የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ነገ​ሥት ቀዳ​ማዊ 8

8
የቃል ኪዳኑ ታቦት ወደ ቤተ መቅ​ደስ መግ​ባት
(2ዜ.መ. 5፥26፥2)
1ሰሎ​ሞ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤትና የራ​ሱን ቤተ መን​ግ​ሥት ሠርቶ ከፈ​ጸመ ከሃያ ዓመት በኋላ ያን​ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን ታቦት ከዳ​ዊት ከተማ ከጽ​ዮን ያወጡ ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና የነ​ገድ አለ​ቆ​ችን ሁሉ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ቤቶች መሳ​ፍ​ንት ንጉሡ ሰሎ​ሞን በጽ​ዮን ሰበ​ሰ​ባ​ቸው። 2ይኸ​ውም አታ​ሚን#ጥቅ​ምት። በሚ​ባል በሰ​ባ​ተ​ኛው ወር ነበር። 3ካህ​ና​ቱም ታቦ​ቷን አነሡ፤ 4የም​ስ​ክ​ሩ​ንም ድን​ኳን፥ በድ​ን​ኳ​ኑም ውስጥ የነ​በ​ረ​ውን የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ዕቃ ሁሉ አመጡ። 5ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን ከእ​ርሱ ጋር የተ​ሰ​በ​ሰቡ የእ​ስ​ራ​ኤል ማኅ​በር ሁሉ ከእ​ርሱ ጋር በታ​ቦቷ ፊት ሆነው፥ ከብ​ዛ​ታ​ቸው የተ​ነሣ የማ​ይ​ቈ​ጠ​ሩ​ት​ንና የማ​ይ​መ​ጠ​ኑ​ትን በጎ​ችና በሬ​ዎች ይሠዉ ነበር። 6ካህ​ና​ቱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን ታቦት በቤቱ በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳን ውስጥ ከኪ​ሩ​ቤል ክንፍ በታች ወደ ነበ​ረው ወደ ስፍ​ራዋ አገቧት። 7ኪሩ​ቤ​ልም በታ​ቦቷ ስፍራ ላይ ክን​ፎ​ቻ​ቸ​ውን ዘር​ግ​ተው ነበር፤ ኪሩ​ቤ​ልም ታቦቷ​ንና የተ​ቀ​ደሱ ዕቃ​ዎ​ችን በስ​ተ​ላይ በኩል ሸፍ​ነው ነበር። 8መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹም ረጃ​ጅ​ሞች ነበሩ፤ በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳኑ ፊት ከመ​ቅ​ደሱ ውስጥ ጫፎ​ቻ​ቸው ይታዩ ነበር፤ በውጭ ግን አይ​ታ​ዩም ነበር፤#ዕብ. “እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ አሉ” የሚል ይጨ​ም​ራል። 9በታ​ቦ​ቷም ውስጥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከግ​ብፅ ምድር በወጡ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ቃል ኪዳን ባደ​ረገ ጊዜ ሙሴ በኮ​ሬብ ካስ​ቀ​መ​ጣ​ቸው የቃል ኪዳን ጽላት ከሚ​ባ​ሉት ከሁ​ለቱ የድ​ን​ጋይ ጽላት በቀር ምንም አል​ነ​በ​ረ​ባ​ትም። 10ካህ​ና​ቱም ከመ​ቅ​ደሱ በወጡ ጊዜ ደመ​ናው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ሞላው። 11የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ቤቱን ሞል​ቶት ነበ​ርና ካህ​ናቱ ከደ​መ​ናው የተ​ነሣ ለማ​ገ​ል​ገል ይቆሙ ዘንድ አል​ቻ​ሉም።
12ያን​ጊ​ዜም ሰሎ​ሞን እን​ዲህ አለ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ በደ​መ​ናው ውስጥ እኖ​ራ​ለሁ ብሎ​አል፤ 13እኔም ለዘ​ለ​ዓ​ለም የም​ት​ኖ​ር​በ​ትን ማደ​ሪያ ቤት በእ​ው​ነት ሠራ​ሁ​ልህ።”
ንጉሡ ሰሎ​ሞን ለሕ​ዝቡ ያደ​ረ​ገው ንግ​ግር
(2ዜ.መ. 6፥3-11)
14ንጉ​ሡም ፊቱን ዘወር አድ​ርጎ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ጉባኤ ሁሉ መረ​ቃ​ቸው፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ጉባኤ ሁሉ ቆመው ነበር። 15እር​ሱም አለ፥ “ለአ​ባቴ ለዳ​ዊት በአፉ የተ​ና​ገረ፥ በእ​ጁም የፈ​ጸመ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን። 16ሕዝ​ቤን እስ​ራ​ኤ​ልን ከግ​ብፅ ካወ​ጣ​ሁ​በት ቀን ጀምሮ ስሜ በዚያ ይሆን ዘንድ በእ​ር​ስ​ዋም ቤት ይሠ​ራ​ልኝ ዘንድ፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ ሁሉ ከተ​ማን አል​መ​ረ​ጥ​ሁም፤ አሁን ግን ስሜ በዚያ ይሆን ዘንድ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን መር​ጫ​ለሁ፤ በሕ​ዝ​ቤም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ ይሆን ዘንድ ዳዊ​ትን መር​ጫ​ለሁ።” 17አባ​ቴም ዳዊት ለእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ቤት ይሠራ ዘንድ በልቡ አሰበ። 18እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አባ​ቴን ዳዊ​ትን፥ “ለስሜ ቤት ትሠራ ዘንድ በል​ብህ አስ​በ​ሃ​ልና ይህን በል​ብህ ማሰ​ብህ መል​ካም አደ​ረ​ግህ። 19ነገር ግን ከወ​ገ​ብህ የሚ​ወ​ጣው ልጅህ እርሱ ለስሜ ቤት ይሠ​ራል እንጂ ቤት የም​ት​ሠ​ራ​ልኝ አንተ አይ​ደ​ለ​ህም” አለው። 20እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል አጸና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተስፋ እንደ ሰጠ በአ​ባቴ በዳ​ዊት ፋንታ ተነ​ሣሁ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዙፋን ላይ ተቀ​መ​ጥሁ፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ቤት ሠራሁ። 21ከግ​ብ​ፅም ምድር ባወ​ጣ​ቸው ጊዜ ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ጋር ያደ​ረ​ገው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ኪዳን ላለ​ባት ታቦት ስፍ​ራን በዚያ አደ​ር​ግ​ሁ​ላት።
