መጽ​ሐፈ ዜና መዋ​ዕል ካልእ 7

7
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ቅዳሴ መከ​በር
(1ነገ. 8፥62-66)
1ሰሎ​ሞ​ንም ይህን ጸሎት በፈ​ጸመ ጊዜ እሳት ከሰ​ማይ ወርዶ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን ቍር​ባ​ንና መሥ​ዋ​ዕ​ቱን ሁሉ በላ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ቤቱን ሞላ። 2የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ሞል​ቶት ነበ​ርና ካህ​ናቱ በዚ​ያች ዕለት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት መግ​ባት አል​ቻ​ሉም። 3የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ እሳቱ ሲወ​ርድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር በቤቱ ላይ ሲሆን ያዩ ነበር፤ ድን​ጋይ በተ​ነ​ጠ​ፈ​በ​ትም ምድር በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ተደ​ፍ​ተው ሰገዱ፥ “እርሱ ቸር ነውና፥ ምሕ​ረ​ቱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና” እያሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገኑ።
4ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሕዝብ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ርቡ ነበር። 5በዚ​ያ​ችም ዕለት ንጉሡ ሰሎ​ሞን ሃያ ሁለት ሺህ በሬ​ዎ​ች​ንና መቶ ሃያ ሺህ በጎ​ችን ሠዋ። እን​ዲሁ ንጉ​ሡና ሕዝቡ ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ቅዳሴ አከ​በሩ። 6ካህ​ና​ቱም በየ​ሥ​ር​ዐ​ታ​ቸው ሌዋ​ው​ያ​ኑም ደግሞ፥ “ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ” የሚ​ለ​ውን የዳ​ዊ​ትን መዝ​ሙር እየ​ዘ​መሩ፥ ንጉሡ ዳዊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለማ​መ​ስ​ገን የሠ​ራ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የዜማ ዕቃ ይዘው ቆመው ነበር፤ ካህ​ና​ቱም በፊ​ታ​ቸው መለ​ከት ይነፉ ነበር፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ቆመው ነበር። 7ሰሎ​ሞ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ፊት የነ​በ​ረ​ውን የአ​ደ​ባ​ባ​ዩን ውስጥ ቀደሰ፤ ሰሎ​ሞ​ንም የሠ​ራው የናስ መሠ​ዊያ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የእ​ህ​ሉን ቍር​ባን፥ ስቡ​ንም መያዝ አል​ቻ​ለ​ምና የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የደ​ኅ​ን​ነ​ቱ​ንም መሥ​ዋ​ዕት፥ ስብ በዚያ አቀ​ረበ።
8ሰሎ​ሞ​ንም፥ ከእ​ር​ሱም ጋር እጅግ ታላቅ ጉባኤ የሆኑ ከኤ​ማት መግ​ቢያ ጀምሮ እስከ ግብፅ ወንዝ ድረስ ያሉ እስ​ራ​ኤል ሁሉ፥ በዚያ ጊዜ ሰባት ቀን በዓል አደ​ረጉ። 9መሠ​ዊ​ያ​ው​ንም ቀድሶ፥ ሰባት ቀን በዓል አድ​ርጎ ነበ​ርና በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀን የፍ​ጻሜ በዓል አደ​ረገ። 10በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ወር በሃያ ሦስ​ተ​ኛው ቀን ሕዝ​ቡን ወደ ድን​ኳ​ና​ቸው አሰ​ና​በተ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዳ​ዊ​ትና ለሰ​ሎ​ሞን፥ ለሕ​ዝ​ቡም ለእ​ስ​ራ​ኤል ስላ​ደ​ረ​ገው ቸር​ነት በል​ባ​ቸው ደስ ብሎ​አ​ቸው ሄዱ።
11ሰሎ​ሞ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤትና የን​ጉ​ሡን ቤት፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤትና በራሱ ቤት ይሠ​ራው ዘንድ በልቡ ያሰ​በ​ውን ሁሉ ጨረሰ፤ አከ​ና​ወ​ነም። 12እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሰ​ሎ​ሞን በሌ​ሊት ተገ​ልጦ እን​ዲህ አለው፥ “ ጸሎ​ት​ህን ሰም​ቻ​ለሁ፤ ይህ​ንም ስፍራ ለራሴ ለመ​ሥ​ዋ​ዕት ቤት መር​ጫ​ለሁ። 13ዝናብ እን​ዳ​ይ​ወ​ርድ ሰማ​ያ​ቱን ብዘጋ፥ ወይም የሚ​ያ​ፈ​ራ​ውን እን​ጨት ሁሉ ይበላ ዘንድ አን​በ​ጣን ባዝ​ዘው፥ ወይም በሕ​ዝቤ ላይ ቸነ​ፈር ብሰ​ድድ፥ 14በስሜ የተ​ጠ​ሩት ሕዝቤ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውን አዋ​ር​ደው ቢጸ​ልዩ፥ ፊቴ​ንም ቢፈ​ልጉ፥ ከክፉ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውም ቢመ​ለሱ፥ በሰ​ማይ ሆኜ እሰ​ማ​ለሁ፥ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ይቅር እላ​ለሁ፤ ምድ​ራ​ቸ​ው​ንም እፈ​ው​ሳ​ለሁ። 15አሁ​ንም በዚህ ስፍራ ለሚ​ጸ​ለይ ጸሎት ዐይ​ኖች ይገ​ለ​ጣሉ፤ ጆሮ​ዎ​ችም ያዳ​ም​ጣሉ። 16አሁ​ንም ስሜ ለዘ​ለ​ዓ​ለም በዚያ ይኖር ዘንድ ይህን ቤት መር​ጫ​ለሁ፤ ቀድ​ሻ​ለ​ሁም፤ ዐይ​ኖ​ችና ልቤም ዘወ​ትር በዚያ ይሆ​ናሉ። 17አን​ተም ደግሞ አባ​ትህ ዳዊት እንደ ሄደ በፊቴ ብት​ሄድ፥ እን​ዳ​ዘ​ዝ​ሁም ሁሉ ብታ​ደ​ርግ፥ ሥር​ዐ​ቴ​ንና ፍር​ዴ​ንም ብት​ጠ​ብቅ፥ 18ከአ​ባ​ትህ ከዳ​ዊት ጋር፦ ‘በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አለቃ የሚ​ሆን ከዘ​ርህ አይ​ታ​ጣም’ ብዬ ቃል ኪዳን እን​ዳ​ደ​ረ​ግሁ የመ​ን​ግ​ሥ​ት​ህን ዙፋን አጸ​ና​ለሁ።
19“እና​ንተ ግን ብት​መ​ለሱ፥ የሰ​ጠ​ኋ​ች​ሁን ሥር​ዐ​ቴ​ንና ትእ​ዛ​ዜን ብት​ተዉ፥ ሄዳ​ች​ሁም ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት ብታ​መ​ልኩ፥ ብት​ሰ​ግ​ዱ​ላ​ቸ​ውም፥ 20እኔም ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ከሰ​ጠ​ኋ​ቸው ምድር እነ​ቅ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ለስ​ሜም የቀ​ደ​ስ​ሁ​ትን ይህን ቤት ከፊቴ እጥ​ለ​ዋ​ለሁ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም ሁሉ መካ​ከል ምሳ​ሌና ተረት አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ። 21ከፍ ከፍ ብሎ የነ​በ​ረ​ው​ንም ይህን ቤት እያየ በዚያ የሚ​ያ​ልፍ መን​ገ​ደኛ ሁሉ፦ ‘እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚህ ሀገ​ርና በዚህ ቤት ስለ ምን እን​ዲህ አደ​ረገ?’ ብሎ ይደ​ነ​ቃል። 22መል​ሰ​ውም፦ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ቸ​ውን ያባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትተው ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት ስለ ተከ​ተሉ፥ ስለ ሰገ​ዱ​ላ​ቸ​ውም፥ ስለ አመ​ለ​ኩ​አ​ቸ​ውም፥ ስለ አገ​ለ​ገ​ሏ​ቸ​ውም፥ ስለ​ዚህ ይህን ክፉ ነገር ሁሉ አመ​ጣ​ባ​ቸው” ይላሉ።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