የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 2 4:1-12

ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 2 4:1-12 አማ2000

ስለ​ዚህ እንደ ቸር​ነቱ የሰ​ጠን ይህ መል​እ​ክት አለ​ንና አን​ሰ​ለ​ችም። ነገር ግን በስ​ውር የሚ​ሠ​ራ​ውን አሳ​ፋሪ ሥራ እን​ተ​ወው፤ በተ​ን​ኰ​ልም አን​መ​ላ​ለስ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል በው​ሸት አን​ቀ​ላ​ቅል፤ ለሰ​ውም ሁሉ አር​አያ ስለ መሆን እው​ነ​ትን ገል​ጠን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ራሳ​ች​ንን እና​ጽና። ወን​ጌ​ላ​ችን የተ​ሰ​ወረ ቢሆ​ንም እንኳ፥ የተ​ሰ​ወ​ረ​ባ​ቸው ለሚ​ጠ​ፉት ነው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​መ​ስ​ለው የክ​ር​ስ​ቶስ የክ​ብሩ ወን​ጌል ብር​ሃን እን​ዳ​ያ​በ​ራ​ላ​ቸው የዚህ ዓለም አም​ላክ ልባ​ቸ​ውን አሳ​ው​ሮ​አ​ልና። ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ጌታ እንደ ሆነ እን​ሰ​ብ​ካ​ለን እንጂ ራሳ​ች​ንን የም​ን​ሰ​ብክ አይ​ደ​ለም፤ ስለ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም ብለን ራሳ​ች​ንን ለእ​ና​ንተ አስ​ገ​ዛን። በጨ​ለማ ውስጥ “ብር​ሃን ይብራ” ያለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ፊት የክ​ብ​ሩን ዕው​ቀት ብር​ሃን በል​ባ​ችን አብ​ር​ቶ​ል​ና​ልና። ነገር ግን ከእኛ ያይ​ደለ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ገኘ ታላቅ ኀይል ይሆን ዘንድ በሸ​ክላ ዕቃ ውስጥ ይህ መዝ​ገብ አለን። በሁሉ መከ​ራን እን​ቀ​በ​ላ​ለን፤ ነገር ግን አን​ጨ​ነ​ቅም፤ እን​ና​ቃ​ለን፥ ነገር ግን ተስፋ አን​ቈ​ር​ጥም። እን​ሰ​ደ​ዳ​ለን፤ ነገር ግን አን​ጣ​ልም፤ እን​ወ​ድ​ቃ​ለን፤ ነገር ግን አን​ጠ​ፋም። የክ​ር​ስ​ቶስ ሕይ​ወቱ በዚህ በሟች ሰው​ነ​ታ​ችን ላይ ይገ​ለጥ ዘንድ፥ ዘወ​ትር የክ​ር​ስ​ቶ​ስን ሞት በሥ​ጋ​ችን እን​ሸ​ከ​ማ​ለን። በሕ​ይ​ወት የም​ን​ኖር እኛም በሟች ሰው​ነ​ታ​ችን ላይ የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ሕይ​ወቱ ይገ​ለጥ ዘንድ፥ ዘወ​ትር ስለ ኢየ​ሱስ ክስ​ር​ቶስ ብለን ተላ​ል​ፈን ለሞት እን​ሰ​ጣ​ለን። ስለ​ዚ​ህም ሞት በእኛ ላይ፥ ሕይ​ወ​ትም በእ​ና​ንተ ላይ ይሠ​ራል።