የሰ​ሎ​ሞን ጸሎት
(2ዜ.መ. 6፥12-42)
22የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ጉባኤ ሁሉ እያዩ ሰሎ​ሞን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ፊት ቆሞ እጆ​ቹን ወደ ሰማይ ዘረጋ። 23እን​ዲ​ህም አለ፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ አቤቱ! በላይ በሰ​ማይ፥ በታ​ችም በም​ድር አን​ተን የሚ​መ​ስል አም​ላክ የለም፤ በፍ​ጹም ልቡ በፊ​ትህ ለሚ​ሄድ ባሪ​ያህ ቃል ኪዳ​ን​ንና ምሕ​ረ​ትን የም​ት​ጠ​ብቅ፥ 24ለባ​ሪ​ያህ ለአ​ባቴ ለዳ​ዊት የሰ​ጠ​ኸ​ውን ተስፋ የጠ​በ​ቅህ፥ በአ​ፍህ ተና​ግ​ረህ፥ እንደ ዛሬ ቀንም በእ​ጅህ ፈጸ​ም​ኸው። 25አሁ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ አቤቱ፦ አንተ በፊቴ እንደ ሄድህ ልጆ​ችህ በፊቴ ይሄዱ ዘንድ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን ቢጠ​ብቁ፥ በፊቴ በእ​ስ​ራ​ኤል ዙፋን የሚ​ቀ​መጥ ሰው ከአ​ንተ አይ​ጠ​ፋም ብለህ ለአ​ባ​ቴ ለ​ዳ​ዊት ተስፋ የሰ​ጠ​ኽ​ውን ጠብቅ። 26አሁ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሆይ! ለባ​ሪ​ያህ ለአ​ባቴ ለዳ​ዊት የተ​ና​ገ​ር​ኸው ቃል እባ​ክህ እው​ነት ይሁን።
27“በውኑ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰው ጋር በም​ድር ላይ ይኖ​ራ​ልን? እነሆ ሰማይ ከሰ​ማ​ያ​ትም በላይ ያለው ሰማይ ይይ​ዝህ ዘንድ አይ​ች​ልም፤ ይል​ቁ​ንስ እኔ ለስ​ምህ የሠ​ራ​ሁት ቤት እን​ዴት ያንስ! 28አቤቱ አም​ላኬ ሆይ! ወደ ባሪ​ያህ ጸሎ​ትና ልመና ተመ​ል​ከት፤ ዛሬም ባሪ​ያህ በፊ​ትህ የሚ​ጸ​ል​የ​ውን ጸሎት ስማ፤ 29ባሪ​ያህ ወደ​ዚህ ስፍራ የሚ​ጸ​ል​የ​ውን ጸሎት ትሰማ ዘንድ፦ በዚያ ስሜ ይሆ​ናል ወዳ​ል​ኸው ስፍራ ወደ​ዚህ ቤት ዐይ​ኖ​ችህ ሌሊ​ትና ቀን የተ​ገ​ለጡ ይሁኑ። 30ባሪ​ያ​ህና ሕዝ​ብህ እስ​ራ​ኤል ወደ​ዚህ ስፍራ የሚ​ጸ​ል​ዩ​ትን ልመና ስማ፤ በማ​ደ​ሪ​ያህ በሰ​ማይ ስማ፤ ሰም​ተ​ህም ይቅር በል።
31“ሰው ባል​ጀ​ራ​ውን ቢበ​ድል፥ ይም​ልም ዘንድ በላዩ መሐላ ቢጫ​ን​በት፥ እር​ሱም መጥቶ በዚህ ቤት በመ​ሠ​ዊ​ያህ ፊት ቢና​ዘዝ፥ 32በሰ​ማይ ስማ፤ አድ​ር​ግም፤ በባ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ህም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ዳኛ ሁን፤ በበ​ደ​ለ​ኛ​ውም ላይ ፍረድ፤ መን​ገ​ዱ​ንም በራሱ ላይ መል​ስ​በት፤ ጻድ​ቁን አጽ​ድ​ቀው፤ እንደ ጽድ​ቁም ክፈ​ለው።
