ጴጥሮስም አፉን ከፈተና እንዲህ አለ፥ “እግዚአብሔር ለሰው ፊት እንደማያዳላ በእውነት አየሁ። ነገር ግን በሕዝብ ሁሉ ዘንድ እርሱን የሚፈራና እውነትን የሚያደርግ በእርሱ ዘንድ የተወደደ ነው። ቃሉን ለእስራኤል ልጆች ላከ፤ በኢየሱስ ክርስቶስም ሰላምን ነገራቸው፤ እርሱም የሁሉ ገዢ ነው። ዮሐንስ ከሰበከው ጥምቀት በኋላ ከገሊላ ጀምሮ በይሁዳ የሆነውን ነገር ሁሉ እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ። ስለ ናዝሬቱ ስለ ኢየሱስ እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ በኀይልም እንደ ቀባው፥ እየዞረም መልካም እንደ አደረገ፥ ሰይጣን ያሸነፋቸውንም እንደ ፈወሰ ታውቃላችሁ። እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበርና።
የሐዋርያት ሥራ 10 ያንብቡ
ያዳምጡ የሐዋርያት ሥራ 10
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: የሐዋርያት ሥራ 10:34-38
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች