መጽ​ሐፈ ነገ​ሥት ቀዳ​ማዊ 22:37-39

መጽ​ሐፈ ነገ​ሥት ቀዳ​ማዊ 22:37-39 አማ2000

ወደ ሰማ​ር​ያም መጡ፤ ንጉ​ሡ​ንም በሰ​ማ​ርያ ቀበ​ሩት፤ ሰረ​ገ​ላ​ው​ንም በሰ​ማ​ርያ ምንጭ አጠ​ቡት። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በነ​ቢዩ አድሮ እንደ ተና​ገረ ውሾ​ችና ጅቦች ደሙን ላሱት። አመ​ን​ዝ​ሮች ሴቶ​ችም በደሙ ታጠ​ቡ​በት። የቀ​ረ​ውም የአ​ክ​ዓብ ነገር፥ ያደ​ረ​ገ​ውም ነገር ሁሉ፥ ከዝ​ሆን ጥር​ስም የሠ​ራው ቤት፥ የሠ​ራ​ቸ​ውም ከተ​ሞች ሁሉ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ ተጽ​ፎ​አል።