33“ሕዝ​ብህ እስ​ራ​ኤል አን​ተን ስለ በደሉ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው ፊት ድል ቢሆኑ፥ ወደ አን​ተም ቢመ​ለሱ፥ ለስ​ም​ህም ቢና​ዘዙ፥ 34በዚ​ህም ቤት ቢጸ​ል​ዩና ቢለ​ም​ኑህ፥ አንተ በሰ​ማይ ስማ፤ የሕ​ዝ​ብ​ህ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ኀጢ​አት ይቅር በል፤ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ወደ ሰጠ​ሃት ምድር መል​ሳ​ቸው።
35“አን​ተን ስለ በደሉ ሰማይ ቢዘጋ፥ ዝና​ብም ባይ​ዘ​ንብ፥ በዚ​ህም ስፍራ ቢጸ​ልዩ፥ ለስ​ም​ህም ቢና​ዘዙ፥ ባስ​ጨ​ነ​ቅ​ሃ​ቸ​ውም ጊዜ ከኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው ቢመ​ለሱ፥ 36አንተ በሰ​ማይ ስማ፤ የሚ​ሄ​ዱ​በ​ት​ንም መል​ካም መን​ገድ በማ​ሳ​የት የባ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ህ​ንና የሕ​ዝ​ብ​ህን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ኀጢ​አት ይቅር በል፤ ለሕ​ዝ​ብ​ህም ርስት አድ​ር​ገህ ለሰ​ጠ​ሃት ምድር ዝና​ብን ስጥ።
37“በም​ድር ላይም ራብ፥ ወይም ቸነ​ፈር፥ ወይም ዋግ፥ ወይም አረ​ማሞ ቢሆን፥ አን​በጣ፥ ወይም ኩብ​ኩባ ቢመጣ፥ የሕ​ዝ​ብ​ህም ጠላት ከከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው በአ​ን​ዲቱ ከብቦ ቢያ​ስ​ጨ​ን​ቃ​ቸው፥ መቅ​ሠ​ፍ​ትና ደዌ ሁሉ ቢሆን፥ 38ማና​ቸ​ውም ሰው የል​ቡን ሕመም ዐውቆ ጸሎ​ትና ምህላ ቢያ​ደ​ርግ፥ እጆ​ቹ​ንም ወደ​ዚህ ቤት ቢዘ​ረጋ፥ 39በማ​ደ​ሪ​ያህ በሰ​ማይ ስማ፤ ይቅ​ርም በል፤ አንተ ብቻ የሰ​ውን ልጆች ሁሉ ልብ ታው​ቃ​ለ​ህና ልቡን ለም​ታ​ው​ቀው ሰው ሁሉ እንደ መን​ገዱ ሁሉ መጠን ክፈ​ለ​ውና ስጠው። 40ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን በሰ​ጠ​ሃት ምድር ላይ በሚ​ኖ​ሩ​በት ዘመን ሁሉ ይፈ​ሩህ ዘንድ።
41“ከሕ​ዝ​ብ​ህም ከእ​ስ​ራ​ኤል ወገን ያል​ሆነ እን​ግዳ ስለ ስምህ ከሩቅ ሀገር ቢመጣ፥ 42ታላ​ቁን ስም​ህን፥ ብር​ቱ​ይ​ቱ​ንም እጅ​ህን፥ የተ​ዘ​ረ​ጋ​ች​ው​ንም ክን​ድ​ህን ሰም​ተው ቢመ​ጡና በዚህ ቤት ቢጸ​ልዩ፥ 43አንተ በማ​ደ​ሪ​ያህ በሰ​ማይ ስማ፤ የም​ድ​ርም አሕ​ዝብ ሁሉ ስም​ህን ያውቁ ዘንድ፥ እንደ ሕዝ​ብህ እንደ እስ​ራ​ኤል ይፈ​ሩህ ዘንድ፥ በዚ​ህም በሠ​ራ​ሁት ቤት ስምህ እንደ ተጠራ ያውቁ ዘንድ፥ እን​ግ​ዳው የሚ​ለ​ም​ን​ህን ሁሉ አድ​ርግ።
44“ሕዝ​ብ​ህም ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ለመ​ው​ጋት አንተ በም​ት​መ​ል​ሳ​ቸው መን​ገድ ቢወጡ፥ አን​ተም ወደ መረ​ጥ​ሃት ከተማ፥ እኔም ለስ​ምህ ወደ ሠራ​ሁት ቤት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ቢጸ​ልዩ፥ 45ጸሎ​ታ​ቸ​ው​ንና ልመ​ና​ቸ​ውን በሰ​ማይ ስማ፤ ፍር​ድ​ንም አድ​ር​ግ​ላ​ቸው።
46“የማ​ይ​በ​ድ​ልም ሰው የለ​ምና አን​ተን ቢበ​ድሉ፥ ተቈ​ጥ​ተ​ህም ለጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው አሳ​ል​ፈህ ብት​ሰ​ጣ​ቸው፥ ሩቅ ወይም ቅርብ ወደ ሆነ ወደ ጠላ​ቶች ሀገር ቢማ​ረ​ኩም፥ 47በተ​ማ​ረ​ኩ​በ​ትም ሀገር ሆነው በል​ባ​ቸው ንስሓ ቢገቡ፥ በተ​ማ​ረ​ኩ​በ​ትም ሀገር ሳሉ ተመ​ል​ሰው፦ ኀጢ​አት ሠር​ተ​ናል፥ በድ​ለ​ን​ማል፥ ክፉ​ንም አድ​ር​ገ​ናል ብለው ቢለ​ም​ኑህ፥ 48በማ​ረ​ኩ​አ​ቸው በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው ሀገር ሳሉ በፍ​ጹም ልባ​ቸ​ውና በፍ​ጹም ነፍ​ሳ​ቸው ወደ አንተ ቢመ​ለሱ፥ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ወደ ሰጠ​ሃት ወደ ምድ​ራ​ቸው ወደ መረ​ጥ​ሃ​ትም ከተማ ለስ​ም​ህም ወደ ሠራ​ሁት ቤት ቢጸ​ልዩ፥ 49ጸሎ​ታ​ቸ​ው​ንና ልመ​ና​ቸ​ውን በማ​ደ​ሪ​ያህ በሰ​ማይ ስማ፤#ዕብ. “ፍር​ድ​ንም አድ​ር​ግ​ላ​ቸው” የሚል ይጨ​ም​ራል። 50አን​ተ​ንም የበ​ደ​ሉ​ህን ሕዝ​ብ​ህን ፥ በአ​ን​ተም ላይ ያደ​ረ​ጉ​ትን በደ​ላ​ቸ​ውን ሁሉ ይቅር በል፤ ይራ​ሩ​ላ​ቸ​ውም ዘንድ በማ​ረ​ኩ​አ​ቸው ፊት ምሕ​ረ​ትን ስጣ​ቸው፤ 51ከግ​ብጽ ምድር ከብ​ረት እቶን ውስጥ ያወ​ጣ​ሃ​ቸው ሕዝ​ብ​ህና ርስ​ትህ ናቸ​ውና። 52በጠ​ሩህ ጊዜ ሁሉ ትሰ​ማ​ቸው ዘንድ ለባ​ሪ​ያ​ህና ለሕ​ዝ​ብህ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልመና ዐይ​ኖ​ችህ የተ​ገ​ለጡ፥ ጆሮ​ዎ​ችህ የተ​ከ​ፈቱ#“ጆሮ​ዎ​ችህ የተ​ከ​ፈቱ” የሚ​ለው በዕብ. የለም። ይሁኑ። 53ጌታዬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ! አባ​ቶ​ቻ​ች​ንን ከግ​ብፅ ባወ​ጣህ ጊዜ በባ​ሪ​ያህ በሙሴ እጅ እንደ ተና​ገ​ርህ ርስት ይሆ​ኑህ ዘንድ ከም​ድር አሕ​ዛብ ሁሉ ለይ​ተ​ሃ​ቸ​ዋ​ልና።”#የምዕ. 8 ቍ. 53 የመ​ጨ​ረ​ሻው ዐረ​ፍተ ነገር በዕብ. የለም። ያን​ጊ​ዜም ሰሎ​ሞን ሥራ​ውን በጨ​ረሰ ጊዜ ስለ​ዚያ ቤት እን​ዲህ ሲል ተና​ገረ። “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ማይ ፀሐ​ይን አሳየ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጨ​ለማ ውስጥ እን​ደ​ሚ​ኖር ተና​ገረ፤ ቤቴን ሥራ፤ በመ​ታ​ደ​ስም ለመ​ኖር ለራ​ስህ ጥሩ ቤትን ሥራ፤” ይህ​ችስ በመ​ሐ​ልይ መጽ​ሐፍ የተ​ጻ​ፈች አይ​ደ​ለ​ምን?
