሳ​ድ​ደኝ የና​ዝ​ሬቱ ኢየ​ሱስ ነኝ’ አለኝ። አብ​ረ​ውኝ የነ​በ​ሩ​ትም መብ​ረ​ቁን አይ​ተው ደነ​ገጡ፤ ነገር ግን ይና​ገ​ረኝ የነ​በ​ረ​ውን ቃል አል​ሰ​ሙም። ‘አቤቱ፥ ጌታዬ ምን ላድ​ርግ?’ አልሁ፤ ጌታም፦ ‘ተነ​ሥና ወደ ደማ​ስቆ ሂድ፤ ልታ​ደ​ር​ገው የሚ​ገ​ባ​ህ​ንም ሁሉ በዚያ ይነ​ግ​ሩ​ሃል’ አለኝ። ከዚ​ያም በኋላ ከመ​ብ​ረቁ ነፀ​ብ​ራቅ የተ​ነሣ ዐይ​ኔን ታወ​ርሁ፤ አብ​ረ​ውኝ የነ​በ​ሩ​ትም እየ​መ​ሩኝ ወደ ደማ​ስቆ ደረ​ስሁ። “እንደ ሕጉም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ ሐና​ንያ የሚ​ባል አንድ ሰው ነበረ፤ በደ​ማ​ስ​ቆም የሚ​ኖሩ አይ​ሁድ ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ኑት ነበር። ወደ እኔም መጥቶ በፊቴ ቆመና፦ ‘ወን​ድሜ ሳውል ሆይ፥ እይ’ አለ፤ ያን​ጊ​ዜም ወደ እርሱ አየሁ። እን​ዲ​ህም አለኝ፤ ‘የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን አም​ላክ ፈቃ​ዱን ታው​ቅና ጽድ​ቁ​ንም ታይ ዘንድ፥ ቃሉ​ንም ከአ​ን​ደ​በቱ ትሰማ ዘንድ መረ​ጠህ። በሕ​ዝ​ብም ሁሉ ዘንድ ባየ​ኸ​ውና በሰ​ማ​ኸው ምስ​ክር ትሆ​ነ​ዋ​ለህ። አሁ​ንም የም​ታ​ደ​ር​ገ​ውን ልን​ገ​ርህ፦ ተነሥ ስሙን እየ​ጠ​ራህ ተጠ​መቅ፤ ከኀ​ጢ​አ​ት​ህም ታጠብ።’