መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ቀዳ​ማዊ 17:38-40

መጽ​ሐፈ ሳሙ​ኤል ቀዳ​ማዊ 17:38-40 አማ2000

ሳኦ​ልም ለዳ​ዊት ጥሩር አለ​በ​ሰው፤ በራ​ሱም ላይ የናስ ቍር ደፋ​ለት። ዳዊ​ት​ንም ሰይ​ፉን በል​ብሱ ላይ አስ​ታ​ጠ​ቀው፤ ዳዊ​ትም አን​ድና ሁለት ጊዜ ሲራ​መድ ደከመ። ዳዊ​ትም ሳኦ​ልን፥ “አለ​መ​ድ​ሁ​ምና በዚህ መሄድ አል​ች​ልም” አለው። ከላ​ዩም አወ​ለ​ቁ​ለት። ዳዊ​ትም በት​ሩን በእጁ ያዘ፤ ከወ​ን​ዝም አም​ስት ድብ​ል​ብል ድን​ጋ​ዮ​ችን መረጠ፤ በእ​ረኛ ኮሮ​ጆ​ውም በኪሱ ከተ​ታ​ቸው፤ ወን​ጭ​ፍም በእጁ ነበረ፤ ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውም ቀረበ።