54ሰሎ​ሞ​ንም ይህ​ችን ጸሎ​ትና ልመና ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸልዮ በፈ​ጸመ ጊዜ፥ በጕ​ል​በቱ ተን​በ​ር​ክኮ፥ እጁ​ንም ወደ ሰማይ ዘር​ግቶ ነበ​ርና ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ፊት ከሰ​ገ​ደ​በት ተነሣ። 55ቆሞም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ጉባኤ ሁሉ በታ​ላቅ ድምፅ ሲመ​ርቅ እን​ዲህ አለ፦ 56“እንደ ተና​ገ​ረው ተስፋ ሁሉ ለሕ​ዝቡ ለእ​ስ​ራ​ኤል ዕረ​ፍ​ትን የሰጠ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን፥ በባ​ሪ​ያው በሙሴ ቃል ከተ​ና​ገ​ረው ከመ​ል​ካም ቃል ሁሉ ያጐ​ደ​ለው አን​ድም ቃል የለም። 57አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ጋር እንደ ነበረ ከእ​ኛም ጋር ይሁን፤ አይ​ተ​ወን፤ አይ​ጣ​ለ​ንም፤ 58በመ​ን​ገ​ዱም ሁሉ እን​ሄድ ዘንድ፥ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ንም ያዘ​ዛ​ትን ትእ​ዛ​ዙ​ንና ሥር​ዐ​ቱን እን​ጠ​ብቅ ዘንድ፥ ልባ​ች​ንን ወደ እርሱ ይመ​ልስ። 59ለባ​ሪ​ያ​ውና ለሕ​ዝቡ እስ​ራ​ኤል በየ​ዕ​ለቱ ፍር​ድን ያደ​ርግ ዘንድ ይህች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የለ​መ​ን​ኋት ቃል በቀ​ንና በሌ​ሊት ወደ አም​ላ​ካ​ችን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቀ​ረ​በች ትሁን፤ 60የም​ድር አሕ​ዛብ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ አም​ላክ እንደ ሆነ፥ ከእ​ር​ሱም በቀር ሌላ እንደ ሌለ ያውቁ ዘንድ፥ 61እንደ ዛሬው ቀን በሥ​ር​ዐቱ እን​ሄድ ዘንድ፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም እን​ጠ​ብቅ ዘንድ፥ ከአ​ም​ላ​ካ​ችን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ልባ​ችን ፍጹም ይሁን።”
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ቅዳሴ
(2ዜ.መ. 7፥4-10)
62ንጉ​ሡም ከእ​ር​ሱም ጋር የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት መሥ​ዋ​ዕት ሠዉ። 63ንጉሡ ሰሎ​ሞ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ሰላም መሥ​ዋ​ዕት ሃያ ሁለት ሺህ በሬ​ዎ​ች​ንና መቶ ሃያ ሺህ በጎ​ችን አቀ​ረበ። ንጉ​ሡና የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ እን​ዲሁ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ቀደሱ፤ አከ​በ​ሩም። 64በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያለው የናሱ መሠ​ዊያ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የእ​ህ​ሉን ቍር​ባን የሰ​ላ​ሙ​ንም መሥ​ዋ​ዕት ስብ ይይዝ ዘንድ ታናሽ ስለ ነበረ፥ በዚያ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የእ​ህ​ሉን ቍር​ባን፥ የሰ​ላ​ሙ​ንም መሥ​ዋ​ዕት ስብ አሳ​ር​ጎ​አ​ልና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ፊት የነ​በ​ረ​ውን የአ​ደ​ባ​ባ​ዩን መካ​ከል ንጉሡ በዚያ ቀን ቀደሰ። 65በዚ​ያም ዘመን ሰሎ​ሞን፥ ከእ​ር​ሱም ጋር እስ​ራ​ኤል ሁሉ ከኤ​ማት መግ​ቢያ ጀምሮ እስከ ግብፅ ወንዝ ድረስ ያለው ታላቅ ጉባኤ፥ እርሱ በሠ​ራው ቤት ውስጥ በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እየ​በ​ሉና እየ​ጠጡ፥ ደስ​ታም እያ​ደ​ረጉ ሰባት ቀን በዓ​ሉን አከ​በሩ። 66በስ​ም​ን​ተ​ኛ​ውም ቀን ሕዝ​ቡን አሰ​ና​በተ፤ እነ​ር​ሱም ንጉ​ሡን መረቁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለባ​ሪ​ያው ለዳ​ዊ​ትና ለሕ​ዝቡ ለእ​ስ​ራ​ኤል ስላ​ደ​ረ​ገው ቸር​ነት ሁሉ በል​ባ​ቸው ደስ ብሏ​ቸው፥ ሐሴ​ትም አድ​ር​ገው ወደ እየ​ቤ​ታ​ቸው ሄዱ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