የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ተሰ​ሎ​ንቄ ሰዎች 1 5:5-11

ወደ ተሰ​ሎ​ንቄ ሰዎች 1 5:5-11 አማ2000

ሁላችሁ የብርሃን ልጆች የቀንም ልጆች ናችሁና፤ እኛ ከሌሊት ወይም ከጨለማ አይደለንም። እንግዲያስ እንንቃ በመጠንም እንኑር እንጂ እንደ ሌሎች አናንቀላፋ። የሚያንቀላፉ በሌሊት ያንቀላፋሉና፤ የሚሰክሩም በሌሊት ይሰክራሉና፤ እኛ ግን ከቀን ስለ ሆንን፥ የእምነትንና የፍቅርን ጥሩር የመዳንንም ተስፋ እንደ ራስ ቁር እየለበስን በመጠን እንኑር፤ እግዚአብሔር ለቍጣ አልመረጠንምና፤ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መዳንን ለማግኘት ነው እንጂ። የምንነቃም ብንሆን፥ የምናንቀላፋም ብንሆን፥ ከእርሱ ጋር አብረን በሕይወት እንኖር ዘንድ ስለ እኛ ሞተ። ስለዚህ እናንተ ደግሞ እንደምታደርጉ፥ እርስ በርሳችሁ ተመካከሩ፤ አንዱም አንዱም ሌላውን ያንጸው።