የሐ​ዋ​ር​ያት ሥራ 10:34-38

የሐ​ዋ​ር​ያት ሥራ 10:34-38 አማ2000

ጴጥ​ሮ​ስም አፉን ከፈ​ተና እን​ዲህ አለ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሰው ፊት እን​ደ​ማ​ያ​ዳላ በእ​ው​ነት አየሁ። ነገር ግን በሕ​ዝብ ሁሉ ዘንድ እር​ሱን የሚ​ፈ​ራና እው​ነ​ትን የሚ​ያ​ደ​ርግ በእ​ርሱ ዘንድ የተ​ወ​ደደ ነው። ቃሉን ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ላከ፤ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም ሰላ​ምን ነገ​ራ​ቸው፤ እር​ሱም የሁሉ ገዢ ነው። ዮሐ​ንስ ከሰ​በ​ከው ጥም​ቀት በኋላ ከገ​ሊላ ጀምሮ በይ​ሁዳ የሆ​ነ​ውን ነገር ሁሉ እና​ንተ ራሳ​ችሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ። ስለ ናዝ​ሬቱ ስለ ኢየ​ሱስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ን​ፈስ ቅዱስ በኀ​ይ​ልም እንደ ቀባው፥ እየ​ዞ​ረም መል​ካም እንደ አደ​ረገ፥ ሰይ​ጣን ያሸ​ነ​ፋ​ቸ​ው​ንም እንደ ፈወሰ ታው​ቃ​ላ​ችሁ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ርሱ ጋር ነበ​ርና።