መጽ​ሐፈ ነገ​ሥት ቀዳ​ማዊ 17:17-20

መጽ​ሐፈ ነገ​ሥት ቀዳ​ማዊ 17:17-20 አማ2000

ከዚ​ያም በኋላ የባ​ለ​ቤ​ቲቱ የዚ​ያች ሴት ልጅ ታመመ፤ ትን​ፋ​ሹም እስ​ኪ​ታጣ ድረስ ደዌው እጅግ ከባድ ነበረ። እር​ስ​ዋም ኤል​ያ​ስን፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ሆይ፥ እኔ ከአ​ንተ ጋር ምን አለኝ? አን​ተስ ከእኔ ጋር ምን አለህ? ኀጢ​አ​ቴ​ንስ ታሳ​ስብ ዘንድ፥ ልጄ​ንስ ትገ​ድል ዘንድ ወደ እኔ መጥ​ተ​ሃ​ልን?” አለ​ችው። ኤል​ያ​ስም፥ “ልጅ​ሽን ስጪኝ” አላት፥ ከብ​ብ​ቷም ወስዶ ተቀ​ም​ጦ​በት ወደ ነበ​ረው ሰገ​ነት አወ​ጣው፤ በአ​ል​ጋ​ውም ላይ አስ​ተ​ኛው። ኤል​ያ​ስም፥ “እኔ በቤቷ ያደ​ርሁ የዚች መበ​ለት ምስ​ክ​ርዋ ጌታዬ ሆይ፥ ልጅ​ዋን በመ​ግ​ደ​ልህ ክፉ አድ​ር​ገ​ህ​ባ​ታ​ልና ወዮ​ልኝ!” ብሎ ጮኸ።