መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 22:37-39
መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 22:37-39 አማ2000
ወደ ሰማርያም መጡ፤ ንጉሡንም በሰማርያ ቀበሩት፤ ሰረገላውንም በሰማርያ ምንጭ አጠቡት። እግዚአብሔርም በነቢዩ አድሮ እንደ ተናገረ ውሾችና ጅቦች ደሙን ላሱት። አመንዝሮች ሴቶችም በደሙ ታጠቡበት። የቀረውም የአክዓብ ነገር፥ ያደረገውም ነገር ሁሉ፥ ከዝሆን ጥርስም የሠራው ቤት፥ የሠራቸውም ከተሞች ሁሉ፥ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተጽፎአል።