የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ቀዳ​ማዊ 17:41-50

መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ቀዳ​ማዊ 17:41-50 አማ2000

ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውም መጥቶ ወደ ዳዊት ቀረበ፤ ጋሻ ጃግ​ሬ​ውም በፊቱ ይሄድ ነበር። ጎል​ያ​ድም ዳዊ​ትን ትኩር ብሎ አየው፤ ቀይ ብላ​ቴና፥ መል​ኩም ያማረ ነበ​ረና ናቀው። ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውም ዳዊ​ትን፥ “በት​ርና ድን​ጋይ ይዘህ የም​ት​መ​ጣ​ብኝ እኔ ውሻ ነኝን?” አለው። ዳዊ​ትም፥ “የለም ከውሻ ትከ​ፋ​ለህ” አለው። ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውም ዳዊ​ትን በአ​ም​ላ​ኮቹ ረገ​መው። ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውም ዳዊ​ትን፥ “ወደ እኔ ና፤ ሥጋ​ህ​ንም ለሰ​ማይ ወፎ​ችና ለም​ድር አራ​ዊት እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ” አለው። ዳዊ​ትም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ዉን አለው፥ “አንተ ሰይ​ፍና ጦር፥ ጋሻም ይዘህ ትመ​ጣ​ብ​ኛ​ለህ፤ እኔ ግን ዛሬ በተ​ገ​ዳ​ደ​ር​ኸው በእ​ስ​ራ​ኤል ጭፍ​ሮች አም​ላክ ስም በሰ​ራ​ዊት ጌታ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም እመ​ጣ​ብ​ሃ​ለሁ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዛሬ አን​ተን በእጄ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣል፤ እመ​ታ​ህ​ማ​ለሁ፤ ራስ​ህ​ንም ከአ​ንተ እቈ​ር​ጠ​ዋ​ለሁ፤ ሬሳ​ህ​ንና የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ን​ንም ሠራ​ዊት ሬሶች ለሰ​ማይ ወፎ​ችና ለም​ድር አራ​ዊት ዛሬ እሰ​ጣ​ለሁ። ምድር ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር እን​ዳለ ያው​ቃሉ፤ ይህም ጉባኤ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ይ​ፍና በጦር የሚ​ያ​ድን እን​ዳ​ይ​ደለ ያው​ቃል። ሰልፉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነውና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እና​ን​ተን በእ​ጃ​ችን አሳ​ልፎ ይሰ​ጣል።” ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውም ተነ​ሥቶ ዳዊ​ትን ሊገ​ና​ኘው በቀ​ረበ ጊዜ ዳዊት ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ዉን ሊገ​ና​ኘው ወደ ሰልፉ ሮጠ። ዳዊ​ትም እጁን ወደ ኮሮ​ጆው አግ​ብቶ አንድ ድን​ጋይ ወሰደ፤ ወነ​ጨ​ፈ​ውም፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ው​ንም ግን​ባ​ሩን መታው፤ ድን​ጋ​ዩም ጥሩ​ሩን ዘልቆ በግ​ን​ባሩ ተቀ​ረ​ቀረ፤ እር​ሱም በም​ድር ላይ በፊቱ ተደፋ። ዳዊ​ትም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውን በወ​ን​ጭ​ፍና በድ​ን​ጋይ አሸ​ነ​ፈው፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ው​ንም መትቶ ገደለ ፤ በዳ​ዊ​ትም እጅ ሰይፍ አል​ነ​በ​ረም።

Free Reading Plans and Devotionals related to መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ቀዳ​ማዊ 17:41-50