የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ዜና መዋ​ዕል ካልእ 26

26
የይ​ሁዳ ንጉሥ የዖ​ዝ​ያን ዘመነ መን​ግ​ሥት
(2ነገ. 14፥21-2215፥1-7)
1የይ​ሁ​ዳም ሕዝብ ሁሉ የዐ​ሥራ ስድ​ስት ዓመት ጐል​ማሳ የነ​በ​ረ​ውን ዖዝ​ያ​ንን ወስ​ደው በአ​ባቱ በአ​ሜ​ስ​ያስ ፋንታ አነ​ገ​ሡት። 2ንጉሥ አባ​ቱም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር ከአ​ን​ቀ​ላፋ በኋላ ዖዝ​ያን ኤላ​ትን ሠራ፤ ወደ ይሁ​ዳም መለ​ሳት። 3ዖዝ​ያ​ንም መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የዐ​ሥራ ስድ​ስት ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም አምሳ ሁለት ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም ኢዮ​ኮ​ል​ያስ የተ​ባ​ለች የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሴት ነበ​ረች። 4አባ​ቱም አሜ​ስ​ያስ እን​ዳ​ደ​ረ​ገው ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቅን ነገ​ርን አደ​ረገ። 5እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም መፍ​ራት ባስ​ተ​ማረ በዘ​ካ​ር​ያስ ዘመን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይፈ​ልግ ዘንድ ልብ አደ​ረገ፤ በዘ​መ​ኑም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈለገ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ነገ​ሩን አከ​ና​ወ​ነ​ለት።
6ወጥ​ቶም ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጋር ተዋጋ፤ የጌ​ትን ቅጥር፥ የኢ​ያ​ቢ​ስ​ንም ቅጥር፥ የአ​ዛ​ጦ​ን​ንም ቅጥር አፈ​ረሰ፤ በአ​ዛ​ጦ​ንና በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ሀገር ከተ​ሞ​ችን ሠራ። 7እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንና በዓ​ለት ላይ በሚ​ኖሩ ዓረ​ባ​ው​ያን፥ በም​ዕ​ዑ​ና​ው​ያ​ንም ላይ አጸ​ናው። 8አሞ​ና​ው​ያ​ንም ለዖ​ዝ​ያን ገበሩ፤ እጅ​ግም በር​ትቶ ነበ​ርና ዝናው እስከ ግብፅ መግ​ቢያ ድረስ ተሰማ። 9ዖዝ​ያ​ንም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በማ​ዕ​ዘኑ በርና በሸ​ለ​ቆው በር፥ ቅጥ​ሩም በዞ​ረ​በት ማዕ​ዘን አጠ​ገብ ግን​ቦ​ችን ሠርቶ መሸ​ጋ​ቸው። 10በም​ድረ በዳ​ውም ግን​ቦ​ችን ሠራ፤ ብዙ ጕድ​ጓ​ድም ማሰ፤ በቆ​ላ​ውና በደ​ጋው ብዙ እን​ስ​ሶች ነበ​ሩ​ትና፤ ደግ​ሞም እርሻ ይወ​ድድ ነበ​ርና በተ​ራ​ራ​ማ​ውና በፍ​ሬ​ያ​ማው ስፍራ አራ​ሾ​ችና የወ​ይን አት​ክ​ል​ተ​ኞች ነበ​ሩት። 11ደግ​ሞም ለዖ​ዝ​ያን የሰ​ልፍ ሠራ​ዊት ነበ​ሩት፤ በን​ጉሡ አለቃ በሐ​ና​ንያ ትእ​ዛዝ፥ በአ​ለ​ቃው በመ​ዕ​ሤ​ያና በጸ​ሓ​ፊው በኢ​ዮ​ሔል እጅ እንደ ተቈ​ጠሩ ወደ ሰልፍ በየ​ቍ​ጥ​ራ​ቸው ይወጡ ነበር። 12የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤቶች አለ​ቆች በሰ​ልፍ ጽኑ​ዓ​ንና ኀያ​ላን የሆኑ ሁሉ ቍጥ​ራ​ቸው ሁለት ሺህ ስድ​ስት መቶ ነበረ። 13ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ወደ ሰልፍ የሚ​ወጡ ሦስት መቶ ሰባት ሺህ አም​ስት መቶ ሠራ​ዊት ነበሩ፤ እነ​ዚ​ህም ንጉ​ሡን በጠ​ላቱ ላይ የሚ​ያ​ግዙ፥ በታ​ላቅ ኀይል ወደ ሰልፍ የሚ​ወጡ ጽኑ​ዓን ነበሩ። 14ዖዝ​ያ​ንም ለጭ​ፍ​ራው ሁሉ ጋሻና ጦር፥ ራስ ቍርና ጥሩር፥ ቀስ​ትና የሚ​ወ​ነ​ጭ​ፉ​ትን ድን​ጋይ አዘ​ጋ​ጀ​ላ​ቸው። 15በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም በብ​ል​ሃ​ተ​ኞች እጅ የተ​ሠ​ሩ​ትን ፥ በግ​ን​ብና በቅ​ጥር ላይ የሚ​ኖ​ሩ​ትን፥ ፍላ​ጻና መርግ የሚ​ወ​ረ​ወ​ር​ባ​ቸ​ውን መሣ​ሪ​ያ​ዎች አደ​ረገ፤ እስ​ኪ​በ​ረ​ታም ድረስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በድ​ንቅ ረድ​ቶ​ታ​ልና የመ​ሣ​ሪ​ያ​ዎቹ ዝና#ዕብ. “ዝናው” ይላል። እስከ ሩቅ ድረስ ተሰማ።
16ነገር ግን በበ​ረታ ጊዜ ለጥ​ፋት ልቡ ታበየ፤ አም​ላ​ኩ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በደለ፤ በዕ​ጣን መሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ ያጥን ዘንድ ወደ መቅ​ደስ ገባ። 17ካህ​ኑም ዓዛ​ር​ያስ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ጽኑ​ዓን የነ​በሩ ሰማ​ንያ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ካህ​ናት ተከ​ት​ለው ገቡ። 18ንጉ​ሡ​ንም ዖዝ​ያ​ንን እየ​ተ​ቃ​ወሙ፥ “ዖዝ​ያን ሆይ፥ ዕጣን ማጠን ለተ​ቀ​ደ​ሱት ለአ​ሮን ልጆች ለካ​ህ​ናቱ ነው እንጂ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታጥን ዘንድ ለአ​ንተ አይ​ገ​ባ​ህም፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርቀ​ሃ​ልና ከመ​ቅ​ደሱ ውጣ፤ ይህም በአ​ም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዘንድ ለአ​ንተ ክብር አይ​ሆ​ን​ህም” አሉት። 19ዖዝ​ያ​ንም ተቈጣ፤ በመ​ቅ​ደ​ስም የሚ​ያ​ጥ​ን​በት ጥና በእጁ ነበረ፤ ካህ​ና​ቱ​ንም በተ​ቈጣ ጊዜ በካ​ህ​ናቱ ፊት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ውስጥ በዕ​ጣኑ መሠ​ዊያ አጠ​ገብ ሳለ በግ​ን​ባሩ ላይ ለምጽ ታየ። 20ታላቁ ካህን ዓዛ​ር​ያስ፥ ካህ​ና​ቱም ሁሉ ተመ​ለ​ከ​ቱት፤ እነ​ሆም፥ በግ​ን​ባሩ ላይ ለምጽ ነበረ፤ ፈጥ​ነ​ውም አባ​ረ​ሩት፤ እር​ሱም ደግሞ እግ​ዝ​አ​ብ​ሔር ቀሥ​ፎት ነበ​ርና ይወጣ ዘንድ ቸኰለ። 21ንጉ​ሡም ዖዝ​ያን እስ​ኪ​ሞት ድረስ ለም​ጻም ነበረ፤ ለም​ጻ​ምም ሆኖ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ርቆ​አ​ልና በተ​ለየ ቤት ይቀ​መጥ ነበር፤ ልጁም ኢዮ​አ​ታም በቤተ መን​ግ​ሥቱ ሆኖ በም​ድሩ ሕዝብ ላይ ይፈ​ርድ ነበር። 22የቀ​ሩ​ትም የፊ​ተ​ኞ​ቹና የኋ​ለ​ኞቹ የዖ​ዝ​ያን ነገ​ሮች በነ​ቢዩ በኢ​ሳ​ይ​ያስ መጽ​ሐፍ ተጽ​ፈ​ዋል። 23ዖዝ​ያ​ንም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ ለም​ጻም ነው ብለ​ዋ​ልና የነ​ገ​ሥ​ታቱ መቃ​ብር ባል​ሆነ እርሻ ውስጥ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ከአ​ባ​ቶቹ ጋር በነ​ገ​ሥ​ታቱ መቃ​ብር እርሻ ውስጥ ቀበ​ሩት” ይላል። ቀበ​ሩት፤ ልጁም ኢዮ​አ​ታም በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